No summary available.
መጋቢት 23 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ኂሩት መለሰ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካቾች፡-
በዚህ መዝገብ የቀረበው ጉዲይ የፍርድ አፈፃፀም የሚመለከት ነው። የአሁን አመልካቾች የውርስ ንብረት ከተጠሪ ለመካፈል ያቀረቡትን የአፈፃፀም ክስ የተመለከተው የምሥራቅ ጏጃም ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በብቸና ከተማ የሚገኘው ድርጅት እና መኖሪያ ቤት በአፈፃፀም ተከሳሽ ሳይሆን በልላ ሦስተኛ ወገን ስም ተመዝግቦ የሚገኝ ስለመሆኑ ማዘጋጃ ቤቱ ማረጋገጫ ሰጥቷል በሚል የአመልካቾችን የአፈፃፀም ጥያቄ ላላ ንብረት አፈላልገው ያቅርቡ በሚል ተዘግቷል። የአሁን አመልካቾች ለአማራ ብ/ክ/መ/ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት እና ሰበር ሰሚ ችልት አቤቱታ ያቀረቡ ቢሆንም ተቀባይነት አላገኙም።
ለዚህ ሰበር ያቀረቡት አቤቱታ ይዘት ባጭሩ አከራካሪው ንብረት ውሳኔ ያፈረበት መሆኑን ጠቅሰው የአፈፃፀም ሂደት ለማሰናከል ተጠሪ በተንኮል በልጃቸው ስም ያዛወሩ ስለመሆኑ ገልፀው ቀደም ሲል በተወሰነው መሰረት እንዱፈጸም እንዱታዘዝ አመልክቷል።
ሰበር ሰሚ ችልትም መዝገቡን መርምሮ ውሳኔ ያረፈበትን ቤት በተጠሪ ሳይሆን በልላ ሰው ስም ነው በሚል አመልካቾች ላላ ንብረት እንዱጠቁሙ መታዘዙ በአግባቡ ስለመሆኑ ለመመርመር ተጠሪን አስቀርቧል። ተጠሪ ህዲር 8/2002 ዓ.ም በጽሐፍ ባቀረቡት መልስ ወ/ሮ አበባ ደርሰሕ በስሟ አዘዋውራ የያዘቸው ቤት በተመለከተ ተጠሪ የፈጸሙት ተንኮል የላለ ስለመሆኑ የቤቱም መገምት ባለመብት እንደማያደርግ እንዱሁም በብቸና ከተማ ቀበላ 02 አዱስ ገበያ ተብል በሚጠራ የድርጅት ቤት የወ/ሮ ዘምዘም ጓደ ደርሰህ የግል ሐብት ስለመሆኑ እና የቤት ቁጥር 772 የወ/ሮ አበባ ጓደ ደርሰህ በሰሟ አዛውራ ይዛ የምትገኝ መሆኑን ዘርዝረው ተጠሪ ኃላፉነት የላለባቸው ስለመሆኑ አጥብቀው ተከራክረዋል። አመልካቾችም በመልስ መልሳቸው በልጆቻቸው ስም ያዛወሩዋቸው ንብረቶች ውሳኔ ያረፈባቸው መሆን ጠቅሰው ክርክራቸውን አጠናክረዋል። እኛም የግራ ቀኙን ክርክር ከሥር ፍ/ቤት ውሳኔ አንፃር መርምረናል። ስለዚህ የአፈፃፀም ክርክር መነሻ የሆነው ውሳኔ በም/ጏጃም ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 2284 በ2/13/98 ዓ.ም የተሰጠው መሆኑ ከመዝገቡ ተረድተናል። ከዚህ ውሳኔ ይዘት መረዲት የተቻለው አንደኛ በአዱሱ ገበያ አካባቢ የሚገኝ የድርጅት ቤት ቁጥር አዱስ በአቶ ጓድ ደርሰህ ስም መሆኑ፤ሁለተኛ በብቸና ከተማ 02 ቀበላ ከድሮ ገበያ አካባቢ የሚገኘው መኖሪያ ቤት በወ/ሮ አበባ ጓድ ስም መሆኑ እና በሦስተኛ ደረጃ ከብት ገበያ መሓጃ መንገድ ያለው ቤት በወ/ሮ አስረስ አህመድ ስም ያለ መሆኑ ተጠቅሶ ከማዘጋጃው በተሰጠ ማረጋገጫ መሰረት ወደ ከብት ገበያ መሓጃ የሚገኘው ቤት የውርስ ንብረት ሆኖ ግራ ቀኙ እንዱከፊፈለ መወሰኑን ነው። እንዱሁም በሟች ስም የሚታወቅ ድርጅት ቤት ከገበያ አካባቢ የሚገኝ እንዱካፈለ መወሰኑን ያመለክታል። ከዚህ ውሳኔ መነሻ አፈፃፀም ላይ አከራካሪ የሆነው ጉዲይ ውሳኔ ያረፈበትን ቤት እና ድርጅት ተጠሪ ከውሳኔው በኋላ በልጆቻቸው ስም አዛውረዋል የሚል ነው። የሥር ፍ/ቤት በተጠሪ ስም ያለ አንድ መኖሪያ ቤት እና በሟች ስም ያለ አንድ ድርጅት ቤት አመልካቾች እንዱካፈለ ከወሰነ በኋላ በአፈፃፀም ክርክር ሂደት እነዚህ ቤቶች እንዳት ሉተላለፈ እንደቻለ ሳያጣራ ቤቶቹ በሦስትኛ ወገን ስም የተመዘገቡ ናቸው በማለት ውሳኔውን ሳያስፈጽም መቅረቱን ተረድተናል።
በመሰረቱ አፈፃፀም የያዘው ፍ/ቤት በዋናው ፍርድ የተሰጠውን ውሳኔ ማስፈጸም ይጠበቅበታል። ፍርድ አስፈፃሚው ፍርድ ቤት እንደ ፍርድ ማስፈጸም አሉያም ያልተፈፀመበትን ምክንያት በመዝርዝር በግልጽ ማመልከት እንዲለበት የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ድንጋጌ ቁጥር 374 ያመለክታል።
በተያዘው ጉዲይ ዋና ፍርድ ያፈረበትን ቤትና የድርጅት ቤት በአፈፃፀም ተከሳሽ ሳይሆን በልላ ሦስትኛ ወገን የተመዘገበ ስለመሆኑ የሥር ፍ/ቤት ውሳኔ ላለማስፈጸም መሰናክል መሆኑን የጠቀሰ ስለመሆኑ ከውሳኔው ተረድተናል።
በአመልካቾች በኩል የቀረበው አቤቱታ ደግሞ የሚያመለክተው ተጠሪ ንብረቶቹን በተንኮል ድርጊት ከፍርድ በኋላ በልጆቻቸው ስም አዙረዋል የሚል ነው። በዚህ ረገድ የሥር ፍ/ቤት ያደረገው ማጣራት ሥራ የለም። ከፍ ሲል እንደተጠቀሰው ንብረቶቹ የውርስ ንብረት ናቸው ተብል ውሳኔ ካረፈበት በኋላ በምን አግባብ ወደ ሦስተኛ ወገን እንደተላለፈ ማጣራት አስፈላጊ እና በመሰረታዊ ጉዲይ ነው።
No topics extracted.
ስለሆነም ይህንን ፍሬ ነገር ማጣራት እና ውጤቱ ምን ላሆን እንደሚችል መወሰን ተገቢ ሆኖ አግኝተናል።
ስለዚህም የሥር ፍ/ቤት ይህንኑ ሳያጣራ አመልካቾች ላላ ንብረት ይጠቀሙ ሲል የአፈፃፀም መዝገቡን ለጊዜው መዝጋቱ መሰረታዊ የሕግ ሰሕተት የተፈፀመበት ሆኖ አግኝተናል። ስለሆነም ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
00580 የሰጠው ትእዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
በተጠሪ እና በሟች ስም የነበረው ቤት እና ድርጅት የውርስ ንብረት ነው ተብል በዋናው ፍርድ እንዱከፊፈለ ከተፈረደ በኋላ በአፈፃፀም ክርክር ሂደት ንብረቶቹ በሦስተኛ ወገን የተመዘገቡበት አግባብ እና ውጤቱን አስመልክቶ ተገቢውን ማጣራት በማድረግ ውሳኔ እንዱሰጥበት ብለን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 343/1/ መሰረት መዝገቡን ለምሥራቅ ጏጃም ከፍተኛ ፍ/ቤት መልሰናል።
የዚህን ፍ/ቤት ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኝ የየራሳቸውን ይቻለ። ይፃፍ። መዝገቡ ተዘግቷል ይመለስ።