No summary available.
መጋቢት 29 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ሐጏስ ወልደ ሂሩት መለሰ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- 5 ብራዘርስ ኃ.የተ.የግል ማህበር - ክበበው ደስታ ቀረበ ተጠሪ፡- ዓብደላ ኢብሮ ዮሴፍ - ቀረበ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
አመልካች የሰበር አቤቱታ ያቀረበው ቀደም ሲል በላለሁበት የተሰጠው ውሳኔ ተነስቶ ወደ ክርክሩ እንድገባ በማለት ያቀረብኩት ጥያቄ ከሕግ ውጪ ተቀባይነት አጥቶአል በማለት ነው። ከመዝገቡ እንደሚታየው ተጠሪ በአመልካች እና ሰልሞን ጀንበሩ በተባለው ግለሰብ ላይ ክስ መስርቶ የጉዲት ካሣ እንዱከፈለው አስወስኖአል። ተጠሪ ክሱን የመሰረተው በሰልሞን ጀምበሩ ሹፋርነት ሲሽከረከር የነበረው የአመልካች ንብረት የሆነው መኪና ገጭቶ ጉዲት አድርሶብኛል በማለት ሲሆን፣ በፍ/ቤቱ የታዘዘለትን መጥሪያ ለማድረስ ሞክሮ ተከሳሾችን ማግኘት እንዲልቻለ ለፍ/ቤቱ በመግለጹም ፍ/ቤቱ መጥሪያው በፍ/ቤቱ ቅጥር ግቢ እንዱለጠፍ በማለት ምትክ የመጥሪያ አደራረስ ትዕዛዝ ሰጥቶአል።
ከዚህ በኋላም ተከሳሾች ተጠርተው አልቀረቡም በማለት ክርክሩን ተከሳሾች በላለበት ሰምቶ ውሳኔውን ሰጥቶአል።
አመልካች ከዚህ በኋላ ነው በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ.78 የተመለከተውን ድንጋጌ መሰረት በማድረግ አቤቱታ ያቀረበው።
አቤቱታው የቀረበለት የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ግን አቤቱታውን ባለመቀበል ብይን የሰጠ ሲሆን፣ ይግባኝ የቀረበለት የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤትም ብይኑን አፅንቶአል። የሰበር አቤቱታው የቀረበው በዚህ ላይ ነው።
በበኩላችንም አመልካች ጥቅምት 24 ቀን 2002 ዓ.ም በጻፈው ማመልከቻ ያቀረበውን አቤቱታ መሰረት በማድረግ ክርክሩን ሰምተናል። አቤቱታው በሰበር ችልት እንዱታይ የተደረገው የሥር ፍ/ቤቶች አመልካች በአግባቡ ተጠርቶ ሳይቀርብ ቀርቶአል በማለት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ.78 መሰረት የቀረበውን ጥያቄ ውድቅ ያደረገበትን አግባብ ለመመርመር ነው። በዚህ መሰረትም ይህን ነጥብ ከቀረበልን ክርክር፣ የሥር ፍ/ቤቶች ከሰጡት ውሳኔ እና ከሕጉ ጋር አገናዝበን መርምረናል።
ከሥር ጀምሮ ከተካሄደው ክርክር እና ፍ/ቤቶቹ ከሰጡት ውሳኔ መገንዘብ እንደቻልነው መጥሪያው በፍ/ቤቱ ቅጥር ግቢ እንዱለጠፍ ምትክ የመጥሪያ አደራረስ ትዕዛዝ የተሰጠው ተጠሪ የአመልካችን አድራሻ አላውቅም በማለቱ ነው።
ከዚህ ውጪ ግን አመልካች የንግድ ድርጅት እንደመሆኑ መጠን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ.97 በተመለከተው አይነት መጥሪያው እንዱደርሰው ስለመታዘዙ ወይም በዚህ መሰረት ትዕዛዙ ተላልፍ ለመቀበል ፈቃደኛ ሳይሆን ስለመቅረቱ በተመለከተ ምንም የተባለ ነገር የለም። ላላው ቀርቶ ተጠሪ አመልካችን ፈልጎ ለማግኘት ያልቻለው መጥሪያውን በየትኛው አድራሻው ወስድ ፍለጋ አድርጎ እንደሆነ አልተረጋገጠም። አመልካች የንግድ ድርጅት (ሃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር) ስለሆነ ተመዝግቦ ንግደን የሚያካሂድበት መስሪያ ቤት ወይም ጽ/ቤት እንዲለው ይገመታል። ተጠሪ ጉዲቱን ያደረሰበት መኪና የአመልካች ንብረት መሆኑ እስካወቀ ድረስ አድራሻውን ማወቅ አይችልም ማለትም የሚያስቸግር ነው።
ተከሳሽን በአግባቡ መጥራት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕጉ ከተቀመጡት የመስማት መብት ከሚረጋገጥባቸው መርሆዎች አንደ ነው። ይህን መርህ ባለመጠበቅ የሚሰጠው ትዕዛዝ ወይም ውሳኔ በሕጉ አግባብ እንደተሰጠ አይቆጠርም።
በመሆኑም ክሱ የቀረበለት ፍ/ቤት ወደጉዲዩ ሥረ-ነገር ገብቶ ተከሣሹን ባለዕዲ የሚያደርግ ውሳኔ ከመሰጠቱ በፉት ተከሳሹን በአግባቡ ስለመጠራቱ ማረጋገጥ ይጠበቅበታል። በያዝነው ጉዲይ እንደምናየው ክሱን የሰማው ፍ/ቤት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ.95(3) እና 97 በተደነገገው መሰረት መጥሪያው ለአመልካች ስለመላኩ አላረጋገጠም። በመሆኑም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ.105 መሰረት ምትክ የመጥሪያ አሰጣጥ ትዕዛዝ የሰጠው በአግባቡ አልነበረም። ሲጠቃለል ፍ/ቤቱ አመልካችን በሕጉ አግባብ መሰረት እንዱጠራ አድርጎአል ለማለት የሚቻል አይደለም። ሁኔታው ይህ ከሆነ ደግሞ አመልካች በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ.78(1) መሰረት ያቀረበለትን ጥያቄ አልቀበልም የሚልበት የሕግ ምክንያት የለም።
ጥያቄውን ውድቅ በማድረጉም የአመልካችን የመከራከር መብት የሚጎዲ ውሳኔ ሰጥቶአል ለማለት የሚቻል በመሆኑ ውሳኔው በሕጉ አተረጓጎም ረገድ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው ብለናል።
No topics extracted.
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ. ሰኔ 3 ቀን 2001 ዓ.ም የሰጠው ብይን እና የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ. ጥቅምት 11 ቀን 2002 ዓ.ም የሰጠው ፍርድ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ.348(1) መሰረት ተሽረዋል።
አመልካች በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ.78(1) መሰረት ያቀረበው ጥያቄ ተቀባይነት ያለው በመሆኑ ክሱ አመልካች ባለበት ይሰማ ብለናል።
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አመልካችን ወደ ጉዲዩ በማስገባት ክሱን እንደገና ከሰማ በኋላ ተገቢውን ይወስን ብለናል። ይጻፍ።