No summary available.
መጋቢት 06 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ መንበረፀሐይ ታደሰ ሂሩት መለሰ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- ወ/ሮ ሰኢዲ ሁሴን ይመር ተጠሪ፡- የለም **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ የፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፍትሐብሕር ይግባኝ ችልት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 480 ስር የተመለከተውን መሰረት በማድረግ ያስተላለፈውን የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት በመሆኑ ሉታረም ይገባል በማለት አመልካች ነሐሴ 07 ቀን 2001 ዓ.ም በተፃፈ ማመልከቻ ስላመለከቱ የቀረበ ነው።
አመልካች በጠቅላይ ፍርድ ቤት የፍትሐብሕር ይግባኝ ሰሚ ችልት የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈፅሟል የሚለት አመልካች ፈፀሙ የተባለት ድርጊት ስለመፈፀሙ በአሳማኝ ማስረጃ ያልተረጋገጠ መሆኑን፣ ድርጊቱ ስለመፈፀሙ ከችልቱ ውጪ ላላ ምርመራ ተከናውኖ ባግባቡ ሉጣራ ይችል የነበረ እንጂ ለውሳኔው መሰረት የሆነውን ድንጋጌ የማያሟላ መሆኑን፣ ችልቱ የአመልካችን መከላከያ ማስረጃዎችን የመዘነበት አግባብ የማስረጃ አሰማም እና ምዘና ሥርዓትን ያልተከተለ መሆኑን ያሳያለ ያሎቸውን ምክንያቶችን በመዘርዘር ነው።
ይህ ችልትም የአመልካችን አቤቱታ ለአቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ ግልባጭ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሯል።
በዚህም መሰረት አመልካች ጥፊተኛ የተባለት በፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከሶሪቲ ኢንተርናሽናል ትሬዱንግ ጋር በነበረባቸው የፍትሐብሕር ይግባኝ ክርክር ጉዲዩ ገና በምርመራ ላይ ባለበት ሁኔታ ጉዲዩ አልቋል፣ አስጨርሼአለሁ፣ የተፈረደላችሁን ገንዘብ አታገኙም፣ ጉዲዩን ለማስጨረስ ከዳኞች ጋር ተነጋግሬ ገንዘብም ከፍያለሁ እያለ ስለመናገራቸው ለጉዲዩ መልስ ሰጪ የነበረው ሶሪቲ ኢንተርናሽናል ትሬዱንግ ባቀረባቸው ማስረጃዎች ተረጋግጧል ተብል እና ይህ አድራጎት ደግሞ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 480 ስር የተመለከተውን ድንጋጌ ያሟላል በሚል ነው። አመልካች የፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የፍትሐብሕር ይግባኝ ሰሚ ችልት ድርጊቱ ስለመፈፀሙ የሰማቸው ምስክሮች ቃል ክብደት ተሰጥቶ በአንፃሩ የአመልካች ምስክሮች ቃል ክብደት ውድቅ ያደረገው ያላግባብ ነው፣ ድርጊቱ ስለመፈፀሙ በቂና አሳማኝ ማስረጃ አልቀረበብኝም በማለት የሚከራከሩ ቢሆንም የስር ፍርድ ቤት በቂ ማስረጃ አስቀርቦ የግራ ቀኙን ማስረጃዎችን ቃል በመመዘን የወሰነ መሆኑን ስለተገነዘብን እና ይህ ችልት የማስረጃ ምዘናን በተመለከተ ስልጣን የላለው በመሆኑ አመልካች በዚህ ረገድ ያቀረቡትን ክርክር የምንቀበለው ሆኖ አላገኘነውም።
አመልካች አጥብቀው የሚከራከሩት ላላው ነጥብ፤ ተፈፀመ የተባለው ድርጊት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 480 ስር የተመለከተውን ድንጋጌ የማያቋቁም፣ ራሱን የቻለ ምርመራ ላደረግበት የሚችል እንጂ ችልቱ በራሱ ወዱያውኑ በቀጥታ ቅጣት እንዱያስተላልፍ ስልጣን የሚሰጠው አይደለም በሚል ነው።
በመሰረቱ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 480 ይዘት ሲታይ የማንኛውም ችልት ሰብሳቢ ዲኛ የፍርድ ቤቱን የዲኝነት ስራ አካሓድ ስነ ስርዓት ለማስከበር ማናቸውንም አስፈላጊ መስል የታየውን እርምጃ ሉወስድ እንደሚችል፣ ይህንንም ለማስፈፀም ለፍርድ ቤቱ ችልት ክብር ወይም ለዲኝነቱ ሥነ-ሥርዓት መልካም አመራር ተቃራኒ የሆነ ጠባይ የሚያሳየውን ማናቸውንም ተከራካሪ ወገን ወይም ጠበቃ ወይም በችልቱ ውስጥ የሚገኘውን ማናቸውንም ሰው ተቃራኒ ተግባር በሰራበት ጊዜ በያዘው መዝገብ ላይ የገንዘብ መቀጮ ሉወስንበት የሚችል ስለመሆኑ ያስገነዝባል። ድንጋጌው በፍርድ ቤቱ እይታ ውስጥ ወይም ፉት ለፉት የተፈፀሙ፤ የፍርድ ቤቱን ስራ የሚያውኩ ተግባሮችን ማስቆም፣ አስፈላጊ እርምጃዎች እንዱወሰድ ለፍርድ ቤቱ ወዱያውኑ በቀጥታ የመወሰን ስልጣን የሚሰጥ መሆኑን እንገነዘባለን። የድንጋጌው አስፈላጊነትም ተከራካሪ ወገኖችም ሆኑ ማናቸውም ግለሰብ የሚፈፅሟቸው ተግባሮች የፍርድ ቤትን ሥርዓትና ክብር የሚያናጉ፣ ህብረተሰቡ በፍርድ ቤት ላይ ያለውን አመኔታ የሚቀንሱ ከሆነ ማስወገድ ነው ተብል ይታሰባል።
ወደ ተያዘው ጉዲይ ስንመለስም አመልካች ጥፊተኛ የተባለት በፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከሶሪቲ ኢንተርናሽናል ትሬዱንግ ጋር በነበረባቸው የፍትሐብሕር ይግባኝ ክርክር ጉዲዩ ገና በምርመራ ላይ ባለበት ሁኔታ ጉዲዩ አልቋል፣ አስጨርሼአለሁ፣ የተፈረደላችሁን ገንዘብ አታገኙም፣ ጉዲዩን ለማስጨረስ ከዳኞች ጋር ተነጋግሬ ገንዘብም ከፍያለሁ እያለ ማስወራታቸው በሚገባ በማስረጃ ተረጋግጦባቸው ነው። ይህ አድራጎት የዲኝነትን ክብርን፣ የዲኝነት አስተዲደርን የሚነካ፣ ሕብረተሰቡ በፍርድ ቤቱ ላይ እምነት እንዲይኖረው የሚያደርግ ስለመሆኑ ግልፅ ነው። በመሆኑም የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አመልካች ያስወሩት ተግባር በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 480 ስር የተመለከተውን ድንጋጌ የሚያሟላ ነው በማለት አመልካችን ወዱያውኑ በቀጥታ በያዘው መዝገብ ጥፊተኛ በማድረግ በብር 10,000.00(አስር ሺህ) መቅጣቱ ሕጋዊ እንጂ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው ለማለት የሚያስችል ሆኖ ስላላገኘነው ውሳኔው ሉፀና የሚገባው ሆኖ ተገኝቷል። በዚህም መሰረት ተከታዩን ወስነናል።
No topics extracted.
ው ሣ ኔ
በፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመ/ ሐምል 30 ቀን 2001 ዓ.ም የሰጠው የጥፊተኝነትም ሆነ የቅጣት ውሳኔ ፀንቷል።
መዝገቡ ተዘግቷል፤ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።