No summary available.
መጋቢት 20 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ኂሩት መለሰ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- ወ/ሮ ሰዓዲ ኢድሪስ - ወኪል አደም እንድሪስ ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ረሺድ ቡባ - ቀረቡ
በዚህ መዝገብ የቀረበው ጉዲይ የሥነ-ሥርአት ህጉን የሚመለከት ነው። ተጠሪ በድሬዲዋ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ባቀረቡት ክስ ከአውራሻቸው ከወ/ሮ ለላ መሐመድ በኑዛዜ ያገኘሁትን ቤትና ቦታ የመሬት ልማት ባለስልጣን (የስር አንደኛ ተከሳሽ) መብት ሳይኖረው አሳልፍ ለአመልካች ስለሰጠ ተከሳሾቹ ቤቱና ቦታውን እንዱያስረክቧቸው እንዱወሰንላቸው አመልክተው ፍ/ቤቱ ግራ ቀኙን ካከራከረ በኋላ የከሳሽ አውራሽ ራሳቸው በቤቱ ላይ መብት የነበራቸው ስለመሆኑ የቀረበ ማስረጃ ስለላለ ክሱ ተቀባይነት የለውም በማለት ውድቅ አድርጏታል።
በዚህ ውሳኔ ላይ ተጠሪ ለድሬዲዋ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት ይግባኝ አቅርበው ፍ/ቤቱ ይግባኙን ባለመቀበል መዝገቡን ዘግቷል። ከዚህ በኋላ ተጠሪ የስር ፍ/ቤት በውሳኔው ላይ የቤቱን ካርታ ቁጥር 6001 ከማለት ፊንታ 001 ብል ስለመዘገበው ይኸው የቁጥር ስህተት እንዱታረም ለስር ፍ/ቤት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 208 መሰረት አመልክተው ፍ/ቤቱ የቁጥሩን ስህተት አርሟል። ተጠሪም ይህን ትእዛዝ መነሻ በማድረግ ቀደም ሲል በድሬዲዋ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት ይግባኝ አቅርበው ውድቅ የተደረገባቸውን መዝገብ ያንቀሳቅሳለ። ፍ/ቤቱም የተዘጋውን ይግባኝ ከቀረበው ማስተካከያ አንፃር ለመመረመር ይግባኙ አመልካችን ያስቀርባል በማለት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ ተጠሪ ቤቱ ላይ መብት አላቸው በማለት የስር ፍ/ቤት ውሳኔን ሽሯል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሳኔ ላይ ነው። አመልካችም የድሬዲዋ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 337 መሰረት የዘጋውን የይግባኝ መዝገብ የስር ፍ/ቤት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 208 መሰረት የሰጠውን እርምት መሰረት በማድረግ እንቀሳቅሶ ውሳኔ መስጠቱ መሰረታዊ ሥነሥርአት ሕግ ስህተት ነው የሚልና ላልች ቅሬታዎች አቅርበዋል። ይህ ችልትም ይህንኑ ነጥብ ለመመርመር ሲል አቤቱታው ለሰበር ችልት ያስቀርባል በማለቱ ግራ ቀኙ ቀርበው ክርክራቸውን በጽሁፍ አቅርበዋል።
በልላ በኩል የስር አንደኛ ተከሳሽ የነበረው የመሬት አስተዲደር የድሬዲዋ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት በሰጠው ውሳኔ ላይ በሰበር መ/ቁ. 45172 የሰበር አቤቱታ ያቀረበ ሲሆን ችልቱም መዝገቡ ከመ/ቁ. 44931 ጋር እንዱታይ ያስቀርባል በማለቱ ግራ ቀኙ ክርክራቸውን በፁሁፍ አቅርበዋል። በሁለቱ መዝገቦች የቀረበው ጉዲይ ተመሳሳይ በመሆኑም ችልቱ ሁለቱንም መዝገቦች አጣምሮ ከተያዘው ጭብጥ አኳያ መርምሯል።
ተጠሪ የድሬዲዋ ከተማ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በሰጠው ውሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኛቸውን ለከተማው ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት አቅርበው ይግባኙ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 377 መሰረት ተዘግቶ መዝገቡ የመጨረሻ ውሳኔ አግኝቷል። ተጠሪ በዚህ ውሳኔ ላይ የሰበር አቤቱታ ከማቅረብ ይልቅ የወሰደት አማራጭ ውሳኔ እንደገና እንዱታይላቸው ለይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት ማመልከትን ነው። ተጠሪ ውሳኔ ያገኘው ጉዲይ እንደገና እንዱታይላቸው ያመለከቱትም የስር ፍ/ቤቱ በውሳኔው ላይ የቤቱን ካርታ ቁጥር አሳስቶ የፃፈው መሆኑን በመግለጽ ቁጥሩ እንዱታረምላቸው ባቀረቡት አቤቱታ መሰረት የተሰጠው የማስተካከያ ትእዛዝ መሰረት አድርገው ነው። በመሆኑም ይህ ማስተካከያ ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት የሰጠው ውሳኔ ለመሻር ወይም ለማረም ሥልጣን ይሰጠዋል ወይ? የሚለው መመልከት ተገቢ ይሆናል።
አንድ ፍ/ቤት የመጨረሻ ውሳኔ ከሰጠ ውሳኔው የሚታረመው የይግባኝ ቅሬታ በማቅረብ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 320/1/ እና 348/1/ አገናዝቦ በማንበብ መረዲት ይቻላል። በእርግጥ በተሰጠ ፍርድ ላይ ይግባኝ ማለት የሚቻል ቢሆንም ውሳኔውን የሰጠው ፍ/ቤት በሕግ በተሰጠው ስልጣን መሰረት ፍርደን ለማረም ወይም ለማሻሻል ወይም እንደገና ለማጣራት የሚችል ከሆነ ይግባኝ ማቅረብ የሚቻለው የኸው ስርዓት ከተፈፀመ በኋላ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 320/2/ ያመለክታል። ውሳኔ የሰጠው ፍ/ቤትም የሰጠውን ፍርድ በድጋሚ አይቶ ፍርደን የሚያርምበት የተለያዩ ሥርአቶች በስነ-ሥርዓት ሕጉ ውስጥ ተካተዋል። ለምሳላ በክርክሩ ውስጥ ከሥነ-ሥርአት ውጪ የሆነው ጉዲይ ሲኖር በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 209 መሰረት አቤቱታ ሲቀርብ ወይም ደግሞ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 6 መሰረት ዲኝነት እንደገና እንዱታይ አቤቱታ ሲቀርብ ውሳኔ የሰጠው ፍ/ቤት ጉዲዩን በድጋሚ ማየት ይችላል። በተያዘው ጉዲይ ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት የሰጠውን ትእዛዝ በድጋሚ አይቶ የለወጠው ከፍ ሲል እንዲየነው ተጠሪ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 208 የስር ፍ/ቤት የሰጠውን ማስተካከያ መሰረት በማድረግ ነው። ይህ ድንጋጌ በተሰጠው ፍርድ፣ውሳኔ ወይም ትእዛዝ ላይ የቁጥር አፃፃፍ ጉድለት ወይም ያልታሰበና ባለማስተዋል የተዘለለ ድንገተኛ ቃል ስህተት መኖሩን ሲረጋገጥ ስህተቱ የሚታረምበትን ስርአት የዘረጋ ድንጋጌ ነው። በድንጋጌውም እንዱታረም የተፈቀደው የውሳኔውን ይዘት ሉቀይሩ የማይችለ መሰረታዊ ያልሆኑ የጽህፈት ወይም የቁጥር ስህተቶች ወይም ግድፈቶች ብቻ ናቸው። ስለሆነም ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት የካርታ ቁጥሩ መስተካከል ውሳኔውን ሉያስቀይር የሚችል ነው በማለት መዝገቡን ለማንቀሳቀስ የሚችልበት የስነ-ሥርዓት ሕግ የለም። በመሰረቱ በስር ፍ/ቤት የተጠሪ ክስ ውድቅ የተደረገው ተጠሪ በቤቱ ላይ መብት እዲንለኝ ያስረዲልኛል ያለት የቤት ካርታ በስር ፍ/ቤት ቀርቦ ታይቶ ነው። ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤትም በመጀመሪያ ይግባኙን ውድቅ ሲያደርግም ይህንኑ ሰነድ ተመልክቶ ነው። የካርታው ቁጥር በመሳሳቱ በውሳኔው ላይ ያስከተለው አለታዊ ውጤት ስለመኖሩም በተጠሪም በኩል ሆነ በድጋሚ ጉዲዩን ባየው የይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት የሰጠውን መጨረሻ ውሳኔ በድጋሚ አይቶ እንዱያርመው ስልጣን የሚሰጠው የሥነ-ሥርአት ሕግ የለም። በመሆኑም ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት የስር ፍ/ቤት የሰጠው የቁጥር ማስተካከያ ትእዛዝን ብቻ መሰረት በማድረግ የሰጠውን ውሳኔ በድጋሚ አይቶ መሻሩ መሰረታዊ የሥነ-ሥርአት ስህተት ነው።
No topics extracted.
የድሬዲዋ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 00248/2001 መጋቢት 1 ቀን 2001 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ ተሽሯል።
የድሬዲዋ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት ቀደም ሲል ውድቅ ያደረገውን የይግባኝ ቅሬታ ያለህጋዊ ምክንያት በድጋሚ አይቶ ውሳኔውን መሻሩ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ነው ብለናል።
ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።
የዚህ ውሳኔ ግልባጭ ከመ/ቁ. 45172 ጋር ይያዝ።