No summary available.
መጋቢት 20 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ኂሩት መለሰ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን - የቀረበ የለም ተጠሪ፡- ጌታይዲ ኃ/የተ/የግል ማህበር - የቀረበ የለም **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ ያላግባብ የተከፈለ ቀረጥ ይመለስልኝ ጥያቄን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ ተጠሪ በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ባሁኑ አመልካች ላይ መጋቢት 07 ቀን 1998 ዓ.ም በመሰረተው ክስ መነሻ ነው።
የክሱ ይዘትም፡- ተጠሪ ድርጅት ሄርታለን ከሚባል የኔዘርላንድ ድርጅት የፈሳሽ መከላከያና ተዛማጅ እቃዎችን በአምራቹ የመሸጫ ዋጋ መሰረት የጉምሩክ ቀረጥን እየከፈለ ሲያስገባ መቆየቱንና በሦስት የተለያዩ ጊዜያት ከከፈላቸው ክፍያዎች ውስጥ ድምሩ ብር 60,858.82(ስልሳ ሺህ ስምንት መቶ ሃምሳ ስምንት ብር ከሰማንያ ሁለት ሳንቲም) የሆነውን ገንዘብ ያላግባብ አመልካች ማስከፈለንና ይኸው ያላግባብ የተከፈለው ገንዘብ እንዱመለስለት ተጠሪ ጥያቄ ቢያቀርብም አመልካች ፈቃደኛ አለመሆኑን በመዘርዘር ክሱ የተመሰረተበትን ገንዘብ ያለአግባብ ከተከፈለበት ጊዜ ጀምሮ ከሚታሰብ ወለድና ከክሱ ወጪና ኪሣራ ጋር አመልካች እንዱከፍል ይወሰንለት ዘንድ ዲኝነት መጠየቁን የሚያሳይ ነው። አመልካችም ለክሱ በሰጠው መልስ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ እና የፍሬ ነገር ክርክር ነጥቦችን በማንሳት ተከራክሯል። ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ክርክር በመስማት የአመልካችን ምስክሮች መስማት አስፈላጊ አለመሆኑን ገልፆ ጉዲዩን በመመርመር የአመልካችን ክርክር ውድቅ አድርጏ ለክሱም ኃላፉ በማድረግ ክሱ የተመሰረተበትን ገንዘብ ክሱ ከተመሰረበት ጊዜ ጀምሮ ከሚታሰብ ሕጋዊ ወለድ 9%(ዘጠኝ በመቶ) ጋር አመልካች ለተጠሪ እንዱከፍል ሲል ወስኗል። በዚህ ውሳኔ አመልካች ባለመስማማት ይግባኙን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርቦ ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በኋላ የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ ሙለ በሙለ ፀንቷል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ ለማስቀየር ነው።
የአመልካች ነገረ ፈጅ የካቲት 20 ቀን 2001 ዓ.ም በፃፈት ሁለት ገጽ የሰበር አቤቱታ በበታች ፍርድ ቤቶች ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል የሚለበትን ምክንያት ዘርዝረው አቅርበዋል። ይዘቱም ባጭሩ፡- የስር ፍርድ ቤት ይርጋን በተመለከተ የቀረበውን መቃወሚያ ማለፈም ሆነ የአመልካችን ምስክሮችንም ሳይሰማ መቅረቱ ያለአግባብ ሆኖ የደረሰበት ድምዲሜም የአዋጅ ቁጥር 68/89 አንቀጽ 48/7/,/11/ እና መመሪያ ቁጥር 10/1996 ስር የተመለከቱትን ድንጋጌዎችን የሚፃርር በመሆኑ ሉሻር ይገባዋል በማለት መከራከሩን የሚያሳይ ነው። አቤቱታውም ተመርምሮም በሰበር ችልቱ ላታይ ይገባዋል በመባለ ተጠሪ በጠበቃቸው አማካኝነት ጥቅምት 12 ቀን 2002 ዓ.ም በተፃፈ ሁለት ገጽ ማመልከቻ የበታች ፍርድ ቤቶችን ውሳኔ አግባብነት ገልጸው ሉፀና ይገባል ሲለ ተከራክረዋል።
የአመልካች ነገረ ፈጅ በበኩላቸው ጥር 18 ቀን 2002 ዓ.ም በሰጡት የመልስ መልስ የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር ተራክረዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
እንደመረመረውም የዚህን ችልት ምላሽ የሚያስፈልገው አቢይ ነጥብ የአመልካች ምስክሮች ሳይሰሙ ውሳኔ መሰጠቱ ባግባቡ ነው ወይስ አይደለም? የሚለው ሆኖ አግኝቶታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው ተጠሪ ክሱን ሉመሰርቱ የቻለት ያላግባብ የከፈልኩት የቀረጥ ገንዘብ ሉመለስልኝ ይገባል በሚል ሲሆን፤ አመልካች በበኩለ ክፍያውን ያስፈጸመው በሕጉ በተሰጠው ስልጣን መሰረት የዋጋ መረጃን በማየት መሆኑን ገልፆ ያላግባብ የተከፈለ የቀረጥ ገንዘብ የላለ መሆኑን ጠቅሶ ተከራክሯል። የስር ፍርድ ቤት የአመልካችን የዋጋ መረጃ ለጉዲዩ አግባብነት የላለው መሆኑን፣ጉዲዩን ለማስረዲት የተቆጠሩት ምስክሮችንም መስማቱ አስፈላጊ አለመሆኑን ገልፆ አመልካች በተጨማሪነት የወሰደውን የቀረጥ ገንዘብ ባግባቡ የወሰደ መሆኑን፣አላስረዲም በሚል ምክንያት ክርክሩን ውድቅ ማድረጉን ነው።
የጉምሩክ ባሥልጣንን እንደገና ለማቋቋም እና አሰራሩን ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 60/89 አንቀጽ 47 ላይ እንደተመለከተው ወደ ሐገር ውስጥ ለሚገባ ማናቸውም እቃ የጉምሩክ ቀረጥ ማስከፈያ ዋጋ የሚሆነው በትክክል ለእቃው የተደረገ ጠቅላላ ወጪ ነው። እቃው የተገዛበት ዋጋ ደግሞ ከወጪዎች አንደ ነው ስለሆነው ለቀረጥ ማስከፈያ መሰረት የሚሆነው ትክክለኛ የእቃው ዋጋ ስለመሆኑ ሕጉ በዋናነት ያስቀመጠው አስራር ነው። ከዚሁ የሕጉ መንፈስ መረዲት የሚቻለው ላላው ቁም ነገር ደግሞ በአስመጪው የሚቀርበው የእቃው ግምት ትክክለኛውን የእቃውን ዋጋ የማይናገር መሆኑ ከተረጋገጠ የቀረጥ ሂሳብን ለማስላት መነሻ(መሰረት) ላሆን የማይችል መሆኑን ነው። በመሰረቱ ወደ አገር ውስጥ የሚገባ እቃ ቀረጥ ማስከፈያ ዋጋ ምን ያህል እንደሆነና እንዳት እንደሚሰራ በአዋጅ ቁጥር 60/1989 አንቀጽ 48 ስር ተዘርዝሯል። የተጠቀሰው የአዋጅ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ 7 እና 8 ድንጋጌዎች ሲታዩም የጉምሩክ ባለሥልጣን ባስመጪው የቀረበለትን የዋጋ ግምት አልቀበልም በማለት የቀረጥ ሂሳቡን ለማስላት ላልች አማራጭ መንገድችን መከተል የሚችል ስለመሆኑ ያስገነዝባለ። የተጠቀሰው የአዋጅ አንቀጽ ንኡስ ቁጥር 6 ድንጋጌ ደግሞ፤የጉምሩክ ባለስልጣን በአስመጪዎች የቀረበለትን የዋጋ ግምት አልቀበልም ስለሚልበት ሁኔታ የገቢዎች ቦርድ መመሪያ ማውጣት የሚችል መሆኑን ደንግጓል። በዚሁ ሕግ በተሰጠው ስልጣን መሰረትም የተጠቀሰው አካል መመሪያውን ማውጣቱ የተረጋገጠ ሲሆን በዚህ መመሪያ መሰረትም በትራንዛክሽን ዋጋ ላይ የተመሰረተ የጉምሩክ ዋጋ አተማመን ተግባራዊ የማይሆንባቸው ምክንያቶች ተቀምጠዋል። ከነዚህም ምክንያቶች መካከል ወደ ሐገር ውስጥ የገባው እቃ ዋጋ ከአንድ ዓይነት እና ከተመሳሳይ እቃዎች ዋጋ በጉምሩክ ከተፈቀደው ልዩነት በላይ እንሶ መገኘት ስለመሆኑ መመሪያው በአንቀጽ 1/5/ ስር አስቀምጧል። ወደ ሃገር በገባ ወይም ከሐገር በወጣ እቃ ላይ የተከፈለው ቀረጥ በማናቸውም ምክንያት ሉከፈል ከሚገባው ቀረጥ ያነሰ መሆኑ በምርመራ የተደረሰበት እንደሆነ ደግሞ ባለሥልጣኑ የእቃውን ባለቤት ወይም ወኪለን በልዩነት ያልተከፈለውን ቀረጥ ማስከፈል እንደሚችል በአንቀጽ 57/1/ ስር በግልጽ አስፍሯል። በልላ በኩል በብልጫ የተከፈለ የቀረጥ ገንዘብ ለከፊዩ ሉመለስ እንደሚገባ አዋጁ በአንቀጽ 55 ስር በግልጽ ደንግጓል። በተያዘው ጉዲይ አመልካች ቀረጡን አስከፈልኩ የሚለው በመመሪያ ቁጥር 10/1996 መሰረት ስለመሆኑ፣በዚህ መመሪያ መሰረት የተፈፀመ ስለመሆኑ ደግሞ የሚያስረደት ምስክሮች ያለት ስለመሆኑ በስር ፍርድ ቤት በማስረጃነት ዘርዝሮ አቅርቦ ፍርድ ቤቱ አመልካች የቆጠራቸውን ምስክሮች መስማት አስፈላጊ አይደለም ብል ከአለፈ በኋላ አመልካች ክርክሩን በማስረጃ አላስረዲም በማለት ለክሱ ኃላፉ አድርጏታል። በአርግጥ በተከራካሪ ወገን የተቆጠረውን ምስክር ሁለ ፍርድ ቤቱ እንዱሰማ የማይገደድ ስለመሆኑ በፍትሐብሕር ስነ-ስርአት ሕጉ ስለማስረጃ አቅራረብ እና አቀባበል የተደነገጉት ድንጋጌዎች ይዘት የሚያስገነዝበን ነጥብ ሲሆን ፍርድ ቤቱ ይህንኑ ስልጣኑን መተግበር ያለበት በዘፈቀደ ላሆን አይገባም። በመሆኑም በተከራካሪ ወገን የተቆጠሩት ምስክሮች ሳይሰሙ የሚቀሩት ለጉዲዩ የሚሰጡት ምስክርነት አግባብነት የላለው መሆኑ ሲረጋገጥ ብቻ ነው።
በተያዘው ጉዲይ የአመልካች ምስክሮች ሉያስረደ ይገባል የተባለው አመልካች በሕጉ የተሰጠውን ስልጣን ባግባቡ በመጠቀም የተጠሪን ጥያቄ ያልተቀበለው ስለመሆኑ እና በመመሪያ ቁጥር 10/1996 መሰረት ብልጫ ቀረጥ የተባለው አለመከፈለን ነው። እንዱህ ከሆነ በምስክሮች የሚሰጠው ቃል ለጉዲዩ አግባብነት የላለው ነው ለማለት የሚያስችል አለመሆኑን ይህ ችልት ተገንዝቧል። ለጉዲዩ አግባብነት ያለው ማስረጃ ሳይሰማ ደግሞ ማስረጃውን የቆጠረው ተከራካሪ ክርክሩን በማስጃ አላስደገፈም ልባል አይችልም። በመሆኑም የስር ፍርድ ቤት ጉዲዩን የመራው አዋጅ ቁጥር 60/89 አንቀጽ 48 እና መመሪያ ቁጥር 10/1996 እንዱሁም በፍትሐብሕር ስነ ስርአት ሕጉ ስለማስረጃ አቀራረብና አቀባበል የተደነገጉትን ድንጋጌዎች ባገናዘበ መልኩ ባለመሆኑ የፍርድ አካሄደ የተሟላ ነበር ለማለት አልተቻለም። የፍርድ አካሄድ ሳይሟላ የተሰጠ ፍርድ ደግሞ የሕግ ሥርአቱን ያልጠበቀ በመሆኑ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ነው። ስለሆነም የበታች ፍርድ ቤቶች በጉዲዩ ላይ የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት በመሆኑ ተከታዩን ወስነናል።
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ቁ. 66236 ሐምል 23 ቀን 1999 ዓ.ም ተሰጠቶ በፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ. 59649 ጥር 28 ቀን 2001 ዓ.ም የፀናው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
አመልካች ቀረጡን ያስከፈለበትን ሁኔታ ለማስረዲት የቆጠራቸው ምስክሮች ተሰምተው እና ላላም ተገቢ ነው የተባለ ሁለ ተፈጽሞ በጉዲዩ ላይ እንደገና ውሳኔ ላሰጥበት የሚገባው በመሆኑ የፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የአመልካችን ምስክሮችን በመስማት ጉዲዩን እንደገና አይቶ ይወስን በማለት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.
343/1/ መሰረት መልሰንለታል። ይፃፍ።
No topics extracted.