No summary available.
መጋቢት 8 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሃይ ታደሰ ሂሩት መለሰ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- አቶ ፈንታ ምህረቱ - ወኪል አልማዝ ፈንታ ቀረቡ ተጠሪ፡- የኢትዮጵያ ንግድ ባንከ - አልቀረበም
አመልካች በም/ጎጃም ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ባቀረቡት ክስ አመልካች ሁለት ቤቶች በመያዣ አስይዘው ገንዘቡን ባለመክፈላቸው ተጠሪ ቤቶቹን ለመሸጥ ማስታወቂያ አውጥቶ ገዢ ባለመቅረቡ ቢበዛ በ3 ወር ውስጥ ሁለተኛ ጨረታ ማውጣት ሲገባው ከሶስት አመት በኋላ በማውጣቱና አንደኛው ቤት ላይ ከህግ ውጪ ለሶስተኛ ጊዜ ጨረታ አዘግይቶ በማውጣቱ ወለደ ጨምሮ አመልካች ላይ ጉዲት ስለደረሰ ተጠሪ ብር 152,222.40(አንድ መቶ ሃምሣ ሁለት ሺህ ሁለት መቶ ሃያሁለት ብር ከአርባ ሣንቲም) እንዱከፈላቸው ጠይቀዋል።
ተጠሪ ለክሱ በሰጠው መልስ ቤቶቹን ለመሸጥ የመጀመሪያው ጨረታ ሲወጣ ገዢ በመጥፊቱ ሁለተኛ ጨረታ የወጣ ሲሆን ቁጥር 276 ለሆነው ቤት ገዢ ባለመቅረቡ ባንኩ ቤቱን የተረከበው ሲሆን ቁጥር 247 ለሆነው ቤት የቀረቡት ተጫራቾች ግን ከቤቱ ግምት በጣም የወረደ ዋጋ በመጥራታቸው ጨረታው ሰዓት ከመድረሱ በፉት ስለተሰረዘ ሁለተኛ ጨረታ እንደወጣ ሉቆጠር አይችልም፣ ድጋሚ ጨረታ ለማውጣት የዘገየው ቤቱን ለመሸጥ ገበያ ሲፈላለግ ነው፣ በሶስት ወር ውስጥ ጨረታ እንድናወጣ የሚያስገድድ ህግ የለም፣ ይርጋ እስካላገደን ጨረታ ማድረግ እንችላለን፣ ወለድ ልከፍል አይገባም የሚለው ተገቢነት የላለው ክርክር ነው፣ አመልካች ቤቱን እንዱለቁ ቢነገራቸውም እስከ መስከረም 25 ቀን 1997 ዓ.ም ድረስ ይጠቀሙበት ነበር በማለት ክሱ ውድቅ እንዱሆን አመልክቷል።
ፍ/ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ መርምሮ ተጠሪ ጨረታውን ሲያካሂድ አላግባብ አዘግይቷል፣ በሁለተኛ ጨረታ ቤቱ ካልተሸጠ መረከብ ነበረበት፣ ተጠሪ በጨረታው መነሻ ግምት ተረክቦ ዕዲውን የሚቃለልበት መንገድ መፈለግ ነበረበት፣ ሶስተኛ ጨረታ መደረጉ ህጉን የተከተለ አይደለም፣ ሁለተኛ ጨረታ እጅግ ቢዘገይ በሶስት ወር ውስጥ መደረግ ነበረበት፣ ጨረታው ከሶስት አመት በላይ ዘግይቶ በመደረጉ በወለድ ምክንያት ከፍ ላለው ዕዲ ኃላፉ ነው በማለት ተጠሪ ብር 112,738.80(አንድ መቶ አስራ ሁለት ሺህ ሰባት መቶ ሰላሳ ስምንት ብር ከሰማንያ ሣንቲም) እንዱከፍል ወስኗል።
በዚህ ውሳኔ ላይ ተጠሪ ለአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ አቅርቦ ፍ/ቤቱ ሁለቱን ወገኖች አቅርቦ ካከራከረ በኋላ ከብድሩም ሆነ ከመያዣ ውለና እነዚህን ከሚመለከቱ ህጎች አኳያ አመልካች ብድሩን ሳይመልሱ ቢቀሩ ንብረቶቹ በአፊጣኝ እንዱሸጡ ለማስገደድ ወይም ቢዘገይ ጉዲት ካሳ ለመጠየቅ የሚያስችል መብት የላቸውም፣ አዋጁ ጨረታ የሚወጣበትን ጊዜና ቢዘገይ ወለድ መታሰብ እንዱቆም ብል አልደነገገም፣ ቤቱም እስከ መስከረም 25 ቀን 1997 ዓ.ም አመልካች እጅ ስለነበር መያዣው ባለመሸጡ ወይም ባንኩ ባለመረከቡ አመልካች ላይ የደረሰ ጉዲት የለም፣ ለወለደ መጨመር ብቸኛ ምክንያት አመልካች ብድሩን አለመክፈላቸው ነው፣ ስለሆነም ባንኩ ሃላፉ የሚሆንበት የህግ አግባብ የለም በማለት የስር ፍ/ቤትን ውሳኔ ሽሯል።
በዚህ ውሳኔ ላይ አመልካች ለአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የሰበር አቤቱታ ያቀረቡ ቢሆን ችልቱ የጠቅላይ ፍ/ቤቱ ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የለውም በማለት አቤቱታው ውድቅ አድርጎታል።
የአሁኑ ሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሳኔ ላይ ነው። የአመልካች አቤቱታ በአጭሩ፤ በአዋጅ ቁጥር 97/90 ተጠሪ አመልካችን ወክል መያዣውን ሲሸጥ በፍ/ብ/ህ/ቁ. 2211 የተቀመጠውን የወኪልነት ስነ-ምግባር በመከተል ባለእዲው እዲ እንዲይበዛበት ተግቶ መስራት ይገባዋል፣ በአዋጁ አንቀፅ 6 እንደተመለከተው ሉከተል የሚገባውን የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 394(2) እና 428(2) ወደጎን በመተው ለዕዲው ተመጣጣኝ በሆነ ቤት ላይ ብቻ ጨረታ ማውጣት ሲገባው በሁለቱም ቤቶች ላይ ጨረታ ማውጣቱ፣ በሁለተኛ ጨረታ ካልተሸጡ ከእዲው ጋር ተመጣጣኝ የሆነውን ቤት በመረከብ እዲውን ዘግቶ አንደን ቤት ነፃ ላሆን ሲገባ እንዱዘገይ በማድረግ ወለደ እንዱቆለል ማድረጉ ተረጋግጦ እያለ የጠቅላይ ፍ/ቤትና ሰበር ሰሚ ችልቱ የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት አለበት የሚል ነው።
ይህ ችልትም የመያዣ ንብረቶቹን ከረጅም ጊዜ ቆይታ በኋላ ተጠሪ እንዱረከብ ሲደረግ የተከማቸው ወለድ መታሰቡና አመልካች ያቀረቡት የጉዲት ካሳ ጥያቄ ውድቅ መደረጉን አግባብነት ካላቸው የህግ ድንጋጌዎች አኳያ ለመመርመር አቤቱታው ለሰበር ችልት ያስቀርባል ብሎል። ተጠሪም ህዲር 24 ቀን 2002 ዓ.ም የተፃፈ መልስ ክርክሩን አቅርቧል። ችልቱም መዝገቡን መርምሯል።
በተያዘው ጉዲይ አከራካሪ ሆኖ የተገኘው አበዲሪ ባንኮች ለዕዲው በመያዣ የያዙትን ንብረቶች ሉሸጡ የሚገባበት የጊዜ ገደብ አለ? ወይስ የለም? አለ ከተባለ በጊዜ ገደቡ ውስጥ ንብረቶቹ ባለመሸጣቸው ኃላፉ ሉሆኑ ይገባል? አይገባም?
የሚለው ነው።
ለባንክ በመያዣ የተሰጡ ንብረቶችን በተመለከተ በወጣው አዋጅ ቁጥር 97/90 አንቀፅ 3 መሰረት የማንቀሳቀስ ንብረት በዋስትና የያዘ ባለገንዘብ ባንክ ዕዲው ካልተከፈለው ከሰላሳ ቀናት ያላነሰ ማስታወቂያ ለባለዕዲው በመስጠት ንብረቱን በሃራጅ መሸጥ ይችላል። በተጨማሪ የመጀመሪያ ጨረታ አውጥቶ ገዢ ካልተገኘ ሁለተኛ ጨረታ እንደሚወጣና በሁለተኛው ጨረታ ገዢ ከጠፊ ንብረቱን እንደሚረከብ ያመለክታል። ይህን አዋጅ ለማሻሻል የወጣው አዋጅ ቁጥር 216/92 አንቀፅ 2 ባንኩ ንብረቱን የሚረከበው በመጀመሪያው ጨረታ መነሻ ዋጋ ስለመሆኑ ይናገራል። ከዚህ በቀር ንብረቱ መሸጥ ያለበት መቼ እንደሆነ ወይም ሁለተኛ ጨረታ በስንት ጊዜ ውስጥ መውጣት እንደሚገባ የጊዜ ገደብ ወስኖ አላስቀመጠም።
በልላ በኩል ባንኩ የሃራጅ ሽያጩን ሲያከናውን አግባብነት ያላቸውን ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 394-449 ያለትን ድንጋጌዎች በመከተል መሆኑ በአዋጁ አንቀፅ 6 ስር ተመልክቷል። በመሆኑም የማይንቀሳቀስ ንብረት የሚሸጥበት ሁኔታና ጊዜ የሚመለከቱትን የሥነ-ሥርዓትቱን ድንጋጌዎች መመርመር ተገቢ ይሆናል። ፍርድን ለማስፈፀም የማይንቀሳቀስ ንብረት በሃራጅ ሲሸጥ በቅድሚያ ማስታወቂያ መውጣት እንዲለበት ንብረቱም ሉሸጥ የሚችለው ማስታወቂያ ከወጣ ጀምሮ ለሰላሳ ቀን ቆይቶ መሆኑን የሥነ-ሥርዓት ህጉ አንቀፅ 423(1) እና 426 ተጣምረው ሲነበቡ የሚያስገነዝቡት ጉዲይ ነው። በመጀመሪያ ጨረታ ገዢ ካልቀረበ ባለገንዘቡ ንብረቱን እንደሚረከብ ይናገራል። ከዚህ ውጪ ጨረታዎቹ የሚወጡበት የጊዜ ገደብ የሥነ-ሥርዓት ህጉ ወስኖ አላስቀመጠም። በመሆኑም ባንኩ መብቱን ለመጠየቅ የሚችልበት የጊዜ ገደብ በይርጋ ቀሪ እስከሚሆንበት ድረስ በመብቱ መጠቀም ይችላል። አበዲሪውን ባንክ በአዋጅ ቁጥር 97/90 መሰረት ካሳ መጠየቅ የሚቻለው ደግሞ ባንክ ሽያጩን ሲያከናውን አግባብነት ያለውን ሥነ-ሥርዓት ድንጋጌዎች ባለመከተለ ጉዲት አድርሶ ከሆነ ነው (የአዋጁን አንቀፅ 7 ይመለከቷል)። በተያዘው ጉዲይ ግን ባንኩ ፈፀመ ልባል የሚችለው የሥነ-ሥርዓት ህግ ጥሰት አለ ማለት አልተቻለም።
ከዚህ በተጨማሪ በተያዘው ጉዲይ ባንኩ ጨረታውን በሚከናውንበት ጊዜ ሁለ አመልካች ቤቱን ይዘው ይገለገለበት እንደነበር ያልካደት ጉዲይ ነው። በመሆኑም በአንድ በኩል አመልካች ቤቱን ይዘው እየተጠቀሙበት በልላ በኩል ቤቱ ዘግይቶ ስለተሸጠ ጉዲት ደርሷል በማለት ያቀረቡት ክርክር ተቀባይነት የለውም። ምናልባት ባንኩ ጨረታ ሲያወጣ ቤቱን ከአመልካች ተረክቦ በራሱ ይዞታ ስር አድርጎ ቢሆን ሁኔታው የተለየ ላሆን ይችል ነበር። አመልካች ቤቱን ይዘው በማከራየት ሆነ በልላ መንገድ በመጠቀም እዲውን ሉያቀለ የሚችለበት ሁኔታ ስለሚኖር ባንኩ ቤቱን በቁጥጥሩ ስር አድርጎ እንደገና ጨረታውን ሳያወጣ ቢያዘገይ በአመልካቹ ላይ ጉዲት ሉያስከትል የሚችልበት አጋጣሚ ይኖራል። በተያዘው ጉዲይ ግን ባንኩ ቤቱን እስከተረከበበት ጊዜ ድረስ በአመልካች ይዞታ ስር ስለነበር ጨረታ ዘግይቶ በመውጣቱ አመልካች ላይ ጉዲት አድርሷል ልባል አይችልም። በአጠቃላይ የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤትና የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት አመልካችን ካሳ ሉጠይቁ አይችለም በማለት የደረሱበት መደምደሚያ የህግ ስህተት የለውም። በመሆኑም ተከታዩ ውሳኔ ተሰጥቷል።
የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ/ ጥቅምት 4 ቀን 2001 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ እና የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ ጥር 27 ቀን 2001 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ ፀንቷል።
ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።
No topics extracted.