No summary available.
መጋቢት 07 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ኂሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ አመልካች፡- ክፍለ መሒሪ - ወኪል ተ/ገብራይ መሒሪ ቀረቡ ተጠሪ፡- በላይ ከመላ - ቀረቡ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ የቤት ክርክር ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በኦሮሚያ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት በወልመራ ወረዲ ፍርድ ቤት ነው። ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ አመልካች ግንቦት 24 ቀን 1996 ዓ.ም በመሰረቱት ክስ ነው። የክሱ ይዘትም ባጭሩ፡- አቶ ቄሬንሳ ፋይሳ የግል ቤትና ይዞታቸው የሆነውን ከባለቤታቸው ከወ/ሮ ደስታ ኩምሳ ጋር በመሆን ሐምል 21 ቀን 1984 ዓ.ም በተፃፈ ውል ለአመልካች አባት ለአቶ መሒሪ ገ/እየሱስ ሸጠውላቸው ቤቱን ያስረከቧቸው ሲሆን፤
በእጃቸው ያለውን ቤት በስማቸው እንዱዛወር ይወሰንላቸው ዘንድ ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ሲሆን፤ ጉዲዩ የቀረበለት ፍርድ ቤትም ተቃዋሚ ካለ እንዱቀርብ በጋዜጣ ጥሪ አድርጏ ባለመቅረቡ የአቤቱታ አቅራቢውን ማስረጃ አጣርቶ ቤቱ በስማቸው እንዱዛወር ሰኔ 08 ቀን 1985 ዓ.ም በዋለው ችልት ውሳኔ ሰጥቷል። ከዚህም በኋላ የአሁኑ ተጠሪ ውሳኔውን የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 358 መሰረት በመቃወም አቤቱታቸው ውሳኔውን ለሰጠው ፍርድ ቤት አቅርበው ፍርድ ቤትም አቤቱታውን ተቀብል ግራ ቀኙን ካከራከረ በኋላ ቀድሞ የሰጠውን ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 360(2) መሰረት በመሰረዝ ገዥ ሻጭን የመጠየቅ መብት አለው በማለት ወስኗል።፡ ከዚህም በኋላ የአሁኑ አመልካች ቅር በመሰኘት ይግባኛቸውን ለምእራብ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበው ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በኋላ ለክርክሩ ምክንያት የሆነውን ቤት የሚገኘው ከወልመራ ወረዲ ግዛት ክልል ወጪ ሆኖ እያለ ፍርድ ቤቱ የውል ይፈፀምልኝ ጥያቄን ከመጀመሪያውኑም ቢሆን ተቀብል ማስተናገደ ያለስልጣኑ በመሆኑ ስህተት ነው የሚለውን ምክንያት በመያዝ የስር ፍርድ ቤትን ውሳኔ ሽሮታል። ከዚያም የአሁኑ ተጠሪ ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኛቸውን አቅርበው ተቀባይነት አላገኙም። ከዚህም በኋላ ተጠሪ የሰበር አቤቱታቸውን ለኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት አቅርበው ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በኋላ ይኸው ፍርድ ቤት በዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት ተሰጠቶ በክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት የፀናውን ውሳኔ በመሻር የወረዲውን ፍርድ ቤት ጉዲዩን ለማየት ስልጣን ነበረው በማለት ወስኗል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ ለማስቀየር ነው።
አመልካች መጋቢት 15 ቀን 2001 ዓ.ም በፃፈት ሦስት ገጽ የሰበር አቤቱታ በጉዲዩ ላይ በተሰጠው ውሳኔ ላይ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል የሚለበትን ምክንያት ዘርዝረው አቅርበዋል። አቤቱታቸው ተመርምሮም የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ጉዲዩን ለማየት የወረዲው ፍርድ ቤት ስልጣን አለው ብል የዞኑ ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ ከሻረ በኋላ ጉዲዩ ወደ ዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት ተመልሶ እንዱታይ ሳያደርግ መቅረቱ በአግባቡ መሆን ያለመሆኑን ለመመረመር ሲባል ጉዲዩ ለሰበር ችልቱ እንዱቀርብ ተደርጏአል። በዚህም መሰረት ተጠሪ ታሕሣሥ 06 ቀን 2002 ዓ.ም በተፃፈ ሁለት ገጽ ማመልከቻ የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት ጉዲዩ ላይ የሰጠው ውሳኔ የተፊጠነ ፍትሕ ከማግኘት መብት አኳያ ተገቢ ነው በማለት ውሳኔ ሉጸና ይገባል ሲለ ተከራክረዋል። አመልካች በበኩላቸው የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር የመልስ መልሳቸውን ሰጥተዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መሰረት ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩ ለሰበር ችልት ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ አንፃር በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው ጉዲዩ በመጀመሪያ ደረጃ ይግባኝ የቀረበለት የምእራብ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የወረዲው ፍርድ ቤት ጉዲዩን የተመለከተው ከሥልጣኑ ውጪ ነው በማለት ፍሬ ጉዲዩን ሳይመረምር ውሳኔውን መሻሩን፣የክልለ ሰበር በበኩለ የወረዲው ፍርድ ቤት ጉዲዩን ለማየት ስልጣን አለው በሚል ምክንያት የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ ሲሽር በፍሬ ጉዲዩ ላይ የዞኑ ፍርድ ቤት እንደገና አከራክሮ እንዱወስን ሳያደርግ መቅረቱን፣ይኸው ፍርድ ቤት ዋናውን ጉዲይ ራሱ የመረመረ ስለመሆኑ በግልጽ ሳያስቀምጥ የወረዲው ፍርድ ቤት የወረዲው የፍሬ ጉዲዩ ላይ የሰጠውን ውሳኔ የማጽናት ውጤት ያለው ውሳኔ መስጠቱን ነው። የክልለ ሰበር ችልት የወረዲው ፍርድ ቤት በዋናው ጉዲይ ላይ የሰጠውን ውሳኔ የተቀበለበትን ምክንያት አለመግለፁ ወይም የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በዋናው ጉዲይ ላይ ተገቢውን ውሳኔ እንዱሰጥበት አለማድረጉ የአመልካችን የይግባኝ መብት ያጣበበ ነው። ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት በዋናው ጉዲይ ላይ የራሱን ውሳኔ ካላሳለፈና የበላይ ችልቱ የይግባኝ ሰሚውን ፍርድ ቤት ውሳኔ ካልተቀበለው በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 341፣342፣343 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎችን መሰረት በማድረግ ተገቢውን መወሰን አለበት።
No topics extracted.
በተያዘው ጉዲይ የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ስልጣንን መሰረት አድርጏ የሰጠውን ውሣኔ ከሻረ በኋላ የወረዲው ፍርድ ቤት በዋናው ጉዲይ ላይ የሰጠውን ውሳኔ ያለምክንያት ማጽናቱ የአመልካችን የይግባኝ መብት ያጣበበ እና ስነ-ስርአታዊ ያልሆነ ሆኖ አገኝተነዋል። በመሆኑም በጉዲዩ ላይ የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ስለአገኘነው ተከታዩን ወስነናል።
የኦሮሚያ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ቁ. 49541 ታህሣሥ 27 ቀን 2001 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
በዋናው ጉዲይ ላይ የምእራብ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት እንደገና በማየት ተገቢውን ይወስን ዘንድ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 341/1/ መሰረት መልሰንልታል። ይፃፍ።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሳራ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።