No summary available.
መጋቢት 7 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገጌ ጌታነህ መንበረፀሃይ ታደሰ ሂሩት መለሰ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ አመልካች፡- መብራቱ፣ ተ/ማርያም፣ ገ/ማርያም የሽርክና ማሕበር - የቀረበ የለም ተጠሪ፡- አቶ መብራቱ ዓንዲይ - የቀረበ የለም
ለሰበር አቤቱታ መነሻ የሆነው አመልካች ማህበር በተጠሪ ላይ ያቀረበው ክስ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 216(4) መሰረት ውድቅ በመደረጉ ነው። አመልካች ተጠሪ የማህበሩ ሉ/መንበር ሆነው በሚሰሩበት ወቅት በእጃቸው የገባውን የማህበሩን ቼክ ለግል መኪና መግዣ የከፈለት በመሆኑ ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) ገንዘቡ ከባንክ ከተወሰደበት ጊዜ ጀምሮ ከሚታሰብ ወለድ ጋር እንዱከፍለ ክስ አቅርቧል። ተጠሪም ክስ የቀረበበትን ገንዘብ አመልካች ቀደም ሲል አቅርቦ በነበረው ክስ አጠቃል ሉያቀርበው ሲገባ ላላ ክስ ማቅረቡ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 216 መሰረት ተገቢ አይደለም የሚል መቃወሚያና በፍሬ ጉዲይ ላይ ላልች ክርክሮች አቅርበዋል። ጉዲዩ የቀረበለት የመቀላ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤትም የተጠሪን መቃወሚያ ውድቅ በማድረግ ተጠሪ ገንዘቡን ውሳኔ ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ ከሚታሰብ ወለድ ጋር እንዱከፍለ ወስኗል። ተጠሪ በዚህ ውሳኔ ላይ ለትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ አቅርበው ፍ/ቤቱ የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ አመልካች ቀደም ሲል አቅርቦት የነበረው ክስና አሁን ያቀረበው ክስ ተጠሪ የማህበሩን ገንዘብ ለግል ጥቅም አውለዋል የሚል በመሆኑ ተጠቃለው ሉቀርቡ ሲገባ ለያይቶ ማቅረቡ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 216 መሰረት ህጋዊ አይደለም በማለት የከፍተኛ ፍ/ቤትን ውሳኔ በድምፅ ብልጫ ሽሮታል። በዚህ ውሳኔ ላይ አመልካች ለክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ አቅርበው ፍ/ቤቱ ክስ የቀረበበት ጉዲይ አመልካች ቀደም ሲል ካቀረበው ክስ ጋር ተጣምሮ መቅረብ የሚገባው በመሆኑ ተነጣጥል መቅረቡ ተገቢ አይደለም በማለት ተጠሪ ገንዘቡን ከወለድና ከላልች ወጪና ኪሳራ ጋራ እንዱከፍለ የተሰጠውን ውሳኔ መሻሩ ተገቢ ነው በማለት ጠቅላይ ፍ/ቤቱ የሰጠውን ውሳኔ ሲያፀናው ዲኝነትን አስመልክቶ የተሰጠውን ውሳኔ ብቻ በማሻሻል አመልካች ብር 1,675.00(አንድ መቶ ሺህ ስድስት መቶ ሰባ አምስት ብር) ብቻ እንዱከፍለ ወስኗል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንን ውሳኔ ለማስለወጥ ሲሆን አመልካች በአቤቱታው ተጠሪ ብር 100,000(መቶ ሺህ ብር) የያዘ ቼክ ለመኪናቸው መግዣ ያዋለት መሆኑ የተረጋገጠው የመጀመሪያው ክስ ከቀረበ በኋላ በመሆኑ አመልካች ሆነ ብል ቀንሶ ያስቀረው ባለመሆኑ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 216(3) መሰረት ክሱ ውድቅ የመደረጉን አግባብነት ለመመርመር አቤቱታው ለሰበር ያስቀርባል በማለቱ ግራ ቀኙ መልስና የመ/መልስ በሬጅስትራር ጽ/ቤት በኩል እንዱለዋወጡ የታዘዘ ቢሆን ተጠሪ መልስ ባለማቅረባቸው መልስ የመስጠት መብታቸውን አልፈን መዝገቡን መርምረናል።
አመልካች በስር ፍ/ቤት ክስ አቅርቦ የነበረው ከላይ እንደተመለከተው ተጠሪ የማህበሩ ሉ/መንበር ሆነው ሲሰሩ በእጃቸው የገባውን ቼክ ለራሳቸው ለገዙት መኪና መክፈያ አውለውታልና ገንዘቡን ከነወለደ ይመልሱ በሚል ነው።
ተጠሪም በመልሳቸው አመልካች ቀደም ሲል በተመሳሳይ ጉዲይ ክስ ሲመሰርት ይህንኑ ክስ አጠቃል ሉከስ ሲገባ ቀንሶ ባስቀረው ገንዘብ ላይ ድጋሚ ክስ እንዲይመሰርት የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 216 የከለክለዋል የሚል መቃወሚያ አቅርበዋል።
በመሆኑም የአመልካች ክስ በተጠቀሰው የሥነ-ሥርዓት ድንጋጌ ውድቅ ላደረግ ይገባል ወይ የሚለው ጭብጥ ፍ/ቤቱ መርምሯል። ለዚህ ይረዲ ዘንድ ድንጋጌውን መመልከቱ ተገቢ ነው። የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 216 በአጠቃላይ ስለ ክስ አቀራረብና አገላለፅ የሚመለከት ድንጋጌ ነው። በተለየ ከተያዘው ጉዲይ ጋር አግባብነት ያለው የድንጋጌው ንዐስ ቁጥር 2 እና 3 ነው። የንዐስ ቁጥር 2 የመጀመሪያው ዓረፍተ ነገር አንድ ከሳሽ ክስ ሲያቀርብ ለክሱ ምክንያት የሆኑትን ነገሮች በሙለ አጠቃል መቅረብ እንደሚገባ የሚናገር ሲሆን ንዐስ ቁጥር 3 ደግሞ አንድ ከሳሽ ሉከስበት ሲችል ሆነ ብል በመቀነስ ባስቀረው ሃብት ምክንያት እንደገና ላላ ክስ ለማቅረብ እንደማይፈቀድለት ይገልፃል። በመሆኑም ከሳሽ ክስ ሲያቀርብ ክሱን ለማቅረብ ምክንያት የሆኑት ነገሮች በሙለ አጠቃል ማቅረብ የሚጠበቅበት ሲሆን ማቅረብ ሲችል ሆነ ብል ቀንሶ ባስቀረው ሃብት ላይ ግን ድጋሚ ክስ ሉያቀርብ እንደማይችል ከድንጋጌዎቹ መረዲት ይቻላል።
ወደተያዘው ጉዲይ ስንመለስ ተጠሪ የማሕበሩ ሉ/መንበር ሆነው በሰሩበት ጊዜ ያለአግባብ ያባከኑትን የማሕበሩን ገንዘብ ብር 100,000(መቶ ሺህ ብር) እንዱከፍለ ክስ ቀርቦባቸዋል። በልላ በኩል ግን አመልካች እኚሁ ተጠሪ የማሕበሩ ሉ/መንበር ሆነው ሲሰሩ በስራቸው ምክንያት በእጃቸው ከገባው የማሕበሩ ገንዘብ ውስጥ ብር 689,306.49(ስድስት መቶ ሰማንያ ዘጠኝ ብር ሦስት መቶ ስድስት ብር ከአርባ ዘጠኝ ሣንቲም) ስላጎደለ ይህንን ገንዘብ እንዱከፍለ ሚያዚያ 24 ቀን 1997 ዓ.ም ክስ የመሰረተባቸው ስለመሆኑ ችልቱ ተገንዝቧል። በመሆኑም በሁለቱም ክስ ጥያቄ የቀረበው ተጠሪ የማሕበሩ ሉ/መንበር ሆነው ሲሰሩ ያጎደለትን ገንዘብ እንዱከፍለ ነው። ስለሆነም አመልካች በሁለተኛ ክስ የቀረበውን ጥያቄ በመጀመሪያው ክስ አጠቃል ሉያቀርበው የሚገባው ነበር። አመልካች በሰበር አቤቱታው ተጠሪው ብር 100,000(መቶ ሺህ ብር) ቼክ ለመኪናቸው መግዣ የከፈለ መሆኑ የታወቀው የኦዱት ሪፕርት ከተሰራና የመጀመሪያው ክስ ከቀረበ በኋላ በመሆኑ ሆነ ብል ገንዘቡን ቀንሶ ክስ መስርቷል ልባል አይችልም የሚል መከራከሪያ አቅርቧል።
No topics extracted.
በእርግጥ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 216(3) ድጋሚ ክስ እንዲይቀርብ የሚከለክለው ከሳሹ ሉከስ ሲችል ሆነ ብል በመቀነስ ባስቀረው ሃብት ላይ ነው። ይህ ሰበር ችልትም ለትክክለኛ ፍትሕ አሰጣጥ እንዱያስችለው አመልካች ቀደም ሲል ባቀረበው ክስ በተሰጠው ውሳኔ ላይ ተጠሪ ለፋ/ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ያስከፈቱት መዝገብ ን ተመልክቷል። በዚህ መዝገብ አመልካች የመጀመሪያውን ክስ ያቀረበው ሚያዚያ 24 ቀን 1997 ዓ.ም መሆኑን ተረድተናል። በልላ በኩል ደግሞ ተጠሪ ብር 100,000(መቶ ሺህ ብር) እንዱከፍለ ክስ የተመሰረተው የመጀመሪያው ክስ ከቀረበ 10 ቀን ሳይሞላው በ03/09/1997 ነው። በመሆኑም አመልካች ተጠሪ ተጨማሪ ብር 100,000(መቶ ሺህ ብር) ማጉደላቸው የተረጋገጠው የመጀመሪያው ክስ እንደቀረበና እንዲውም ተጠሪ ለመጀመሪያው ክስ መልስ ሳይሰጡ በመሆኑ አመልካች ክሱን በማሻሻል በዚህ መዝገብ ክስ ያቀረበበትን ጉዲይም አጠቃል ሉያቀርብ ይችል ነበር። ተጠሪ ላይ የሚፈለግ ተጨማሪ ጉድለት መኖሩን የመጀመሪያው ክስ እንደቀረበ ወዱያው ያወቀው በመሆኑ በመጀመሪያው ክስ አጠቃል ሉያቀርበው ሲገባ ሁለተኛ ክስ ማቅረቡ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 216(3) መሰረት የማይቻል በመሆኑ በዚህ ምክንያት ክሱ ውድቅ በመደረጉ ተፈፀመ ልባል የሚችል መሰረታዊ የህግ ስህተት የለም። በመሆኑም ተከታዩ ውሳኔ ተሰጥቷል።
የትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ የካቲት 18 ቀን 2000 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ ፀንቷል።
ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።