No summary available.
የካቲት 8 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሃይ ታደሰ ሐጏስ ወልደ ኂሩት መለሰ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ አመልካች፡- የገነተ-ጽጌ ቅ/ጊዮርጊስ ማህበር በኩር ሰንበቴ - ም/ሰብሣቢ ደሣለኝ ዱባባ ቀረቡ ተጠሪ፡-
ፍ/ቤቱም አመልካች ያቀረባቸውን መቃወሚያዎች ውድቅ በማድረግ ተጠሪዎቹ ጥፊት ለመፈፀማቸው በቂ ማስረጃ አልቀረበም በሚል እግደ ተነስቶ ከሙለ መብታቸው ጋር ወደ ማሕበሩ አባልነት እንዱመለሱ ወስኗል። በዚህ ውሳኔ ላይ አመልካች ለፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ አቅርቦ የነበረ ቢሆንም ፍ/ቤቱ ግራ ቀኙን አከራክሮ የስር ፍ/ቤትን ውሳኔ አጽንቷል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሳኔ ላይ ሲሆን አመልካች በቅሬታው በዋናነት ተጠሪዎች የታገደት በማሕበሩ የመጨረሻ የስልጣን አካል በመሆኑ ፍ/ቤቱ ጉዲዩን ለማየት ስልጣን የለውም፣ተጠሪዎችም የታገደት በጥፊታቸው በመሆኑ ውሳኔው ሉሻር ይገባል የሚል ክርክር አቅርቧል። ይህ ችልትም የአመልካች አቤቱታ ለሰበር ችልት ያስቀርባል በማለቱ ግራ ቀኙ ክርክራቸውን በፁሁፍ አቅርበዋል። ችልቱም መዝገቡን መርምሯል።
ተጠሪዎች በስር ፍ/ቤት ባቀረቡት ክስ አመልካች ከማህበሩ ያለአግባብ ያገዲቸው መሆኑን ጠቀሰው ይኸው ውሳኔ እንዱነሳላቸው ነው የጠየቁት። አመልካች ደግሞ በተጠሪዎችን ከማህበሩ ማገደን ሳይክድ እርምጃው ተገቢ ነው በማለት ነው የሚከራከረው። በመሆኑም በዚህ ጉዲይ በጭብጥነት ሉመለስ የሚገባው ተጠሪዎቹ ለ6 ወር ሉታገደ ይገባል አይገባም የሚለው ጉዲይ ነው። ከክርክሩ ሂደት እንደተገነዘብነውም ተጠሪዎች ጥፊት አጥፍተዋል በሚል ከማህበሩ የታገደት ከጥር 25 ቀን 2000 ዓ.ም ጀምሮ ነው። የታገደትም ለ6 ወራት ስለመሆኑ ተጠሪዎች በክሳቸውም የጠቀሱት ጉዲይ ነው። ይህ ጉዲይ በክርክር ላይ እያለ ግን ተጠሪዎቹ ከማህበሩ የታገደበት የጊዜ ገደብ አብቅቷል። ጊዜው ካበቃ ደግሞ እገዲው አግባብ ነው አይደለም የሚለው ነጥብ መወሰኑ ውጤት የሚኖረው አይሆንም። ምክንያቱም ለክሱ ምክንያት የሆነው ጉዲይ አብቅቷልና ነው። ክሱ በሚቀጥልበት በማንኛውም ጊዜ ለክሱ ምክንያት የሆነው ነገር መቋረጡን ወይም ጨርሶ መቅረቱን ፍ/ቤቱ በቂ በሆነ ማስረጃ የተገነዘበው ከሆነ ክሱን ሉዘጋው እንደሚችል በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.
280 ስር ተመልክቷል። ይህ ከሆነ ደግሞ የእገዲውን ግዜ በመጠናቀቁና የክሱም ምክንያት በዚሁ ስለተቋረጠ ክርክሩ ሉቀጥል የሚገባበት የሕግ ምክንያት አይኖርም። በመሆኑም ተጠሪዎች ሉታገደ ይገባል አይገባም የሚለውን ፍሬ ጉዲይ መወሰን ሳያስፈልግ መዝገቡን መዝጋቱ ተገቢ ሆኖ ተገኝቷል። ስለሆነም ተከታዩ ትእዛዝ ተሰጥቷል።
ት እ ዛ ዝ ለክሱ ምክንያት የሆነው ነገር ስለተቋረጠ መዝገቡ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 280 መሰረት ተዘግቷል።
መዝገቡ ለመዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.