No summary available.
የካቲት 22 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ መንበረፀሐይ ታደሰ ሐጏስ ወልደ ኂሩት መለሰ አልማው ወላ አመልካች፡- አቶ ታዬ ሆሳዕና - የቀረበ የለም ተጠሪ፡- ወ/ሮ መሰረት ወልደየስ - ቀረቡ
በዚህ መዝገብ የቀረበው ጉዲይ የባልና ሚስት ንብረት ክፍፍልን የሚመለከት ነው። አመልካች በፋ/መ/ደረጃ ፍ/ቤት ባቀረቡት አቤቱታ የጋራና የግል ንብረት ነው የሚሎቸውን ንብረቶች ዘርዝረው ለመካፈል ጠይቀዋል። በአቤቱታቸውም ከላልች ንብረቶች በተጨማሪ የመለዋወጫና የሕንፃ መሳሪያ ሱቅ ከእንቁላል ፊብሪካ ጉለላ ከነበረበት ወጥቶ ተጠሪ በ22 ማዞሪያ በከፈቱት ሱቅ ውስጥ ስለተቀመጠ ንብረቶቹን በአይነት ለመካፈል ጠይቀዋል።
ተጠሪ በበኩላቸው የመለዋዋጫና የሕንፃ መሣሪያው ሱቅ ከፍቺ በፉት ንግደ ተዘግቶ የንግድ ፈቃደ መመለሱን በመግለጽ መልስ ሰጥተዋል። ጉዲዩ የቀረበለት የፋ/መ/ደረጃ ፍ/ቤት በዚህ ነጥብ ላይ ውሳኔ ሳይሰጥ አልፍታል። በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት አመልካች ለፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት ባቀረቡት ይግባኝ የመለዋወጫና የሕንፃ መሣሪያ ድርጅቱን ከነሙለ እቃው ክፍፍለ ውስጥ እንዱገባ ጠይቀው የስር ፍ/ቤት ውሳኔ ሳይሰጥ በማለፈ ይኸው እንዱወሰንላቸው አመልክተዋል። ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤትም ግራ ቀኙን ካከራከረ በኋላ አመልካች በስር ፍ/ቤት ድርጅት ለመካፈል አልጠየቁም፣የመለዋወጫ እቃዎችን በተመለከተ የእቃዎቹን ዝርዝር ካለማቅረባቸውም በላይ ተጠሪ እነዚህ ንብረቶች መሸጣቸውን ገልፀው የሚከራከሩ ቢሆንም አመልካች ግን እቃዎቹ ስለመኖራቸው ያቀረቡት ማስረጃ የለም። ስለዚህ ምንም እንኳን የስር ፍ/ቤት በዚህ ጉዲይ ላይ ውሳኔ ሳይሰጥ ማለፈ አግባብ ባይሆንም ከውጤቱ አንፃር የሚያመጣው ለውጥ የለም በማለት የስር ፍ/ቤትን ውሳኔ አጽንቷል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሳኔ ላይ ሲሆን አመልካች በቅሬታቸው ላይ ንግድ ፍቃደም ቢመለስ ንብረቶቹ በተጠሪ እጅ ስለሚገኙ መካፈል ሲገባን መታለፈ ስህተት ነው በማለት ተከራክረዋል። ይህ ችልትም ይህንኑ የአመልካችን ቅሬታ ለመመርመር አቤቱታው ለሰበር ችልት እንዱቀርብ በማድረጉ የግራ ቀኙ የቃል ክርክር ተሰምቷል። መዝገቡም እንደሚከተለው ተመርምሯል።
አመልካች በስር ፍ/ቤት የመለዋወጫና የህንፃ መሳሪያ ለመካፈል ጠይቀዋል። ነገር ግን በስር ፍ/ቤት እንዱሁም በዚህ ችልት ግራ ቀኙ ካደረጉት ክርክር አመልካች የሚጠይቁትን ንብረቶች ዝርዝር አለማቅረባቸውን ተረድተናል። አንድ ከሳሽ የሚጠይቀውን ነገር ለይቶ ማስቀመጥ እንዲለበት የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 225/1/ ያመለክታል። በዚህ መሰረት አመልካች የሚጠይቁትን ንብረቶች ዝርዝር ለይተው ማስቀመጥ ሲገባቸው ይህ አላደረጉም። ከዚህ ላላ ተጠሪ በክርክራቸው የመለዋወጫና የህንፃ መሳሪያ ሱቅ ሲዘጋ እቃዎቹ መሸጣቸውን በመግለጽ ተከራክረዋል። አመልካች ንብረቱ አለ በማለት የሚከራከሩ በመሆኑ ስለንብረቱ መኖር የማስረዲት ሸክም አለባቸው። በፍትሐብሕር ክርክር አንድ መብት ወይም ግዳታ አለ ብል የሚከራከር ወገን መብቱ ወይም ግዳታው ስለመኖሩ የማስረዲት ሸክም አለበት(one who alleges in the affirmative shall prove it)። ይህ መብት ወይም ግዳታ መኖሩን ካላስረዲ ፍ/ቤቱ ጥያቄውን ውድቅ ሉያደርገው ይገባል። በተያዘው ጉዲይ አመልካች ንብረቶቹ አለ በማለት ይከራከሩ እንጂ ስለመኖራቸው ማስረጃ እንዲላቀረቡ ከመዝገቡ ተረድተናል። በመሆኑም አመልካች ተጠሪ እንዱያካፍሎቸው የሚጠይቁት የንብረት አይነቶች ዘርዝረው ያላቀረቡ ከመሆኑም በላይ ንብረቶቹ ስለመኖራቸው እንኳን ማስረጃ ስላላቀረቡ የስር ፍ/ቤቶች ያቀረቡትን ጥያቄ ውድቅ በማድረጋቸው መሰረታዊ የሕግ ስህተት ፈጽመዋል ለማለት አይቻልም።
የፋ/መ/ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 51214 ጥቅምት 6 ቀን 2000 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ እንዱሁም የፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 60553 ጥር 25 ቀን 2001 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ ፀንቷል።
ግራ ቀኙ ወጪና ኪሳራ ይቻቻለ።
No topics extracted.