No summary available.
የካቲት 25 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ መስፍን እቁበዮናስ ኂሩት መለሰ ተሻገር ገ/ስላሴ አልማው ወላ አመልካች፡- አቶ ተስፊዬ አለሙ - ጠ/ሃይለ ንጋቱ ቀረቡ ተጠሪ፡-
ለዚህ ሰበር አቤቱታ መነሻ የሆነው አመልካች በፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት ያቀረቡት ክስ ነው። አመልካች በክሳቸው ሁለተኛ እና ሦስተኛ ተጠሪ ባልና ሚስት ሆነው የሳሙና ፊብሪካ ድርጅት በብር 450,000 እንደሸጡላቸው፣ አመልካች ብር 250,000 ከፍለው ድርጅቱን ተረክተው ብር 150,000 አውጥተው ግንባታ መስራታቸውን፣ሁለተኛ ተጠሪ ሆነ ብለው ስንቅ የላለው ቼክ ለአንደኛ ተጠሪ ሰጥተው ሲፈረድባቸው ለአመልካች የሸጡት ቤት ለውሳኔው ማስፈጸሚያ መያዙን፣በዚህም ምክንያት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 418 መሰረት መቃወሚያ አቅርበው መቃወሚያው ውድቅ በመደረጉ ክሱን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 421 መሰረት ማቅረባቸውን ገልፀው ንብረቱ የተከበረው ያለአግባብ ነው እንዱባልና በድርጅቱ ላይ አመልካች መብት ያላቸው መሆኑ ተረጋግጦ እንዱወሰንላቸው ጠይቀዋል። አንደኛ ተጠሪ በሰጡት መልስ በመ/ቁ.
137/93 በተሰጠው ውሳኔ እና በመ/ቁ. 11684 በተሰጠው ትእዛዝ የመልካች ጥያቄ ውድቅ የተደረገ በመሆኑ ድጋሚ ክስ ሉያቀርቡ አይገባም በማለት ተከራክረዋል። ሁለተኛ እና ሦስተኛ ተጠሪዎችም አመልካች ውል እንዱፈፀምላቸው ክስ አቅርበው እያለ በድጋሚ ይህን ክስ ማቅረባቸው ተገቢ እንዲልሆነና አንደኛ ተጠሪ ከሁለተኛ እና ሦስተኛ ተጠሪ ጋር ተጣምረው መከሰሳቸው ከሥነ-ሥረአት ውጪ ነው በሚል ክሱን ተቃውመዋል። ፍ/ቤቱም ጉዲዩን መርምሮ አንደኛ ተጠሪ የሚከሰሱበት ምክንያት የለም በማለት ከክሱ ሲያሰናብታቸው ፍሬ ጉዲዩን በተመለከተ ደግሞ አመልካች ውል ይፈፀም በሚል ክስ ስላቀረቡ በተመሳሳይ ጉዲይ ዲግመኛ ክስ ላቀርብ አይገባም በማለት የአመልካችን ክስ ውድቅ አድርጏታል። በዚህ ውሳኔ ላይ አመልካች ለፋ/ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ አቅርበው ፍ/ቤቱ የስር ፍ/ቤት ውሳኔ አጽንቷል።
የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሳኔ ላይ ነው። የአመልካች ቅሬታ በአጭሩ አንደኛ ተጠሪ ልከሰስ አይገባም ብለው ሳይቃወሙ ከክሱ ውጪ መደረጋቸው የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 421ን ያላገናዘበ ነው፣በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 418 የቀረበ መቃወሚያ ውድቅ ከተደረገ በሁለቱ ወገኖች መሃከል በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 421 “ን” መሰረት መብት ለማረጋገጥ ክስ ላቀርብ እንማይችል ተደርጏ የተሰጠው ብይን የተሳሳተ ነው፣እንዱሁም ውል እንዱፈፀም የቀረበው ክስ በከፍተኛ ፍ/ቤት የተያዘው ክርክር ውጤት እዱጠብቅ ተብል የቆመ በመሆኑ በጉዲዩ ላይ ውሳኔ ተሰጥቶበት እደገና ክስ እንደቀረበ ተደርጏ የተሰጠው ብይን አግባብ አይደለም የሚል ነው። የስር ፍ/ቤቶች የአመልካች ክስ ካሁን በፉት የታየ ነው በሚል ክሱን ውድቅ ማድረጋቸው አግባብ መሆን አለመሆኑን ለመመርመር አቤቱታው ለሰበር ችልት ያስቀርባል ተብሎል። በዚህ መሰረት አንደኛ ተጠሪ ቀርበው መልስ የሰጡ ሲሆን ሁለተኛ እና ሦስተኛ ተጠሪዎች ግን መጥሪያ ለመቀበል ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ጉዲዩ በላለበት ታይቷል። ችልቱም መዝገቡን ከተያዘው ጭብጥ አኳያ መርምሯል።
ለዚህ ሰበር አቤቱታ መነሻ የሆነው አመልካች በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 421 መሰረት ያቀረቡት ክስ ነው። ከፍ ሲል እንደተገለፀው አመልካች ከሁለተኛ እና ሦስተኛ ተጠሪዎች ላይ ገዛሁት የሚለት የሳሙና ፊብሪካ በሁለተኛ ተጠሪና በአንደኛ ተጠሪ መሐከል በነበረው ክርክር በአፈፃፀም በመያዙ አመልካች ለፍርደ አፈፃፀም በተያዘው ንብረት ላይ በላለበት የቀዲሚነት መብት ያላቸው መሆኑን በመግለጽ መቃወሚያ አቅርበው ውድቅ ተደርጏባቸዋል። በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 421 ስር የቀዲሚነት መብት አለኝ በሚል መቃወሚያ አቅርቦ መቃወሚያው ውድቅ የተደረገበት ሰው ለክርክሩ መነሻ በሆነው ንብረት ላይ ክስ ለማቅረብ እንደሚችል ተመልክቷል። በመሆኑም አመልካች በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 418 መሰረት ያቀረቡት መቃወሚያ ውድቅ ስለተደረገባቸው በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 421 መሰረት ክስ ማቅረባቸው የሕግ ድጋፍ አለው። አመልካች በሰበር አቤቱታቸው ላይ እንዲለት ሳይሆን ጉዲዩ የቀረበለት የፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤትም ይህን እንደተገነዘበው መዝገቡ ያሳያል።
ፍ/ቤቱ የአመልካች ክስ ውድቅ ያደረገው አመልካች ቀደም ሲል ውል ይፈፀምልኝ የሚል ክስ ያቀረቡ በመሆኑ በተመሳሳይ ጉዲይ ድጋሚ ክስ ሉያቀርቡ አይችለም በማለት ነው። ይህ ችልትም ለትክክለኛ ፍትህ አሰጣጥ ይረዲው ዘንድ አመልካች ውል እንዱፈፀምላቸው ክስ ያቀረቡበትን መዝገብ አስቀርቦ ተመልክቷል። በዚህ መዝገብ አመልካች በሁለተኛ እና ሦስተኛ ተጠሪዎች ላይ ሳሙና ፊብሪካ ድርጅት መግዛታቸውንና ድርጅቱን መረከባቸውን ገልፀው በውለ መሰረት የሸጡትን ንብረት በከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 137/93 የተሰጠውን እግድ ትእዛዝ ጨምሮ ከማናቸውም እዲና እገዲ ነፃ በማድረግ የውል ግዳታቸውን እንዱፈጽሙ፣ግዳታቸውን መፈፀም የማይችል ከሆነ ውለ ፈርሶ ወደነበሩበት እንዱመለሱና መቀጫ እንዱከፍለ እንዱወሰንባቸው ክስ መስርተዋል። ለቀረበው ክስ ግራ ቀኙ መልስና የመልስ መልስ ከተቀባበለ በኋላ ፍ/ቤቱ ግንቦት 26 ቀን 1995 ዓ.ም በዋለው ችልት በሰጠው ትእዛዝ ለክርክር ምክንያት የሆነው ቤት በአፈፃፀም ምክንያት በመያዙ አመልካች መቃወሚያ ያቀረቡ በመሆኑ ፍ/ቤቱ በመቃወሚያው ላይ የሚሰጠው ውሳኔ እስኪታወቅ መዝገቡ ለጊዜው እንዱዘጋ አድርጓል። ነገር ግን የከፍተኛው ፍ/ቤቱ አመልካች በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 418 መሰረት ያቀረቡትን መቃወሚያ አይቶ ውሳኔ ከሰጠ በኋላም ቢሆን አምልካች የመ/ቁ. 01520 የሆነውን መዝገብ አላንቀሳቀሱም። አመልካች የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 421 መሰረት አድርገው በመሰረቱት ክስ የጠየቁት የመብት ጥያቄ በመ/ቁ.
No topics extracted.
01520 የሚጠይቁት ጋር ልዩነት የለውም። በዚህ መዝገብ በጠየቁት መሰረት ቢወሰንላቸው በድጋሚ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.
421 መሰረት ክስ ማቅረብ አያስፈልጋቸውም። በመሆኑም አመልካች በአንድ በኩል ውል እንዱፈፀምላቸው ክስ መስርተው ይህ ጉዲይ እልባት ሳያገኝ በድጋሚ በልላ መዝገብ ተመሳሳይ ጥያቄ ማቅረባቸው አግባብ አይደለም። የቀዲሚነት መብት አለኝ በሚል መቃወሚያ አቅርቦ ጥያቄው ውድቅ የተደረገበት ሰው በድጋሚ ክስ ማቅረብ የተፈቀደለት በአፈፃፀም ችልቱ የንብረቱ ባለመብትነት በጭብጥነት ተይዞ በመደበኛው የሙግት ስርአት አይነት የአመልካቹ ጥያቄ ከግራ ቀኙ ክርክርና ማስረጃ አንፃር ተመርምሮ ውሳኔ የሚሰጥበት ባለመሆኑ ይህንን እድል ለመስጠት ነው። አመልካቹ ይህንን መብት የሚያስከብርለት ላላ ክስ የመሰረተ ከሆነ ግን የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 421 ክስ ለማቅረብ ስለሚፈቅድ ብቻ በተመሳሳይ ጉዲይ ዲግመኛ ክስ ማቅረብ ስነ-ስርአት ህጉ አላማ አይደለም። በመሆኑም አመልካች ውል ይፈጽምልኝ በሚል ክስ ያቀረቡበትን መዝገብ በማንቀሳቀስና ክርክሩን መቀጠል እየቻለ በድጋሚ ክስ ማቅረባቸው ተገቢ ባለመሆኑ ክሱ ውድቅ በመደረጉ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል ማለት አይቻልም። በመሆኑም ተከታዩ ውሳኔ ተሰጥቷል።
የፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 24926 ሚያዝያ 3 ቀን 1998 ዓ.ም የሰጠው ብይንና ፋ/ጠ/ፍ/ቤት በመ/ ጥር 23 ቀን 2000 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ ፀንቷል።
ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።