No summary available.
ጥር 12 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ መንበረፀሐይ ታደሰ ሑሩት መለሰ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- የቀድሞ ወረዲ ዐ7 ቀበላ 32 አስተዲደር ጽ/ቤት - ነ/ፈጅ ደረጀ ይታገሱ - ቀረቡ።
ተጠሪ፡- ወ/ሮ ጆሮ ዋቅጅራ - ቀረቡ።
**
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ ዲኝነት በድጋሚ እንዱታይ የሚቀርብ አቤቱታ መሰረት ያደረገ ነው። ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ አመልካች በተጠሪ በተመሰረተበት የቤት ይለቀቅልኝ ክርክር የአዱስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት መጋቢት 18 ቀን 1994 ዓ.ም. በዋለው ችልት ቁጥራቸው 5ዐ8 እና 5ዐ9 የሆኑት ቤቶች ለአሁኑ ተጠሪ እንዱመለሱላቸው ውሣኔ ከሰጠ በኋላ ጥር 13 ቀን 1995 ዓ.ም. በተፃፈ አቤቱታ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 6 መሰረት ዲኝነት በድጋሚ እንዱታይለት ምክንያቱን ገልፆ ፍርደን በድጋሚ እንዱያየውና እንዱለውጠው የመጀመሪያውን ፍርድ ለሰጠው ለዚሁ ፍርድ ቤት አቤቱታውን አቅርቦ ፍርድ ቤቱም ግራ ቀኙን ካከራከረ በኋላ በመጀመሪያው ፍርድ ቤት ይግባኝ ከተባለ በኋላ ዲኝነት በድጋሚ እንዱታይ አቤቱታ ላቀርብ እንደማይችል፣ እንዱሁም አቤቱታው በቀረበበት ጉዲይ የመጀመሪያው ፍርድ የተሰጠበት አግባብ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 6 ሥር የተመለከቱትን ነገሮች ባለበት ስለመሆኑ በድጋሚ የቀረበው አቤቱታ እንደሚያሳይ ገልፆ ዲኝነቱ በድጋሚ ላታይ አይገባም በማለት የአመልካችን አቤቱታ ውድቅ አድርጓል። በዚህ ብይን አመልካች ባለመስማማት ይግባኙን ለከተማው ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት አቅርቦ ይህ ፍርድ ቤት በበኩለ ግራ ቀኙን ካከራከረ በኋላ በፍ/ብሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 6 መሰረት አቤቱታ ቀርቦ ከታየ በኋላ ብይኑ ይግባኝ የላለው በመሆኑ በይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የማታይበት አግባብ የለም በማለት ዋናውን ጉዲይ ሳይመለከተው መዝገቡን ዘግቶታል። ከዚህም በኋላ አመልካች አቤቱታውን ለከተማው ሰበር ሰሚ ችልት አቅርቦ በይግባኝ ሰሚው ችልት የተሰጠው ትዕዛዝ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የለበትም በሚል ውድቅ ሆኖበታል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሣኔ ለማስቀየር ነው።
የአመልካች ነገረ ፈጅ ጥር 15 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም. በፃፈት አራት ገጽ የሰበር አቤቱታ በበታች ፍርድ ቤቶች ውሣኔ ላይ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል የሚለበትን ምክንቶች ዘርዝረው አቅርበዋል። ይዘቱም ባጭሩ፡- ተጠሪ ለክርክሩ ምክንያት የሆኑትን ቤቶች በፍርድ ባለመብት የሆኑበት የባለቤትነት ደብተር ሐሰተኛ መሆኑ ተረጋግጦ በሚመለከተው የአስተዲደር አካል የተሰረዘ ስለመሆኑ በመግለጽ ዲኝነት እንደገና እንዱታይ ለሥር ፍርድ ቤት አቤቱታ ቀርቦለት ሳይቀበለው መቅረቱ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ስለሆነ ታርሞ ለረጅም ጊዜያት በመንግሥት ቁጥጥር ሥር የነበሩት ቤቶች ላይ ተጠሪ መብት የላቸውም ተብል ሉወስን ይገባል ሲለ ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው።
የአመልካች አቤቱታ ተመርምሮም አመልካች ዲኝነት እንደገና እንዱታይለት ያቀረበው ጥያቄ በጉዲዩ ላይ ይግባኝ ስለተጠየቀበትና የቀረበው አዱስ ማስረጃ ተገቢ ባልሆነ መንገድ ስለመገኘቱ አልተረጋገጠም በሚለት ምክንያቶች ውድቅ የመደረጉ ሁኔታ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 6 ድንጋጌን በትክክል በመተርጎም መሆን ያለመሆኑን ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ ለሰበር ችልት እንዱቀርብ ተደርጎ ተጠሪ ጥቅምት 19 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም. በፃፈት ሦስት ገጽ ማመልከቻ መልሳቸውን ሰጥተዋል። የአመልካች ነገረ ፈጅ በበኩላቸው ታህሣሥ 27 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም. በፃፈት ሦስት ገጽ ማመልከቻ የመልስ መልሳቸውን አድርገዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለ መልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሣኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
እንደመረመረውም የችልቱን ምላሽ የሚፈልገው አቢይ ነጥብ ለሰበር አቤቱታ መነሻ ከሆነው የመጨረሻ ውሣኔ ላይ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል ለማለት ይቻላልን የሚለው ነጥብ ሆኖ አግኝቶታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው አመልካች ዲኝነት በድጋሚ እንዱታይለት አቤቱታ አቅርቦ የሥር ፍርድ ቤት ዲግመኛ ዲኝነት እንዱታይ የቀረበውን አቤቱታ ከመቀበለ በፉት የአቤቱታው ግልባጭ ለተጠሪ በመላክ አቤቱታው ሉሰማ የማይችልበትን መከራከሪያ እንዱያቀርቡ ትዕዛዝ ሰጥቶ ክርክሩን መስማቱን፣ ክርክሩን ከሰማ በኋላ የአመልካችን አቤቱታ በጉዲዩ ላይ ይግባኝ የተባለበት በመሆኑ ዲኝነት በድጋሚ እንዱታይ የተጠየቀበት ሰነድም በሐሰተኛ መንገድ የተገኘ ስለመሆኑ አልተረጋገጠም በማለት ዲኝነቱን በድጋሚ ላታይ አይገባውም ሲል ብይን መስጠቱን፣ በዚህ ብይን አመልካች ቅር በመሰኘት ይግባኙን ለይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት አቅርቦም ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በኋላ ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤቱ በጉዲዩ ላይ ይግባኝ የሚባልበት አይደለም በሚል ምክንያት የአመልካችን ዋናውን ክርክር ሳይመለከተው መዝገቡን ከዘጋው ብኋላ አመልካች በዚህ የይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ውሣኔ ላይ ቅር በመሰኘት የሰበር አቤቱታውን ለከተማው ሰበር ሰሚ ችልት አቅርቦ ተቀባይነት ማጣቱን ነው። ከዚህ በግልጽ መረዲት የሚቻለው ለዚህ ችልት ለቀረበው የሰበር አቤቱታ መሰረት የሆነው ውሣኔ በጉዲዩ ላይ ይግባኝ ልባል የሚችልበት አይደለም የተባለበትን ውሣኔ ነው። ከዚህ አንፃር ይህ ችልት ማየትና ተገቢውን ውሣኔ መስጠት ያለበት በዚህ የከተማው ሰበር ሰሚ ችልት በፀናው፣ በጉዲዩ ላይ የሰጠው ብይን ይግባኝ የለበትም ተብል በተሰጠው ውሣኔ ላይ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሟልን የሚለውን መሰረት በማድረግ ስለመሆኑ ተገንዝበናል።
የአመልካች ነገረ ፈጅ በጉዲዩ ላይ ይግባኝ የሚባልበት አይደለም የሚለውን የበታች ፍርድ ቤቶችን ውሣኔም ሆነ በዚህ ረገድ የቀረበውን የተጠሪን ክርክር ተገቢ አይደለም በማለት የሚከራከሩት የሥር ፍርድ ቤት ወደ ዋናው ጉዲይ ገብቶ ሲያከራክር ቆይቷል በሚል ነው። ይሁን እንጂ የሥር ፍ/ቤት የውሣኔ ግልባጭ የሚያሳየው ፍርድ ቤቱ በአመልካች በኩል ዲኝነት በድጋሚ እንዱታይ አቤቱታ ሲቀርብ ተጠሪን በመጥራት ማከራከሩ አቤቱታው ሉሰማ የማይችልበትን መከራከሪያ እንዱያቀርቡ እድል ለመስጠት ስለመሆኑ ሲሆን ተጠሪ በፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ መሰረት ዲኝነቱ በድጋሚ ላታይ የማይችልበትን ምክንያት አቅርበው ተከራክረዋል። ይህም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 6/3/ ሥር የተመለከተው የሥነሥርዓት አካሄድ ሲሆን ተገቢነት ያለውም ነው። የሥር ፍርድ በዚህ መሰረት አቤቱታውን ካስተናገደ በኋላ ግን አመልካች ዲኝነቱ እንደገና እንዱታይ ያቀረበውን አቤቱታና ተጠሪ ዲኝነቱ በድጋሚ ላታይ አይገባውም በማለት ያቀረቡትን መከራከሪያ መሰረት በማድረግ ዲኝነቱ በድጋሚ ላታይ አይገባውም በማለት ብይን ሰጥቶታል። ይህ የስር ፍርድ ቤት ውሣኔ በግልጽ የሚያሳየው ፍርድ ቤት ዲኝነቱ እንደገና ላታይ ይገባዋል በማለት ብይን ከሰጠ በኋላ በዋናው ጉዲይ ግራ ቀኙን አከራክሮ የቀድሞውን ውሣኔ ያፀናው ስለመሆኑ አይደለም። በመሆኑም የአመልካች ነገረ ፈጅ የሥር ፍርድ ቤት በዋናው ጉዲይ ገብቶ ከአከራከረ በኋላ ውሣኔ ሰጥቶ እያለ በጉዲዩ ላይ ይግባኝ የሚባልበት አይደለም በሚል የከተማው ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ሆነ የሰበር ችልት ውሣኔ መስጠታቸው ያላግባብ ነው በማለት ያቀረቡት ክርክር የክርክሩን ሂደት ባግባቡ ያገናዘበ ባለመሆኑ የምንቀበለው ሆኖ አልተገኘም። ቀጠል መታየት ያለበት ጉዲዩ ይግባኝ የሚባልበት አይደለም የመባለን አግባብነት ነው። አንድ ጉዲይ በድጋሚ ዲኝነት ሲቀርብ ዲኝነቱ በድጋሚ ላታይ አይገባውም ወይም ይገባል ሲል ፍርድ ቤቱ ውሣኔ ሲሰጥ ይግባኝ ለማቅረብ የማይቻል ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 6/3/ እና /4/ ድንጋጌዎች ይዘት እና መንፈስ በግልጽ ያሳያለ። በዚህም መሰረት ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤትም ሆነ የሰበር ችልቱ ውሣኔ ሲታይ ሕጋዊ ነው። የአመልካች ነገረ ፈጅ አቤቱታ ሉያቀርቡ ይገባ የነበረው ሥርዓቱን ጠብቀው ለሰበር ሰሚ ችልት እንጂ ለይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት አይደለም። የዚህ ችልት ኃላፉነትና ተግባር ደግሞ በበታች ፍርድ ቤት በተሰጠው የመጨረሻ ውሣኔ ላይ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ሲፈፀም ማረም ስለመሆኑ የኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገ- መንግሥት አንቀጽ 8ዐ/3/ሀ/ እንዱሁም አዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 1ዐ እና 22 ድንጋጌዎች ያሳያለ። በመሆኑም የአዱስ ከተማ አስተዲደር ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤትና የሰበር ችልቱ የሥር ፍርድ ቤት በሰጠው ብይን ላይ ይግባኝ የሚባልበት አይደለም በማለት የተሰጠው የመጨረሻ ውሣኔ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 6/3/ እና /4/ ድንጋጌዎችን መሰረት ያደረገ በመሆኑ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው ለማለት አልተቻለም። በዚህ ምክንያት የአመልካች ነገረ ፈጅ በዋናው ጉዲይ ላይ ያቀረቡትን ክርክር ለመመርመር የሚያስችል ሥነ-ሥርዓት ባለመኖሩ አልፈነዋል። በዚህም መሰረት ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
በአዱስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት በመ/ቁጥር ዐ4111 ሚያዝያ 28 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. ተሰጥቶ በከተማው ሰበር ችልት በመ/ቁ. ዐ7548 ጥቅምት 28 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም. መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የለበትም ተብል በትዕዛዝ የፀናው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348/1/ መሰረት ፀንቷል።
የሥር ፍርድ ቤት ዲኝነቱ እንደገና ላታይ አይገባውም በማለት በሰጠው ብይን ላይ ይግባኝ የለውም ተብል መወሰኑ ባግባቡ ነው ብለናል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሣራ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
መዝገቡ ተዘግቷል፤ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.