No summary available.
ጥር 5 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ መንበረፀሐይ ታደሰ ሐጏስ ወልደ ሂሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- ወ/ሮ ትርሐስ ፍስሐዬ - ወኪል ዚርኡ ፍስሃዬ - ቀረበ ተጠሪ፡- ወ/ሮ ዘነበች በሪሁን - ቀረበች መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 6 መሰረት ዲኝነት እንዱታይ የቀረበውን አቤቱታ መሰረት በማድረግ የተደረገውን ክርክር የሚመለከት ነው። ዋናው ክርክር ሲጀመር ከሣሽ የነበረችው ተጠሪ ስትሆን፣ለአርሲ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ጥያቄ ያቀረበችው የአመልካች ባል ከነበረው ሟች ወልጃቸዋለሁ የምትላቸውን ሁለት ልጆች ልጅነት እንዱረጋገጥላት ነው።
በዚህ ጥያቄ ክስ መነሻነት ክርክር ከተካሄደ በኋላም ተጠሪ እንደ ጥያቄዋ ተወስኖላታል። ውሳኔው እስከ ፋ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ችልት ደርሶ እንደፀና በመዝገቡ ተመልክቷል። ይህ ሁለ ከሆነ በኋላ ነው አመልካች ዲኝነት ይታይልኝ በማለት አቤቱታ ያቀረበችው። ተጠሪ ያስወሰነችው ሐሰተኛ ማስረጃ በማቅረብ ፍ/ቤቱን በማሳሳት በመሆኑ ጉዲዩ በኋላ በተገኘው እውነተኛው ማስረጃ ተረጋግጦ ሉወሰን ይገባል የሚል ምክንያት በመስጠት ክርክሩን በመጀመሪያ ደረጃ ለሰማው የአርሲ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት አቤቱታዋን አቅርባለች። ፍ/ቤቱም የተጠሪንም መልስ ካየ በኋላ፣ጉዲዩ እስከ ፋዳራል ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ችልት ደርሶ የተወሰነ በመሆኑ በዚህ ደረጃ ሉስተናገድ አይችልም የሚል ምክንያት በመስጠት አቤቱታውን ውድቅ አድርጏአል። ጉዲዩን በመጨረሻ ያየው የኦሮሚያ ብ/ክ/መ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ችልትም በዚህ ረገድ የተፈጸመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የለም ብልአል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ላይ ነው።
አመልካች የካቲት 19 ቀን 2001 ዓ.ም በፃፈችው ማመልከቻ ዲኝነት እንዱታይላት ያቀረበችው ጥያቄ በበቂ ምክንያት የተደገፈ እንደሆነ፣የሥር ፍ/ቤቶች ሕጉ ሳይከለከል ጥያቄውን ውድቅ በማድረጋቸው በሕጉ አተረጓጏም ረገድ መሰረታዊ የሆነ ስህተት መፈጸማቸውን፣ባቀረበችው ጥያቄ መሰረት ጉዲዩ እንደገና ቢታይ ተጠሪ ቀደም ሲል ያሰጠችው ውሳኔ እንደሚሻር በመግለጽ አቤቱታዋን አቅርባለች። ተጠሪም ለአቤቱታው በሰጠችው መልስ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 6 “ን” መሰረት በማድረግ ዲኝነት እንዱታይ መጠየቅ የሚቻለው ቀደም ሲል በተሰጠው ውሣኔ ላይ ይግባኝ ከመባለ በፉት ነው።
የፋ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ችልት በመ/ቁ. 16624 በሰጠው ውሣኔ ይግባኝ ከተባለ በኋላ ድንጋጌው ተፈፃሚ እንደማይሆን በመግለጽ የሕግ ትርጉም ሰጥቶአል። አመልካች በኋላ አገኘሁ ያለችው ማስረጃም እኔን በወንጀል ሉያሰቀጣ የማይችል ሆኖ ተገኝቷል። የሚለት ነጥቦች በመከራከሪያነት አቅርባ አቤቱታው ውድቅ እንዱሆን ጠይቃለች።
እኛም ግራ ቀኝ ወገኖች ያሰሙትን ክርክር አቤቱታ ከቀረበበት ውሣኔ እና ከሕጉ ጋር አገናዝበን ተመልክተናል።
አመልካች ያቀረበቸው አቤቱታ በሰበር ችልት እንዱታይ ተወስኖ ክርክሩ እንዱሰማ የተደረገው ቀደም ሲል ለተሰጠው ውሣኔ መሰረት የሆነው ማስረጃ በሐሰት ተዘጋጅቶ የቀረበ ነው እየተባለ ውሣኔው ይግባኝ ተብልበታል በሚል ብቻ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 6 ሉስተናገድ አይችልም የመባለን አግባብነት ለመመርመር ነው። ይግባኝ ከተባለ በኋላ ዲኝነት በድጋሚ ላታይና አቤቱታው ሉስተናገድ ይገባል ወይስ አይገባም የሚለውን ጥያቄ በአግባቡ መመልስ የሚቻለው የድንጋጌው መንፈስ ምን እንደሆነ ትርጉም በመስጠት አንድ መደምደሚያ ላይ መድረስ ሲቻል ነው። ከዚህ ችልት የሚጠበቀውም በዚህ ረገድ ተገቢ ነው የሚለውን የሕግ ትርጉም በመስጠት በተደጋጋሚ እየተነሱ ላለት ተመሣሣይ ጥያቄዎች እልባት መስጠት በመሆኑ ጉዲዩን እንደሚከተለው በዝርዝር ተመልክተናል።
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 6 የተቀመጠው ድንጋጌ አዱስ ክስ የሚስተናገድበት ሥርአት አይደለም። በቀረበው ክስ መሰረት ክርክር ተካሂድ ውሣኔ ከተሰጠ በኋላ ዲኝነት በድጋሚ እንዱታይ ጥያቄ የሚቀርብበት ሥርአት የተዘረጋበት ነው።
ጥያቄውን የሚያቀርበው ወገን ለጉዲዩ አዱስ ሳይሆን፣ ከመጀመሪያውም ተከራካሪ የነበረ በመሆኑ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.
358 መሰረት መቃወሚያ ከሚያቀርበው ወገን በተለየ ሁኔታ የሚስተናገድ ነው። ይህም ሆኖ ጥያቄው የሚቀርበው ይግባኙን ለሚሰማው ፍ/ቤት ሳይሆን፣ውሣኔውን ለሰጠው ፍ/ቤት በመሆኑ ይህም የድንጋጌውን የተለየ ባህርይ ሉያሳይ እንደሚችል አድርጏ ለማየት የሚያስችል ነው። እንግዱህ ከእነዚህ ሁኔታዎች መገንዘብ የሚቻለው ሕጉ በቁጥር 6 የተቀመጠውን ሥርአት በመዘርጋት ሉያሳካው የፈለገው አንድ ግብ እንዲለ ነው። ከዚህ በመነሳትም የድንጋጌው ዓላማ ምንድን ነው የሚለውን ነጥብ ማየቱ አስፈላጊ ይሆናል። በመሆኑም ድንጋጌው አግባብነት የሚኖረው መቼ ነው? ይግባኝ ከመባለ በፉት ወይንስ ይግባኝ ከተባለ በኋላም ጭምር የሚለውን ለጊዜው አቆይተን ዓላማው ምንድን ነው? የሚለውን እንመለከታለን።፡ በዚህ ረገድ ጠቃሚ ሆነው የምናገኛቸው በንኡስ ቁ. (1)(ሀ) እና (ለ) የተቀመጡት ድንጋጌዎች ስለሆኑ ለአጠቃላይ ግንዛቤ ይረዲ ዘንድ ሙለ ይዘታቸውን እንመልከት፡- ሀ. የመጨረሻው ፍርድ ወይም ውሳኔ ወይም ትእዛዝ የተሰጠው በሐሰት ተዘጋጅቶ የቀረበውን ሰነድ ወይም ሐሰተኛ የምስክርነት ቃልን ወይም መደለያን ወይም ወንጀል ጠቀስ የሆነ ተግባርን መሰረት በማድረግ ሲሆንና አቤት ባዩም ፍርድ ከመሰጠቱ በፉት አስፈላጊውን ትጋት አድርጏ ለማወቅ ያለመቻለን ለማስረዲት የቻለ እንደሆነ በሚል የተደነገገ ሲሆን(ለ) ደግሞ ለ. ከዚህ በላይ የተዘረዘሩት ተግባሮች መፈጸማቸው ቢገለጽ ኖሮ ለፍርደ መለወጥ ወይም መሻሻል በቂ ምክንያት ሉሆኑ ይችለ እንደነበር ለማስረዲት የቻለ እንደሆነ፤
ነው ይላል። ሁለቱን ድንጋጌዎች አጣምረን ስንመለከት ሕጉ አቤቱታ የቀረበበት ውሣኔ ያኔ(ውሣኔው ሲሰጥ) ሉደረስባቸው ባልተቻለ ሐሰተኛ እና ወንጀል ጠቀስ የሆኑ ተግባሮችን ወይም ድርጊቶችን መሰረት አድርጏ የተሰጠ ሆኖ ከተገኘ ሕገ ወጥ ነው። በመሆኑም በሕገ ወጥነቱ ሉቀጥል ወይም ተፈፃሚነት ሉያገኝ አይገባም እሚል መነሻ ይዞ ነው የተደነገገው ወደሚለው ድምዲሜ ነው የምንደርሰው። ይህ ደግሞ በክርክር ሂደት እውነትን አንጥሮ ማውጣት ዋነኛው የፍርድ አመራር ስርአቱ ግዳታ ነው የሚል መሰረት ያለው እንደሆነ መገመቱ አይከብድም።
ለተያዘው ክርክር መነሻ የሆነው ቁ. 6 በተካተተበት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕጉ ከሚከናወኑት አበይት ተግባራት አንደ (ዋነኛው) ክርክሩን በተገቢው መንገድ መምራት እና በመጨረሻም እውነትን አንጥሮ በማውጣት ትክክለኛ ፍርድ መስጠት ነው። በዚህ አግባብ የሚሰጠው ፍርድ ፍትሐዊ እንደሚሆን የሚታመን ሲሆን፣እውነትን ለማውጣት ወሳኝ ሚና የሚጫወተው ደግሞ ማስረጃ ነው። የክርክር ጭብጦች የሚነጥሩት በማስረጃ በመሆኑ ሕጉ በዚህ ረገድ ትልቅ ትኩረት የሚሰጠው ማስረጃ የሚቀርብበትን ብቻ ሳይሆን፣የሚገኝበት ሁኔታም(መንገድም) የሕግ መሰረት ያለው ወይም ሕጋዊ ላሆን ይገባል። የክርክሩ አመራርም እንደዚሁ ሕጋዊ እና ወደ እውነት የሚያደርስ መንገድ ሉከተል ይገባል ብል ሕጉ ያምናል።
የሥነ ሥርአት ሕጉ ማስረጃ የሚቀርብበትን አግባብ እና የጊዜ ወሰን በመርህ ደረጃ በአንድ በኩል ሲያስቀምጥ፣ በልላ በኩል ደግሞ ከመርሁ ወጣ ባለ ልዩ ሁኔታ ማስረጃ ላቀርብ የሚችልበትን አግባብ ደንግጏ እናገኛለን። በመርህ ደረጃ ማስረጃ ማቅረብ ያለበት በማስረጃው እጠቀማለሁ የሚለው ተከራካሪ ወገን እንደሆነ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 223 እና 234 የተደነገገ ሲሆን፣ፍ/ቤቱ እውነት ላይ ለመድረስ የሚቻለው በዚህ ብቻ አይደለም የሚል እምነት ከያዘ ግን በራሱ ተነሳሽነት ማስረጃ አስቀርቦ እንደሚሰማ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 264 እና በላልችም ድንጋጌዎች ተመልክቶአል። ማስረጃ የሚቀርብበት የጊዜ ወሰንም እንደዚሁ በቁ. 137 የተቀመጠ ድንጋጌ ቢኖርም፣ይህ ጊዜ ካለፈም በኋላ ማስረጃ ማቅረብ የሚቻልበት ሁኔታ እንዲለ በቁ. 256 ተደንግጓል። ክሱን በሰማው ፍ/ቤት ያልቀረበን ማስረጃ በይግባኝ ደረጃ የሚሰማበት አግባብ እንዲለም በቁ. 345 ከተቀመጠው ድንጋጌ እንመለከታለን። ከእነዚህ ሁኔታዎች እንግዱህ መገንዘብ የምንችለው አንደና ዋነኛው ቁም ነገር ማስረጃ እውነትን አንጥሮ በማውጣት ረገድ ካለው ወሳኝ ሚና በመነሳት ከዋናው የማስረጃ አቀራረብ መርህ ወጣ ባለ ሁኔታም የሚቀርብበትና የሚሰማበት አግባብ በሥነ ሥርአት ሕጉ ተቀባይነት ማግኘቱን ነው።
ዓላማውም የሚሰጠው ውሣኔ እውነት ላይ ብቻ የተመሰረተ እንዱሆን ለማስቻል ነው።
ወደ ያዝነው ጉዲይ ስንመለስ ለዲኝነት እንደገና ይታይልኝ ጥያቄው መሰረት የሆነው ምክንያት የቀድሞው ውሣኔ የተሰጠው በሐሰት ተዘጋጅቶ በቀረበው ማስረጃ ላይ በመመስረት ነው የሚል ነው። ይህ ደግሞ ውሣኔው እውነትን አንጥሮ ያወጣ አይደለም ወይም እውነት የሆነውን ነገር ሐሰተኛ (ሕገወጥ) በሆነ ማስረጃ ተድበስብሶ ቀርቶአል የሚል መነሻ ያለው ነው። በዚህ ረገድ አመልካች የያዘችው እምነት ዲኝነቱ እንደገና ከታየ የቀድሞው ውሣኔ በእርግጥ ይሻራል የሚል ነው። ተጠሪ ደግሞ ዲኝነት እንደገና እንዱታይ ጥያቄ የሚቀርብበት አግባብ አክትሞአል ወይም በሩ ዝግ ነው የሚል መከራከሪያ ነው ያላት። ይህ በተጠሪ የተነሳው የመከራከሪያ ነጥብ ዲኝነቱ እንደገና ታይቶ ማስረጃ ከተሰማ በኋላ ሉገኝ የሚችለውን ውጤት ግምት ውስጥ ያስገባ አይደለም። የአመልካች ክርክር ግን እውነት የሚገኝበትን አግባብ መሰረት ያደረገ ነው። በመሆኑም የሕጉ ትርጉም ይህ ነው ወደሚለው ድምዲሜ ከመድረሳችን በፉት በድንጋጌው ዙሪያ ሉነሱ የሚችለት ሁለት አማራጮችን አንድ በአንድ ማየት ተገቢ ሆኖ አግኝተነዋል።
የመጀመሪያው አማራጭ ለቀድሞው ውሣኔ መሰረት የሆነው ማስረጃ በሐሰት ተዘጋጅቶ የቀረበ መሆኑን በክርክሩ ሂደት አረጋግጦ ውሳኔውን መለወጥ ወይም ማሻሻል የሚቻልበት ሁኔታ እንደሚኖር ቢገመትም፣ድንጋጌው ስለማይፈቅድ(ይግባኝ ስለተባለ) አቤቱታውን ከወዱሁ ውድቅ ማድረግ የሚለው ነው። የመጀመሪያውን አማራጭ ስንመለከት ክርክሩ በሕግ አግባብ ብቻ ተመርቶ እና በሕግ መሰረት ብቻ የተገኘውን ማስረጃ መሰረት አድርጏ የተሰጠው ውሣኔ እውነትን አንጥሮ ያወጣል የሚለው የሕጉን ዓላማ ስለሚያሳካ ውጤቱ መልካም ነው የሚል ግንዛቤ እንይዛለን።
ሁለተኛው አማራጭ በሁለት መልክ ላታይ ይችላል። አንደ በእርግጥም ሕጉ የሚከለክል ከሆነ ሕግን መጣስ በራሱ ክልክል በመሆኑ ሕጉን አክብሮ መቀበለ ተገቢ ነው ወደሚል ድምዲሜ የሚያደርስ ነጥብ እንመለከታለን።
ቀደም ሲል እንዲየነው አከራካሪ የሆነው በንኡስ ቁ. /1/ የተመለከተው ድንጋጌ በተለይም “…..ይግባኝ ላቀርብበት በሚችል ፍርድ ወይም ውሣኔ ወይም ትእዛዝ ላይ ቅሬታውን አቅርቦ ከማሰማቱ በፉት” የሚለው ሐረግ ነው። “ቅሬታውን አቅርቦ ከማሰማቱ በፉት” የሚለውን ሐረግ ለብቻው ወስደን ቃል በቃል ብንተረጉመው በእርግጥም ዲኝነት እንዱታይ የሚቀርበው ጥያቄ አቤቱታ አቅራቢው በተሰጠው ውሣኔ ላይ ይግባኝ አቅርቦ ከማሰማቱ በፉት ነው ወደሚለው ድምዲሜ ያደርሳል ልንል እንችላለን። ይሁንና ድንጋጌው በአጠቃላይ ሉተረጏም የሚገባው በውስጡ ከያዛቸው ላልች ሐረጏች እና በንኡስ ቁ. /1/ሀ/ እና /ለ/ ከተቀመጡት ሁኔታዎች እንዱሁም ከጠቅላላው የሥነ-ሥርአት ሕጉ ዓላማ ጋር ተገናዝቦ በመሆኑ በትርጉም የምንደርስበት መደምደሚያ አንድዋን ሐረግ ብቻ ወስደን ቃል በቃል በመተርጏም ከምንደርስበት የሰፊ ላሆን እንደሚችል ይገመታል።
ላላው ድንጋጌው ሲተረጏም ግምት ውስጥ መግባት ያለበት በድጋሚ ዲኝነት ይታይ ጥያቄ ከይግባኝ በፉት ይቅረብ የተባለበትን ምክንያት ነው። ውሣኔው በይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት ይታረማል (በድጋሚ ይታያል) በሚል እሳቤ ይግባኝ ተብልበት በክርክር ሂደት ባለበት ጊዜ ውሣኔውን ለሰጠው ፍ/ቤት የዲኝነት እንደገና ይታይ ጥያቄ ማቅረብ አንድን ጉዲዩ በተመሳሳይ ጊዜ በበታች እና በይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት እንዱሰማ በማድረግ ወጪን፣ጊዜን እና ጉልበትን ያለአግባብ ከማባከን እንደዚሁም ክርክሩ እንዱወሳሰብ ከማድረግ አልፍ የሚያስገኘው ጠቀሜታ የለም። ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት ጉዲዩን ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ. 345 እንዱሁም ቁ. 182 አንፃር በማየትም ተገቢውን ማስተካከያ ያደርጋል የሚለውንም እንደ አንድ ታሳቢ ሁኔታ አድርጏ መውሰድ ይቻላል።
በልላ በኩል ደግሞ ሕጉ በዚህ ደረጃ የተሻለውንና ምክንያታዊ የሆነውን አካሄድ ቢመርጥም፤ ጉዲዩ በይግባኝ ታይቶ ከተወሰነ በኋላ ለውሣኔው መሰረት የሆነው በቁ. 6/1/ሀ/ ከተመለከቱት ተግባሮች (ወይም ሁለም) ነው የሚል ጥያቄ ሉነሳ ይችላል ብል አላሰበም ማለት ግን የሚቻል አይደለም። ቀደም ሲል በዝርዝር ለማሳየት እንደሞከርነው ከሁለም በላይ መታየት ያለበት ሕጉ ዓላማ አድርጏ የተነሳው እውነት ላይ መድረስ ነው የሚለው ነው። እውነት ላይ መድረስ መቻል በፍትሕ አሰጣጥ ረገድ ከፍተኛ ዋጋ ያለው ውጤታማ ሥራ ነው። ሕግ ሲተረጏም ተጨባጭ ውጤት ላሰጥ በሚችል አኳኋን መሆን እንዲለበት ከአጠቃላይ የሕግ አተረጋጏም መርህ የምንገነዘበው ጉዲይ ነው። አከራካሪ ሆኖ የቀረበው የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 6 ተጨባጭ ውጤት ላሰጥ በሚችል አኳኋን ሉተገበር የሚችለው ውሣኔው ሐሰተኛ እና ወንጀል ጠቀስ የሆኑ ተገባሮችን መሰረት በማድረግ የተሰጠ ነው የሚል አቤቱታ እስከቀረበበት እና በቂና አሣማኝ መሆኑን ፍ/ቤቱ እስካመነበት ድረስ ይግባኝ ይባልበትም አይባልበትም ያለልዩነት ሥራ ላይ እንዱውል በሚያስችል ሁኔታ ሲተረጏም ነው የሚል እምነት መያዙ ተገቢ ሆኖ አግኝተነዋል።
ከዚህ በመቀጠል የተመለከትነው በሰበር መ/ቁ. 16624 በተሰጠው ውሣኔ ለድንጋጌው የተሰጠው ትርጉም አሁን በያዝነው መዝገብ ከተሰጠው ትርጉም ጋር እንዳት ይጣጣማል? የሚለውን ነው። ድንጋጌውን እንደገና በስፊት ማየት ያስፈለገው የዲኝነት በድጋሚ ይታይ ጥያቄ በተደጋጋሚ እየቀረበ በመሆኑና የሚነሳው ክርክርም እውነት ሳይወጣ እየቀረ ነው የሚል ስለሆነ፤ከዚህ በላይ ደግሞ ጥያቄው የሚነሳው ጉዲዩ በይግባኝ ታይቶ ውሣኔ ካገኘ በኋላ እንደሆነ ግንዛቤ ስለተወሰደ ነው። በእርግጥም ጉዲዩ አሳሳቢ ሆኖ በመገኘቱ ከዚህ በፉት የተሰጠው ትርጉም እንደገና አይቶ በተደጋጋሚ እየተነሱ ላለት ጥያቄዎች ምላሽ ላሰጥ የሚችል እልባት ማድረግ አማራጭ ሆኖ አግኝተነዋል። ስለዚህ የፋዳራል ፍ/ቤቶችን አዋጅ እንደገና ለማሻሻል በወጣው አዋጅ ቁ. 454/97 አንቀጽ 2/1/ በተደነገገው መሰረት ቀደም ሲል ተሰጥቶ የነበረውን ትርጉም ለውጠን በዚህ በያዝነው መዝገብ የተሰጠው ትርጉም ገዥ ይሆናል ብለናል። በዚህም ምክንያት ተጠሪ በሰበር መ/ቁ. 16624 የተሰጠውን ውሣኔ መሰረት በማድረግ ያቀረበችውን ክርክር አልተቀበልንም። በመጨረሻም አመልካች ያቀረበችውን የዲኝነት ጥያቄ በመቀበል ተከታዩን ወስነናል።
የአርሲ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 01789 ኀዲር 5 ቀን 2001 ዓ.ም የሰጠው ብይን፣የኦሮሚያ ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ችልት በመ/ቁ. 70413 ታህሣሥ 14 ቀን 2001 ዓ.ም የሰጠው ትእዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽረዋል።
በሰበር መዝገብ ተሰጥቶ የነበረው ትርጉም ከላይ በተመለከተው ሁኔታ ተለውጧል።
አመልካች ያቀረበችው የዲኝነት ይታይልኝ አቤቱታ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 6 መሰረት ሉስተናገድ የሚገባው ነው ብለናል።
የአርሲ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት አመልካች ያቀረበችውን አቤቱታ በመቀበል እና ተጠሪ የምትሰጠውን መልስ አይቶ ጉዲዩን በመመርመር ተገቢ ነው የሚለውን ውሣኔ እንዱሰጥ ይመለስለት ብለናል።
በዚህ ሰበር ችልት በተደረገው ክርክር ግራ ቀኙ ወገኖች ወጪና ኪሣራቸውን ይቻቻለ።
No topics extracted.