No summary available.
የካቲት 26 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ መንበረፀሐይ ታደሰ ሂሩት መለሰ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- ወ/ሮ ፐሽፒላት ጆሴፍ ተጠሪ፡- አቶ ሰይፈ ጎሣዬ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የፋዳራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት የካቲት 18 ቀን 2000 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝና የከፍተኛው ፍርድ ቤት በመዝገብ ግንቦት 10 ቀን 2001 ዓ.ም የሰጠው ፍርድ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት ስላመለከቱ ነው። የክርክሩ መነሻ ተጠሪ ከአመልካች ጋር የነበረን ጋብቻ በፍች ከፈረሰ በኋላ በተስማማነው ሰኔ 27 ቀን 1998 ፍርድ ቤት ባፀደቀው ስምምነት መሰረት አመልካች ከጥቅምት 5 ቀን 1998 ዓ.ም ጀምሮ ትምህርት ቤቱን ለብቻቸው በማስተዲደር ያገኙት ገቢ ተጣርቶ እንድካፈል ይወሰንልኝ በማለት ለፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ያቀረቡት ክስ ነው። አመልካች በሥር ፍርድ ቤት በተከሳሽነት ቀርበው ከጥቅምት 1 ቀን 1998 እስከ ሰኔ 30 ቀን 1998 ዓ.ም በተጣራው ሪፕርት ላይ ባለሙያዎች ቀርበው መጣራት ያለበት ነጥብ እንዲለ በመጥቀስ ተከራክረዋል።
የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የጌታቸው ዋቅጅራና ጓደኞቹ የሂሳብ ባለሙያዎች ከጥቅምት 1 ቀን 1998 ዓ.ም እስከ ሰኔ 1 ቀን 1998 ዓ.ም ያለውን ሂሳብ ኦዱት በማድረግ ስቴፔስ ትምህርት ቤት በዚህ ጊዜ ውስጥ ብር 663,863 (ስድስት መቶ ስልሣ ሶስት ሺህ ስምንት መቶ ሥልሳ ሶስት ብር) የተጣራ ትርፍ ያገኘ በመሆኑ ግማሹን ማለትም ብር 331,931.50(ሶስት መቶ ሰላሣ አንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ ሰላሣ አንድ ብር ከሀምሳ ሣንቲም) ግራ ቀኙ ሰኔ 21 ቀን 1998 ዓ.ም ባደረጉትና ፍርድ ቤት ባፀደቀው መሰረት አመልካች ለተጠሪ እንድታካፍል በማለት ወስኗል። አመልካች በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለከፍተኛው ፍርድ ቤት አቅርበዋል። የከፍተኛው ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሣኔ አፅንቶታል። አመልካች ጋብቻችን በፍች ከፈረሰ በኋላ የጋራ ንብረታችንን ለመካፈል ባደረግነው ስምምነት ለዋይዜድ ህንፃ እና ለወ/ሮ ራሓል ህንፃ የኪራይ ቤቶችና ሻንበል ግቢ የተከፈለ የኪራይ ገንዘብ የጋራ እዲ እንደሆነ ተስማምተናል። ከዚህ አንፃር የሥር ፍርድ ቤት የኦዱት ሪፕርቱን ከውለ ጋር ሣያገናዝብና ላልች ማየት የሚገባውን ማስረጃ ሣያገናዝብ እኔን እዲ ተሸካሚ እንድሆን በማድረግ ተጠሪ ትርፍ እንዱካፈል የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት አመልክተዋል። ተጠሪ በበኩለ በኦዱት ተረጋግጦ በቀረበው መሰረት የሥር ፍርድ ቤት የሰጠው ውሣኔ ሚዛናዊ ነው።
መሰረታዊ የህግ ስህተት የለበትም የሚል ይዘት ያለው ሁለት ገፅ መልስ አቅርቧል።
በሥርና በሰበር የቀረበው ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም ጉዲዩን መርምረናል። ጉዲዩን እንደመረመርነው ተጠሪ አመልካች ጋር የነበረን ጋብቻ በፍች ከፈረሰ በኋላ ስለ ጋራ ንብረት ክፍፍል ባደረግነውና በፍርድ ቤት ቀርቦ ሰኔ 27 ቀን 1998 ዓ.ም ባደረግነው ስምምነት አንቀፅ 5 መሰረት አመልካች ስቴፔስ ትምህርት ቤት በግሎ ከጥቅምት 1 ቀን 1998 ዓ.ም እስከ ሰኔ 1 ቀን 1998 ዓ.ም ያስተዲደረች በመሆኑ በዚህ ጊዜ የተገኘውን የተጣራ ትርፍ በሂሳብ ባለሙያ ተጣርቶ እንድታካፍለኝ በማለት ክስ ያቀረበ መሆኑን አመልካች በበኩሎ በዚህ ጊዜ የተገኘውን ትርፍ ተጠሪ ለመጠየቅ የሚችለው በመጀመሪያ በስምምነታችን አንቀፅ 2 ንዐስ አንቀጽ 2 በጋራ እዲነት የተዘረዘሩት ዕዲዎች ተከፍለው የሚቀር ሲኖር ነው የሚል ክርክር ያቀረቡ መሆኑን ለመገንዘብ ችለናል። ተጠሪና አመልካች ያደረጉት ክርክርና የሚለያዩበት ነጥብ ከላይ በአጭሩ የተገለፀው ከሆነ የሥር ፍርድ ቤት ተገቢውን ጭብጥ በመመሥረት ጉዲዩን ወስኗል ወይስ አልወሰነም?
የሚለው ነጥብ በመጀመሪያ መታየት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል። የአንድ ክርክር ጭብጥ የሚመሰረተው ከሳሽ ያቀረቡትን ክስና ማስረጃ በተከሳሽ ያቀረበውን የመከላከያ መልስና ማስረጃ እንዱሁም ፍርድ ቤት በፍትሐብሕር ሥነ- ሥርዓት ሕግ ቁጥር 241 መሰረት የቃል ምርመራ ሲያደርግ ያገኘውን ፍሬ ጉዲይ መሰረት በማድረግ መሆን እንዲለበት በፍትሐብሕር ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 248 ይደነግጋል። ተጠሪ አመልካች ስቴፔስ ትምህርት ቤት ለብቻቸው ማስተዲደር ከጀመሩበት ከጥቅምት 1 ቀን 1998 ዓ.ም ጀምሮ ያለው ትርፍ ተጣርቶ እንዱሰጠው ሲጠይቅ ተጠሪ በበኩሎ ከዚህ በፉትም ሆነ በኋላ (ለዋይ ዜድ ህንፃ የወ/ሮ ራሓል የኪራይ ቤቶችና የሻንበል ግቢ) የኪራይ ዕዲዎች የጋራ እዲ በመሆኑ በስምምነታችን መሰረት ያለብን ዕዲ ተከፍል ቀሪ ካለ ብቻ ነው ለመጠየቅ የሚችለው የሚል ይዘት ያለው ክርክር አቅርባለች። ፍርድ ቤት በኦዱት ተጣርቶ እንዱቀርብ ትዕዛዝ የሰጠው ስቴፔስ ትምህርት ቤት ከጥቅምት 1 ቀን 1998 እስከ ሰኔ 30 ቀን 1998 ዓ.ም ያገኘውን የተጣራ ትርፍ(ገቢ) ነው። ለውሣኔውም መሰረት ያደረገው በእነዚህ በዘጠኝ ወራት ውስጥ ያለው ወጭና ገቢ ተሰልቶ የተገኘውን የኦዱት ውጤት ነው። አመልካች ያቀረበችው ክርክር በኦዱት ዘመኑ የማይሸፈኑ ለህንፃ ኪራይ የተከፈለ ዕዲዎች የተጠሪ የጋራ እዲ መሆናቸው በስምምነታችን አንቀፅ 2 ንዐስ አንቀፅ 2 ተደንግጓል። በዚህ መሰረት የጋራ እዲችን መጀመሪያ ተሰልቶ ነው መወሰን ያለበት በማለት ነው።
የሥር ፍርድ ቤት ተጠሪ በማስረጃነት ያቀረበውንና አመልካችና ተጠሪ ስለ ጋራ ንብረት ክፍያ ያደረጉትን ስምምነት አመልካች ያቀረበችውንና በኦዱት ዘመኑ የማይሸፈን ክፍያ እና የኦዱት ዘመኑ ያወጣውን ወጭና የተገኘውን ገቢ መነሻ በማድረግ ከኦዱት ከተሸፈነው ጥቅምት 1 ቀን 1998 እስከ ሰኔ 30 ቀን 1998 ዓ.ም ካለው ጊዜ ውጭ ያለው የአመልካችና የጋራ ዕዲ ተከፍል የሚቀር ተጠሪ ሉካፈለው የሚጠይቀው ገንዘብ ያለ መሆን አለመሆኑን በስፊት አይቶ ለመወሰን የሚያስችል ጭብጥ አልመሰረተም። ይኸም የሥር ፍርድ ቤት በፍታብሓር ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 248 ድንጋጌዎች መሰረት መመሥረት የሚገባውን ጭብጥ ሣይመሰርት ከጥቅምት 1 ቀን 1998 እስከ ሰኔ 30 ቀን 1998 ዓ.ም ስቴፔስ ትምህርት ቤት ያገኘውን የተጣራ ገቢ ብቻ መነሻ በማድረግ ውሣኔ የሰጠና መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
በሁለተኛ ደረጃ ተጠሪ አመልካች የስቴፔስ ት/ቤት የተጣራ ገቢ እንድታካፍለው የጠየቀው አመልካችና ተጠሪ ስለ ጋራ ንብረት ክፍፍል ተስማምተው ሰኔ 27 ቀን 1998 ፍርድ ቤት ቀርቦ የፀደቀውን ውል አንቀፅ 5 መሰረት በማድረግ ነው። አመልካች በበኩሎ ተጠሪ የተጣራ ትርፍ ልካፈል የሚል ጥያቄ ማቅረብ የሚችለው በመጀመሪያ በውለ አንቀፅ 2 ንዐስ አንቀፅ 2 የተገለፁት ዕዲዎች ከተከፈለ በኋላ ነው የሚልና ውልን መሰረት ያደረገ ክርክር አቅርባለች። የሥር ፍርድ ቤት ለውሣኔው ብቸኛ ማስረጃ አድርጎ የወሰደው የኦዱት ሪፕርት አመልካችና ተጠሪ ሰኔ 27 ቀን 1998 ዓ.ም በፍርድ ቤት ያፀደቁትን ውል የተሸፈኑ ጉዲዮች በሙለ በማጣራት ያቀረበ አይደለም። የኦዱት ሪፕርቱ ከጥቅምት 1 ቀን 1998 እስከ ሰኔ 3ዐ ቀን 1998 ዓ.ም ያለውን የስቴፔስ ት/ቤት ወጭና ገቢ የሚመለከት ነው። የኦዱት ሪፕርቱ የአመልካችና የተጠሪን ክርክር ለመፍታት እንደ አንድ ጠቃሚ ግብዓት ማስረጃ ከሚያገለግል በስተቀር አመልካች ከጥቅምት 1 ቀን 1998 ዓ.ም በፉት የከፈለትን የህንፃ ኪራይም ሆነ ከሰኔ 30 ቀን 1998 ዓ.ም በኋላ የከፈለትን የህንፃ ኪራይ በተሟላ ሁኔታ የማይሸፍን ማስረጃ ነው። የኦዱት ሪፕርቱ ከኦዱት ዘመን ውጭ 416,680 (አራት መቶ አስራ ስድስት ሺ ስድስት መቶ ሰማንያ ብር) አመልካች ወጭ ያወጡ መሆናቸውን ያመለክታል። ይህም የሚያሳየን አመልካችና ተጠሪ በውል የገቡትን ግዳታ በሚሸፍንና የተሟላ የሂሳብ ማጣራት ያልተደረገ መሆኑን ነው።
ከዚህ አንፃር ስንመለከተው የበታች ፍርድ ቤቶች አመልካችና ተጠሪ ተስማምተውበት በፍርድ ቤት የፀደቀውን ውል በአንቀፅ 2 ንዐስ አንቀፅ 2 የተደነገገውን በማለፍ የውለን አንቀፅ 5 ብቻ ውጤታማ ለማድረግ የሚችል ሂሳብ ተጣርቶ እንዱቀርብ የሰጡት ትዕዛዝና ከጥቅምት 1 ቀን 1998 እስከ ሰኔ 30 ቀን 1998 ዓ.ም ስቴፔስ ትምህርት ቤት ያገኘውን የተጣራ ገቢ ብቻ መነሻ በማድረግ አመልካች ለተጠሪ ብር 331,931.50 (ሶስት መቶ ሰላሣ አንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ ሰላሣ አንድ ብር ከሀምሳ ሣንቲም) እንድትከፍል የተሰጠው ውሣኔ የፍትሐብሕር ህግ ቁጥር አንቀፅ 1734 ንዐስ አንቀፅ 2 እና ሰኔ 27 ቀን 1998 ዓ.ም በፍርድ ቤት የፀደቀውን ውል አንቀፅ 2 ንዐስ አንቀፅ 2 የሚጥስና መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው በማለት ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትና የከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሣኔ ተሽሯል።
የፋዳራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት አመልካች ከጥቅምት 1 ቀን 1998 ዓ.ም በፉትና ከሰኔ 30 ቀን 1998 ዓ.ም በኋላ ለዋይዜድ ህንፃ፣ የወ/ሮ ራሓል ኪራይ ቤቶችና የሻንበል ግቢ የከፈለትን የኪራይ ገንዘብ በማስረጃ በማጣራትና በውለ አንቀፅ 2 ንዐስ አንቀፅ 2 መሰረት የጋራ ዕዲ መሆኑን በመገንዘብ ውሣኔ እንዱሰጥ ጉዲዩን በፍትሐብሕር ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 343 ንዐስ አንቀፅ 1 መሰረት መልሰንለታል ግልባጩ ይላክለት።
በዚህ ፍርድ ቤት የወጡትን ወጭና ኪሣራ ግራቀኙ ለየራሳቸው ይቻለ ይህ ፍርድ በፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የካቲት 26 ቀን 2002 ዓ.ም በሙለ ድምፅ ተሰጠ።
No topics extracted.