No summary available.
የሰ/መ/ ጥር 26 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሐጎስ ወልደ ሂሩት መለሰ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ አመልካች፡- ፔሮፋሰር ረዲ ተ/ኃይማኖት - አልቀረበም ተጠሪ፡- አቶ ልመንህ ተፈራ - ቀረቡ
በዚህ መዝገብ የቀረበው ጉዲይ ስራ ክርክርን የሚመለከት ነው። ተጠሪ በአዲማ ወረዲ ፍ/ቤት ባቀረቡት ክስ አመልካች ያለአግባብ ከስራ ስላሰናበቷቸው የተለያዩ ክፍያዎች እንዱከፍሎቸው ጠይቀዋል። አመልካች ለክሱ በሰጡት መልስ ተጠሪን በትምህርት ቤታቸው እንዱያስተምሩላቸው ቀጥረዋቸው ተጠሪ የተቀጠሩበትን ስራ በመተው ከላላ ት/ቤት ተማሪዎች ግቢ ውስጥ በማምጣት የሚያስተምሩ በመሆኑ ማስጠንቀቂያም ቢሰጣቸው ከድርጊታቸው ያልተቆጠቡ በመሆኑና ተጠሪው በአዲማ ልዩ ዞን ትምህርት ቢሮ ፅ/ቤት ተቀጥረው ደሞዝ የሚከፈላቸው በመሆኑ ከስራ የተሰናበቱት በአግባቡ ነው በማለት ተከራክረዋል። ፍ/ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክር ተመልክቶ ውሳኔ ከሰጠ በኋላ ይግባኝ ቀርቦ ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት ወረዲ ፍ/ቤቱ ጉዲዩን በማስረጃ አጣርቶ እንዱወስን በመመሪያ ተመልሶለታል። በዚህ መሰረት ወረዲ ፍ/ቤቱ ግራ ቀኙ ማስረጃ እንዱያቀርቡ ማዘዙንና ሁለቱም ወገኖች ግን ማስረጃ አለማቅረባቸውን መዝግቦ አመልካች ተጠሪ ፈፀሙ የተባለትን ጥፊት በማስረጃ ያላስረደ በመሆኑና በስራ ስንብት ደብዲቤው ላይ ለስንብቱ በምክንያትነት የተጠቀሰው የተማሪዎች ቁጥር መቀነስ እንጂ ተጠሪ ፈፅመዋል የተባለው ጥፊት ባለመሆኑ ስንብቱ ህገ-ወጥ ነው በማለት ተጠሪ የተለያዩ ክፍያዎች እንዱከፈላቸው ወስኗል። በዚህ ውሳኔ ላይ ይግባኝ የቀረበለት የአዲማ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤትም ሆነ የሰበር አቤቱታ የቀረበለት የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የስር ፍ/ቤት ውሳኔ ስህተት የለበትም በማለት ውሳኔውን አፅንተዋል። የአሁኑ ሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሳኔ ላይ ነው። የአመልካች ቅሬታ በአጭሩ ተጠሪ በስራቸው ላይ ጥፊት የፈፀሙ ለመሆኑ የቀረቡትን ማስረጃዎች ፍ/ቤቱ ሳይሰማ ውሳኔ መስጠቱን የህግ ስህተት ነው የሚል ነው። ይህ ችልትም የአመልካች ማስረጃዎች ሳይሰሙ ውሳኔ የመስጠቱን ህጋዊነት ለመመርመር አቤቱታው ለሰበር ችልት ያስቀርባል በማለቱ ግራ ቀኙ ክርክራቸውን በፅሁፍ አቅርበዋል። ተጠሪ በመልሳቸው በአመልካች የተነገረውን ጥፊቶች ያልፈፀሙ መሆኑን እና አመልካች በማስረጃ ዝርዝራቸው ላይ የቆጠሩዋቸውን ምስክሮች ማቅረብ ሲገባቸው ምስክሮቻቸውን በመለወጣቸው ፍ/ቤቱ ማስረጃቸውን ሳይሰማ ማለፈ አግባብ ነው በማለት የስር ፍ/ቤት ውሳኔ እንዱፀናላቸው ጠይቀዋል። ችልቱም አቤቱታ የቀረበበትን ውሳኔ ከተገቢው ህግ ጋር በማገናዘብ መርምሯል።
በዚህ መዝገብ መልስ ማግኘት ያለበት ጭብጥ አመልካች ያቀረቧቸው ምስክሮች ሳይሰሙ ውሳኔ መሰጠቱ በአግባቡ መሆን አለመሆኑ ነው። ከክርክሩ ሂደት እንደተረዲነው ጉዲዩ ቀደም ሲል የአዲማ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ጉዲዩን ወደስር ፍ/ቤት የመለሰው ተጠሪ ሙለ ቀን ሥራ መስራት አለመስራታቸው፣ ሥራ ትተው ላላ ቦታ ሲሰሩ የቆዩ መሆን አለመሆኑን፣ ከላላ ት/ቤት ተማሪዎች እያመጡ ያስጠኑ የነበረ መሆን አለመሆኑን፣ በአመልካች ላይ ጉዲት የሚያደርስ ድርጊት መፈፀም አለመፈፀማቸውና ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸው የነበረ መሆን አለመሆኑን በማስረጃ እንዱረጋገጥ ነው።
በዚህ መሰረት ግራ ቀኙ ማስረጃ እንዱቀርቡ ታዘው አመልካች ምስክሮቻቸውን በሚያሰሙበት ቀነ ቀጠሮ በ29/05/2001 ዓ.ም በተፃፈ በቃለ መሃላ በተደገፈ አቤቱታ ሁለት ምስክሮቻቸው መኖሪያ አድራሻቸውን በመቀየራቸውና አንደኛዋ በመውለዲቸው ምክንያት ሉያቀርቧቸው ባለመቻላቸው ተለዋጭ ምስክሮች እንዱሰሙላቸው ጠይቀዋል። ፍ/ቤቱም የአመልካችን ጥያቄ በሁለት ምክንያቶች ሳይቀበለው ቀርቷል። አንደኛው የምስክሮቹ ስም በመዝገቡ ውስጥ የላለና ተጠሪ መልስ ያልሰጡባቸው መሆኑ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ አመልካች ምስክሮቻቸውን ሉለውጡ የሚችለት መልሳቸውን በማሻሻል እንጂ እንዱሁ አይደለም የሚል ነው። በመሆኑም ፍ/ቤቱ የአመልካችን ጥያቄ ውድቅ ያደረገባቸው ምክንያቶች በህጉ ተቀባይነት ያለው መሆን አለመሆኑ መመርመር ይገባል።
የስር ፍ/ቤት ከሰጣቸው ከምክንያቶች ውስጥ አንደኛው ተለውጠው የቀረቡት ምስክሮችን አስመልክቶ ተጠሪ መልስ አልሰጠባቸውም የሚል ነው። ከመዝገቡ እንደተረዲነው አመልካች እንደክሳቸው አቀራረብ የሚያስረደላቸው ምስክሮች ዘርዝረው ማቅረባቸው አልተካደም። ነገር ግን እነዚህ ምስክሮች ሉሰሙ በተያዘው ቀነ ቀጠሮ በተለያየ ምክንያት መቅረብ ባለመቻላቸው ተለዋጭ ምስክሮች እንዱሰሙ አመልካች በቃለ-መሃላ በተደገፈ አቤቱታ ጠይቀዋል። በማስረጃ ዝርዝር ላይ የተቆጠሩ ምስክሮችን ማግኘት ባልተቻለ ጊዜ ምስክሮች የሚቀየሩበት የተለየ ሥነ-ሥርዓት በፍትሐ-ብሓር ሥነ-ሥርዓት ሕጉ ውስጥ የተቀመጠ ነገር የለም። በልላ በኩል ደግሞ አንድ ጊዜ በማስረጃ ዝርዝር ላይ የተጠቀሱ ምስክሮች በምንም ሁኔታ መለወጥ የማይቻል ስለመሆኑ የሥነ-ሥርዓት ህጉ ያስቀመጠው ገደብ የለም። በመሆኑም እንደየነገሩ ሁኔታ ፍ/ቤቶች ተለዋጭ ምስክሮች እንዱሰሙ ለመፍቀድ የሚከለክላቸው ህግ የለም። በተያዘው ጉዲይም ፍ/ቤቱ ተለዋጭ ምስክሮቹ በመከላከያ ማስረጃ ላይ ስላልተጠቀሱ አልሰማም ከማለት በቀር ምስክሮቹን እንዲይሰሙ የሚከለክል ህግ መኖሩን አልጠቀሰም። በእርግጥ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 223(2) እና 234 መሰረት የክሱ ማመልከቻና ከማመልከቻው ጋር ተያይዘው የቀረቡት የፅሁፍና ላልች ማስረጃዎች እንዱሁም የምስክሮች ዝርዝርና ማንኛውም ለፍ/ቤቱ የደረሱትን መግለጫዎች ትክክለኛ ግልባጮች ለተከሳሹ ሉደርሰው እንደሚገባ ሁለ ተከሳሹም የሚያቀርበው መልስና የመከላከያ ማስረጃ፣ የምስክሮች ዝርዝር ለከሳሽ ሉደርሰው እና ሉከራከርበት ይገባል። ፍ/ቤቱም እንዱሰሙ በተጠየቁት አዱስ ምስክሮች ላይ ተጠሪው አስተያየት የመስጠት እድል ሉሰጠው ይገባል የሚል ከሆነ ይህንኑ እድል ከመስጠት ባለፈ አመልካች ማስረጃቸውን እንዲያሰሙ የሚከለክልበት ህጋዊ ምክንያት አልነበረም። ተጠሪም ቢሆን ምስክሮቹ ሲመሰክሩ መስቀለኛ ጥያቄ በመጠየቅ ዕውነቱ እንዱወጣ የማድረግ መብት ስላላቸው ምስክሮቹ እንዲይሰሙ የሚከለከለበት የህግ ምክንያት ይህ ችልት አላገኘም።
No topics extracted.
ላላው ፍ/ቤቱ የሰጠው ምክንያት አመልካች ምስክሮቹን የሚለውጡ ከሆነ መልሳቸውን ማሻሻል ነበረባቸው የሚል ነው። በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 91 መሰረት አቤቱታ ሉሻሻል የሚችለው የአቤቱታው መሻሻል ነገሩን ይበልጥ የሚያብራራውና ለትክክለኛ ውሳኔ አሰጣጥ የሚረዲ ሆኖ ሲገኝ እንደሆነ የድንጋጌው ይዘት ያመለክታል። በመሆኑም ክስ ወይም መከላከያ የሚሻሻለው ጉዲዩን በይበልጥ የሚያብራራው ወይም የቀረበውን ክርክር በተሻለ ዓይነት ገልፆ የሚያስረዲው ወይም ሁኔታውን በዝርዝር አገላለፅ የሚያመለክት መሆኑ ሲታመን ብቻ እንጂ ምስክሮች ለመለወጥ ሲባል ብቻ የመልስ አቤቱታ እንዱሻሻል የተጠቀሰው የሥነ-ሥርዓት ድንጋጌ አይፈቅድም። በመሆኑም ስር ፍ/ቤት አመልካች ምስክሮቻቸውን ለመለወጥ የመከላከያ መልሳቸውን ሉያሻሽለ ይገባ ነበር በማለት አመልካች ምስክሮቻቸውን እንዲያሰሙ መከልከለ የሥነ-ሥርዓት ህጉን ያልተከተለ እና በሕገ-መንግስቱ አንቀፅ 20(4) ስር የተመለከተውን የመከላከያ ማስረጃ የማቅረብና ምስክሮቻቸውን የማሰማት መብታቸውን ያጣበበ ውሳኔ መሆኑን ተገንዝበናል። በመሆኑም ተከታዩ ውሳኔ ተሰጥቷል።
የአዲማ ወረዲ ፍ/ቤት በመ/ የካቲት 20 ቀን 2001 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ፣ የአዲማ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ ሚያዚያ 19 ቀን 2001 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ እንዱሁም የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ ግንቦት 12 ቀን 2001 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ ተሽሯል።
የአዲማ ወረዲ ፍ/ቤት አመልካች በተለዋጭ ያቀረቡዋቸውን ምስክሮች ሰምቶ ተገቢውን ውሳኔ እንዱሰጥ ጉዲዩን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 343(1) መሰረት መልሰናል።
ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።