No summary available.
ጥር 25 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ሐጎስ ወልደ ሑሩት መለሰ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ አመልካች፡- አቶ ውብሸት ካሳዬ - ጠበቃ ኃይለ ገ/ሥላሴ ተጠሪ፡- የኢትዮጵያ ማዕድን ሃብት ኮርፕሬሽን - ነ/ፈጅ ግርማ አለሙ ቀረቡ
ለሰበር አቤቱታ መነሻ የሆነው ጉዲይ የጀመረው ከፋ/መ/ደረጃ ፍ/ቤት ነው። አመልካች በስር ፍ/ቤት ከሳሽ ነበሩ።
የክርክሩም አመጣጥ የሚከተለው ነው። ተጠሪ ያለአግባብ ከስራ አሰናብቶኛል በሚል ክፍያ እንዱከፈላቸውና ምስክር ወረቀት እንዱሰጣቸው በፋ/መ/ደረጃ ፍ/ቤት ክስ አቅርበው ተጠሪ አመልካች የአሰሪ ወገን ሳይሆኑ የሰራተኛ ወገን ናቸው በሚል መቃወሚያ በማቀረቡ ፍ/ቤት ተጠሪ የአሰሪ ወይም የሰራተኛ ወገን ስለመሆናቸው በስራ ክርክር ችልት አስወስነው ሲቀርቡ መዝገቡን የማንቀሳቀስ መብታቸውን ጠብቆ መዝገቡን ዘግቶታል። አመልካችም በዚሁ መሰረት በስራ ክርክር ችልት የአሰሪ ወገን መሆናቸውን አስወስነው መዝገቡን እንዱንቀሳቀስላቸው ሲያመለከቱ መዝገቡ በመጥፊቱ የቀድሞ ክስና የተጠሪ መልስ ተያይዞ ክሱ በአዱስ መዝገብ እንዱቀርብ ተደርጓል። ፍ/ቤቱም የአመልካች አቤቱታ ከነአባሪው ለተጠሪ ደርሶ ተጠሪ አስተያየት እንዱያቀርብ አዟል። ከዚህ በኋላ አመልካች በተከታታይ ቀጠሮዎች ባለመቅረባቸው ፍ/ቤቱ መዝገቡን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 280 መሰረት ዘግቷል። አመልካችም የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 71(2)“ን” መሰረት አድርገው መዝገቡ እንዱከፈትላቸው ሲያመለክቱ ፍ/ቤቱ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 280 የተዘጋ መዝገብ አመልካች በጠቀሱት የሥነ-ሥርዓት ህግ መሰረት ሉከፈት አይችልም በማለት ጥያቄውን ሳይቀበለው ቀርቷል። በዚህ ውሳኔ ላይ አመልካች ለፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ ያቀረቡት ይግባኝ ተቀባይነት አጥቷል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሳኔ ላይ ነው። አመልካችም በቅሬታቸው በስር ፍ/ቤት ያቀረቡት ክስ ለተጠሪ ደርሶ መልስ እና የመልስ መልስ የተቀባበልን ስለሆነ ፍ/ቤቱ ጉዲዩን መወሰን ሲገባው መዝገቡን መዝጋቱ ስህተት ነው የሚል ነው። ይህ ችልትም የአመልካች አቤቱታ ለሰበር ችልት ያስቀርባል በማለቱ ግራ ቀኙ ቀርበው የቃል ክርክራቸው ተሰምቷል። ችልቱም አቤቱታ የቀረበበትን ትዕዛዝ ከተገቢው ህግ ጋር በማገናዘብ ተመልክቷል።
ከፍ ሲል የተገለፀው የግራ ቀኙ ክርክርና የስር ፍ/ቤቶች ውሳኔ ሲሆን በዚህ ጉዲይ ምላሽ ማግኘት የሚያስፈልገው ጭብጥ የስር ፍ/ቤት መዝገቡን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 280 መሰረት መዝጋቱ እንዱሁም አመልካች መዝገቡ እንዱከፈት ሲጠይቁ ጥይቄአቸው ውድቅ መደረጉ ተገቢ መሆን አለመሆኑ ነው። ከፍ ሲል እንደተመለከትነው አመልካች ክስ አቅርበው ግራ ቀኙ መልስና የመልስ መልስ ተቀባብለው ጨርሰዋል። ተጠሪ ቀድሞ የቀረበው ክስ፣ መልስ፣ የመልስ መልስ እንደሁም ላልች ማስረጃዎች ደርሶት አስተያየት እንዱሰጥ የታዘዘው የቀድመውን ተከሳሽ ተክቶ በክሱ ውስጥ በመግባቱ ብቻ ነው። ፍ/ቤቱም መዝገቡን በዘጋበት እለት ለመዝገቡ ቀጠሮ ተሰጥቶ የነበረው አመልካች አቤቱታቸውን ከነአባሪዎቹ ለተጠሪ አድርሰው ተጠሪ የሚያቀርበውን አስተያየት ለመቀበል እንጂ ክስ ለመስማት አልነበረም። አመልካች በቀጠሮው እለት ባለመቅረባቸውም ፍ/ቤቱ መዝገቡን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 280 መሰረት መዝገቡን ዘግቷል ይህ የሥነሥርዓቱ ድንጋጌ የሚገኘው ክርክርን ስለማቋረጥ በሚናገረው ሥነ-ሥርዓት ህጉ ክፍል ውስጥ ነው። የተጠቀሰው ድንጋጌም ለክሱ ምክንያት የሆነው ነገር ተቋርጦ በሚቀርብበት ጊዜ ፍ/ቤቱ ስለሚወስደው እርምጃ የሚናገር ሲሆን የድንጋጌው ይዘትም፤
“ክሱ በሚቀጥልበት በማንኛውም ጊዜ ለክሱ ምክንያት የሆነው ነገር መቋረጡን ወይም ጨርሶ መቅረቱን ፍ/ቤቱ በቂ በሆነ ማስረጃ የተገነዘበ እንደሆነ ስለ ኪሳራና ስለ ካሳ ተገቢ የሆነውን ትእዛዝ በመስጠት ክሱን ይዘጋዋል። ምክንያቱንም ዘርዝሮ በመዝገቡ ላይ ያሰፍራል።” በሚል ይነበባል። ድንጋጌው ከሚገኝበት ክፍልና ከድንጋጌው ዝርዝር ይዘት በግልፅ መረዲት እንደሚቻለው ፍ/ቤቱ ክሱን የሚዘጋው የክሱ ምክንያት ሲቋረጥ ወይም ጨርሶ ሲቀር ነው። በተያዘው ጉዲይ ግን ፍ/ቤቱ መዝገቡን የዘጋው የክሱ ምክንያት በመቋረጡ ሳይሆን አመልካች በተከታታይ ቀጠሮ በመቅረታቸው በመሆኑ ፍ/ቤቱ የተጠቀሰውን የሥነ-ሥርዓት ድንጋጌ መሰረት አድርጎ መዝገቡን መዝጋቱ መሰረታዊ የህግ ስህተት ሆኖ አግኝተነዋል።
በልላ በኩል አመልካች መዝገቡ እንዱከፈትላቸው የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 71(2)“ን” መሰረት በማድረግ ለፍ/ቤቱ ጥያቄ አቅርበዋል። በዚህ ሥነ-ሥርዓት መሰረት መዝገብ እንደከፈት ጥያቄ ላቀርብ የሚችለው በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 69(2) ክስ በሚሰማበት ቀነ-ቀጠሮ ከሳሽና ተከሳሽ በመቅረታቸው ወይም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 70(መ) መሰረት ከሳሽ ለተከሳሽ መጥሪያ ሳያደርስ በመቅረቱ መዝገቡ ተዘግቶ ከነበረና ከሳሹ የቀረው ወይም ለተከሳሽ መጥሪያ ያልደረሰው በቂ ሆኖ በሚገመት ምክንያት መሆኑን በማስረዲት ነው። በተያዘው ጉዲይ የአመልካች የክስ መዝገብ የተዘጋው ክስ በሚሰማበት ቀነ-ቀጠሮ በመቅረታቸው ስላልሆነ መዝገቡ እንዱከፈት ይህን ሥነ-ሥርዓት መጥቀሳቸው ተገቢ አልነበረም። ነገር ግን አንድ ተከራካሪ ወገን ፍሬ ነገሩን ከገለፀ ትክክለኛውን የህግ ድንጋጌ አለመጥቀሱ መብቱን ሉያስቀርበት አይችልም።
No topics extracted.
ይልቁንም ፍ/ቤቶች ለቀረበላቸው ጥያቄ አግባብነት ያለውን ድንጋጌ መሰረት በማድረግ ተገቢ ነው ያለትን ውሳኔ የመስጠት ሃላፉነት አለባቸው። በዚህም ምክንያት ከፍ ሲል እንደተመለከትነው ፍ/ቤቱ አመልካች ባለመቅረባቸው መዝገቡን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 280 መሰረት መዝጋቱ ሥነ-ሥርዓታዊ ባለመሆኑ ምንም እንኳን አመልካች የጠቀሱት አንቀፅ ለጉዲዩ አግባብነት ባይኖረውም ተገቢውን ድንጋጌ በመጠቀም ስህተቱን ሉያርም ይገባው ነበር። በክርክሩ ውስጥ ከሥነ-ሥርዓት ውጪ የሆነው ጉዲይ ሲያጋጥም ማንኛውም ተከራካሪ ወገን በሚያቀርበው ጥያቄ ፍ/ቤቱ ከሥነ-ሥርዓት ውጪ የሆነው ነገር በሙለ ወይም በከፉል እንዱሰረዝ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 209 ስልጣን ይሰጠዋል። በተመሳሳይ ሁኔታ አመልካች ለስር ፍ/ቤት ባቀረቡት ማመልከቻ ከተጠሪ ጋር መልስና የመልስ መልስ ተሰጥቶበት ለውሳኔ ያደረ ጉዲይ መሆኑን በመግለፅ መዝገቡ እንዱከፈትላቸው በ21/4/2000 ዓ.ም ስለመጠየቃቸው የስር ፍ/ቤት መዝገብ ያመለክታል።
በመሆኑም ፍ/ቤቱ የአመልካች ክስ የክስ ምክንያቱ ሳይቋረጥ መዝገቡን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 280 መዝጋቱ ከሥነ-ሥርዓት ውጪ በመሆኑ አመልካች ባቀረቡት ጥያቄ መነሻነት ይህንን ስህተቱን በማረም መዝገቡን መክፈት ሲገባው አመልካች የጠቀሱትን የሥነ-ሥርዓት ድንጋጌ አግባብ አለመሆኑን ብቻ መሰረት በማድረግ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 280 መሰረት የተዘጋ መዝገብ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 71(2) መሰረት አይከፈትም በሚል ምክንያት ጥያቄውን ውድቅ ማድረጉ የሥነ-ሥርዓት ድንጋጌዎቹን በአግባብ ያላገናዘበና መሰረታዊ የሥነ-ሥርዓት ህግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ አግኝተነዋል። በመሆኑም ተከታዩን ውሳኔ ተሰጥቷል።
የፋ/መ/ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ ጥር 13 ቀን 2000 ዓ.ም የተሰጠው ትዕዛዝ እና የፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ ሚያዚያ 28 ቀን 2000 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ ተሽሯል።
አመልካች ክስ ያቀረቡበት መዝገብ ተከፍቶ ክርክሩ እንዱቀጥል ተወስኗል።
ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።