No summary available.
የሰ/መ/ ታህሳስ 8 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ሐጎስ ወልደ ሂሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ አልማው ወላ አመልካች፡- ሲ.ጂ.ሲ.ኦቨርሲስ ኮንስትራክሽን ኢትዮጵያ ሉሚትድ - እላኒ አስራት ቀረቡ ተጠሪ፡- ሰለሞን እንዲለ - አልቀረበም መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ለሰበር አቤቱታው መነሻ የሆነው ጉዲይ በላለሁበት ክርክሩ እንዱሰማ የተሰጠው ትዕዛዝ ተነስቶ ወደክርክሩ እንድገባ ይፈቀድልኝ በማለት አመልካች ያቀረበውን አቤቱታ የሚመለከት ነው። ከመዝገቡ እንደሚታየው አመልካች ክርክሩ በተጀመረበት የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ተከሣሽ የነበረ ሲሆን፣ መልስ እንዱሰጥ በተጠራበት ቀነቀጠሮ ባለመቅረቡ ክርክሩ እሱ በላለበት እንዱሰማ ታዟል። በልላ በኩል ደግሞ ትዕዛዙ እንዱነሳለት እና በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ.72 መሰረት ወደ ክርክሩ እንዱገባ እንዱፈቀድለት ጠይቆአል። ፍ/ቤቱም ጥያቄውን ከተመለከተ በኋላ፣ አቤቱታው ትዕዛዙ በተሰጠ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ያልቀረበ በመሆኑና የአንድ ወር ጊዜው ያለፈው በበቂ ምክንያት ለመሆኑ የቀረበ ማስረጃ ስለላለ ትዕዛዙ ሉነሳ አይችልም በማለት ብይን ሰጥቶአል። በዚህ ላይ ይግባኝ የቀረበለት የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤትም ትዕዛዙን አፅንቶአል። የሰበር አቤቱታው የቀረበው በዚህ ላይ ነው።
እኛም አመልካች የካቲት 16 ቀን 2001 ዓ.ም በጻፈው ማመልከቻ ያቀረበውን አቤቱታ መሰረት በማድረግ ተጠሪን አስቀርበን ክርክሩን ሰምተናል። በዚህ ረገድ ግራ ቀኝ ወገኖች ያሰሙትን ክርክርም አቤቱታ ከቀረበበት ውሳኔ እና ከሕጉ ጋር አገናዝበን መርምረናል።
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ. ጥቅምት 7 ቀን 2001 ዓ.ም በሰጠው ብይን እንደተመለከተው አመልካች ቀደም ሲል ተሰጥቶ የነበረው ትዕዛዝ ተነስቶለት ወደ ክርክሩ እንዱገባ ባመለከተበት ጊዜ በጉዲዩ ላይ ውሳኔ አልተሰጠም ነበር። ከመዝገቡ አጠቃላይ ይዘት መገንዘብ እንደቻልነው አመልካች ተከሣሽ የነበረ ሲሆን፣ በቀረበበት ክስ በጽሐፍ መልስ ሰጥቶ ነበር። ጉዲዩ ለቃል ክርክር በተቀጠረበት ዕለትም የአመልካቹ ሰራተኛ የሆነ ቀርቦ የነበረ ሲሆን፣ ፍ/ቤቱ ግን ክርክር ለማቅረብ የሚያስችል የውክልና ሥልጣን የለህም በማለት ክርክሩ አመልካቹ በላለበት እንዱታይ አዞአል። ከዚህ በኋላም ነው አመልካች ክርክሩ በላለበት ይሰማል የሚለው ትዕዛዝ ተነስቶለት ወደክርክሩ እንዱገባ የጠየቀው። ፍ/ቤቱ በዚህ መልክ የቀረበውን አቤቱታ ውድቅ ያደረገው ጥያቄው በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ.78(1) መሰረት በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ አልቀረበም። በህጉ ከተመለከተው የአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ለማቅረብ ያልቻለበት በቂ ምክንያት ያለው ለመሆኑም አላስረዲም የሚለትን ምክንያቶች በመስጠት ነው።
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ መሰረት የሚመራው የፍትሐብሕር ክስ በቀረበ ጊዜ ክርክሩን ለመስማት ፍ/ቤቱ በያዘው ቀነቀጠሮ ተከራካሪ ወገኖች ይቀርባለ ተብል እንደሚጠበቅ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ 69(1) ከተቀመጠው ድንጋጌ መገንዘብ ይቻላል። በልላ በኩል ደግሞ ሁለቱም ተከራካሪ ወገኖች ወይም አንዲቸው ሳይቀርቡ ቢቀሩ ሉወሰደ ስለሚገባቸው የሥነሥርዓት እርምጃዎች በሚመለከት ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ.69 እስከ 78 ድረስ ባለት ድንጋጌዎች በዝርዝር ተቀምጦአል።
በያዝነው ጉዲይ ክርክሩ እንዱሰማ ቀነ ቀጠሮ በተያዘበት ዕለት ሳይቀርብ የቀረው አመልካች (ተከሣሽ የነበረው) ነው። በዚህ ቀነ ቀጠሮ የአመልካች ወኪል ነኝ በማለት የቀረበው ሰራተኛ የተሟላ የውክልና ሥልጣን የለውም በሚል አመልካች እንዲልቀረበ ተቆጥሮ ክርክሩ አመልካች በላለበት እንዱታይ የመታዘዙን አግባብነት ወደኋላ የምንመለከተው ይሆናል።
ፍ/ቤቱ ይህን እምነት በመያዙና ክርክሩ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ. 70(ሀ) መሰረት አመልካች በላለበት እንዱሰማ ትዕዛዝ በመስጠቱ የተነሣ አመልካች ለጉዲዩ የመጨረሻ ውሳኔ ከመስጠቱ በፉት ያቀረበው አቤቱታ የሚስተናገደው በምን አግባብ ነው? የሚለውን ነጥብ በቅድሚያ እንመለከታለን።
በመጀመሪያው ቀነቀጠሮ ባለመቅረቡ ምክንያት ክርክሩ በላለበት እንዱሰማ ትዕዛዝ የተሰጠበት ተከሣሽ በሚቀጥለው ቀነቀጠሮ ቀርቦ በቀዲሚው ቀነቀጠሮ ለመቅረብ ያልቻለው በቂ ሆኖ በሚገመት እክል ምክንያት መሆኑን ያስረዲ እንደሆነና ፍ/ቤቱም ምክንያቱን በቂ አድርጎ የተቀበለው እንደሆነ በቀረበበት ቀን መከላከያውን አቅርቦ እንዱከራከር እንደሚፈቅድለት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ. 72 ተደንግጎአል። በዚህ ድንጋጌ የተቀመጡት ዋነኞቹ ነጥቦች አቤቱታው የሚቀርበው በሚቀጥለው ቀጠሮ ማለትም ጉዲዩ በውሳኔ ከመቋጨቱ በፉት መሆኑን እና በቀዲሚው ቀነ ቀጠሮ ላለመቅረብ በቂ ሆኖ የሚገመት ምክንያት (እክል) መኖር ናቸው። ከዚህ ውጪ ድንጋጌው አቤቱታው የሚቀርብበትን ግልጽ የሆነ የጊዜ ገደብ አላስቀመጠም። በዚህ ይዘቱም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ. 78(1) ከተደነገገው የሚለይ ነው። የኋለኛው “ተከሣሽ በላለበት የተሰጠውን ውሳኔ ስለማንሳት” የሚል ርእስ ያለው ሲሆን፣ የመጀመሪያው ግን “በሚቀጥለው ቀነቀጠሮ ስለመቅረብ” በሚል የተደነገገ ነው። ከዚህም በሁለቱ ድንጋጌዎች መካከል ያለውን ልዩነት ጉዲዩን በያዘው ፍ/ቤት የመጨረሻ ውሳኔ ከመስጠቱ በፉት እና ውሳኔ ከተሰጠ በኋላ በሚል ሉለይ እንደሚችል መገንዘብ ይቻላል።
No topics extracted.
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ. 72 እና 78 መካከል ያለው ልዩነት ይህን ያህል ግልጽ ከሆነ ደግሞ በመጀመሪያው ቀነ ቀጠሮ የቀረ ነገር ግን በሚቀጥለው ቀነ ቀጠሮ የቀረበው ተከሣሽ ጥያቄው ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ. 78(1) አኳያ የሚታይበት አግባብ የለም። በመሆኑም የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ቁ. 78(1)“ን” መሰረት በማድረግ ጉዲዩን ያየው በአግባቡ አይደለም።
በመቀጠል ያየነው አመልካች በአንድ ወር ውስጥ ቀርቦ ያላመለከተበትን ምክንያት አላስረዲም የሚለውን የፍ/ቤቱ ትችት ነው። ቀደም ሲል እንደገለጽነው አመልካች አቤቱታውን ለማቅረብ የቀናትም ይሁን የወራት ገደብ አልተቀመጠለትም። በመሆኑም እንዱያስረዲ የሚጠበቀው ክርክሩ ሉሰማ በተያዘው ቀነ ቀጠሮ ያልቀረበበትን ምክንያት ነው። ለክሱ መልስ በተሰጠበት ጊዜ በኋላ በቃል የመከራከር የተሟላ ውክልና የለህም የተባለው ሰራተኛው ከመቅረቡም በላይ፤ መልሱን እራሱ ፈርሞ እንዲቀረበው በክርክሩ ተመልክቶአል። ጉዲዩን ለመስማት (በቃል) ቀጠሮ በተያዘበት ዕለትም ይኸው ለመከራከር ይችላል ተብል ከአመልካች ውክልና የተሰጠው ሰራተኛ የቀረበ በመሆኑ ቢያንስ በኋላ ትዕዛዙ እንዱነሳለት ላቀረበው አቤቱታ አወሳሰን እንደበቂ ምክንያት ተደርጎ ሉወሰድለት ይገባ ነበር። ከሁለ በላይ ደግሞ አመልካች ያቀረበው በጽሐፍ የተዘጋጀው መልስ ከመዝገቡ የተያያዘ በመሆኑ ፍ/ቤቱ ከዚህ በመነሳት ወደፉት ያለውን ክርክሩ መሰማት ሲገባው ወደ ውሳኔ ማምራቱ ተገቢ ሆኖ አላገኘነውም። ስናጠቃልለው ፍ/ቤቱ ክርክሩን የመራው በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ. 72 የተቀመጠውን ድንጋጌ በአግባቡ ሳይጠቀም በመሆኑ አፈጻጸሙ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው ለማለት ችለናል።
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ. ጥቅምት 7 ቀን 2001 ዓ.ም የሰጠው ብይን እና የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ. የካቲት 2 ቀን 2001 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ 348(1) መሰረት ተሽረዋል።
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አመልካች ወደ ክርክሩ እንዱገባ በማድረግ ከገባበት ቀን ጀምሮ ወደፉት ያለውን ክርክሩን ከሰማ በኋላ ተገቢውን ይወስን ዘንድ ጉዲዩ ይመለስለት ብለናል።
በዚህ ሰበር ችልት በተደረገው ክርክር ግራ ቀኝ ወገኖች ወጪና ኪሣራቸውን ይቻቻለ ብለናል።
መዝገቡ ይመለስ።