No summary available.
ታህሳስ 15 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ሐጎስ ወልደ ሂሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ አልማው ወላ አመልካች፡- ወ/ሮ ኸይሮ መሐመድ - ጠበቃ አታክልት ሃ/ስላሴ ተጠሪ፡-
ይህ የሰበር አቤቱታ ላቀርብ የቻለው አመልካች በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ 358 መሰረት ለፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ያቀረቡት አቤቱታ ተቀባይነት ሳያገኝ በመቅረቱ ሲሆን የጉዲዩ አመጣጥም ባጭሩ ሲታይ በአንደኛ እና ሁለተኛ ተጠሪ መካከል የነበረው ጋብቻ በፍቺ እንዱፈርስ በፋዳራል መ/ደ/ፍ/ቤት ከተወሰነ በኋላ የንብረት ክፍፍለንም ፍ/ቤቱ ተመልክቶ በ8-2-2000 ዓ.ም ውሳኔ ሰጥቷል።
ከዚህ በኋላም የአሁን አመልካች በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ 358 መሰረት የካቲት 17 ቀን 2000 ዓ.ም ለፍ/ቤቱ ባቀረቡት አቤቱታ አመልካችና ተጠሪ የእኔን ሚስትነት ሰርዘው እኔ በማላውቀው ሁኔታ የባልና ሚስት ፍቺ አስወስነው የንብረት ክፍፍልም እንዱደረግ የተወሰነ ስለሆነ ይህ ውሳኔ የእኔን መብት የሚጏዲ ስለሆነ ይሰረዝልኝ በማለት ጠይቀዋል።
የፋዳራል መ/ደ/ፍ/ቤትም ግራ ቀኙን አከራክሮ የመቃወም አመልካች በተጠሪዎች መካከል የነበረው ክርክር በቀጠሮ ላይ እንዲለ ግንቦት 21 ቀን 1998 ዓ.ም የጣልቃገብነት አቤቱታ አቅርባ አመልካችና ተጠሪ (የአሁን ተጠሪዎች) መልስ እንዱሰጡበት ትዕዛዝ ተሰጥቶ ነገር ግን የመቃወም አመልካች ትዕዛዙን ባለማድረሳቸው ድጋሚ ትዕዛዝ ተሰጥቶ በድጋሚውም ትዕዛዝ መሰረት ባለመፈጸማቸው አቤቱታቸውን ባለመቀበል ክርክሩ እንዱቀጥል ተደርጓል።
በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ 358 መሰረት መቃወሚያ ላቀርብ የሚችለው ደግሞ ክርክር እየተደረገ መሆኑን ያልተገነዘበ ወገን በላለበት ክርክር ተደርጎ የተሰጠው ውሳኔ መብቱን የነካበት ሆኖ ሲገኝ ነው። ነገር ግን ክርክር መኖሩን የተገነዘበ ሰው ከበስተጀርባ ሆኖ የክርክሩን ሚዛን በመገምገም እርሱን በሚመለከት አጥጋቢ ፍርድ ባልተሰጠ ጊዜ ጉዲዩ እንደገና እንዱታይ አቤቱታ ማቅረብ ከሥነ-ሥርዓት ሕጉ ዓላማ አኳያ ተቀባይነት አይኖረውም። በዚህም ጉዲይ የመቃወም አመልካች የክርክሩ ተካፊይ ለመሆን አቤቱታ አቅርባ መጥሪያ እንድታደርስ ለሁለት ጊዜ ትዕዛዝ የተሰጠ ቢሆንም በትዕዛዙ መሰረት ሳትፈጽም ቀርታ ከውሳኔ በኋላ ወደ ክርክሩ ለመግባት አቤቱታ ማቅረቧ ክርክር መኖሩን እያወቀች ስለሆነ አቤቱታው በተገቢው አኳኋን አልቀረበም በማለት ሳይቀበለው ቀርቷል።
የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤትም ጉዲዩን በይግባኝ አይቶ መ/ሰጭዎችን ሳይጠራ መዝገቡን ዘግቷል።
የአሁን የሰበር አቤቱታ የቀረበውም በዚህ ውሳኔ ላይ ነው። ይህ ችልትም አቤቱታውን መርምሮ አመልካች በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ 358 መሰረት ያቀረቡት አቤቱታ በሥር ፍ/ቤቶች ተቀባይነት ሳያገኝ መቅረቱ ተገቢነቱን ለመመርመር አቤቱታው ለሰበር እንዱቀርብ አድርጓል።
የክርክሩ ይዘት ከፍ ብል የተመለከተው ሲሆን በበኩላችንም ጉዲዩን እንደሚከተለው መርምረነዋል።
በክርክሩ ውስጥ ተካፊይ መሆን የሚገባው ወይም በክርክሩ ውስጥ ለመግባት የሚችልና እንደዚሁም ተካፊይ ባልሆነበት ክርክር የተሰጠው ፍርድ መብቱን የሚነካበት ማንኛውም ሰው ተካፊይ ባልሆነበት ክርክር የተሰጠው ፍርድ ከመፈጸሙ በፉት መቃወሚያውን ለማቅረብ እንደሚችል በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ 358 ላይ ተመልክቷል።
መቃወሚያ ማቅረብ የሚፈቀድበት ደንብ መሰረታዊ ዓላማም ምንአልባት ፍርድ መስጠቱን ያላወቀና በተሰጠው ፍርድም ጥቅሙ የሚነካ ሰው ፍርደ ቢፈጸም በጥቅሙ ላይ ሉከተል የሚችለውን ጉዲት ለመከላከል ነው። አንድ ሰው በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ 358 መሰረት መቃወሚያ ለማቅረብ የሚችለውም በጉዲዩ የሚያገባውና በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ 41 መሰረት የክርክሩ ተሳታፉ ላሆን የሚችል ሆኖ በሚገኝበት ጊዜ ነው። አመልካችም በተጠሪዎች መካከል የነበረው ክርክር ስለሚመለከተኝ የክርክሩ ተሳታፉ መሆን ይገባኛል ብለው በፍ/ብ/ህ/ሥ/ሥ/ቁ 41 መሰረት በፋ/መ/ደ/ፍ/ቤት አቤቱታ አቅርበው ነበር። አቤቱታቸውም ተቀባይነት አግኝቶ ፍ/ቤቱ ክርክሩን አግድ የጣልቃገብነት ማመልከቻው ለተከራካሪ ወገኖች እንዱደርስና መልስ እንዱሰጡበት ከአንድም ሁለት ጊዜ ትዕዛዝ ሰጥቷል። የጣልቃገብነት አቤቱታ ለተከራካሪ ወገኖች ሳይደርስ የቀረው በአመልካቹ ጉድለት በሆነ ጊዜ ደግሞ ጣልቃገቡ ነገሩን ሆነ ብል እንደተወው ተቆጥሮ መብቱ እንደሚሰረዝበት በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ 41(4) ላይ ተመልክቷል።
No topics extracted.
ስለሆነም አመልካች በተጠሪዎች መካከል ክርክር እየተደረገ መሆኑን ተገንዝበው በክርክሩ ጣልቃ ለመግባት ጠይቀው ተፈቅድላቸው የጣልቃገብነት አቤቱታውን ለተከራካሪ ወገኖች ማድረስ ሲገባቸው ይህን ሳይፈጽሙ ቀርተው መብታቸው ከተሰረዘ በኋላ ፍ/ቤቱ በጉዲዩ ላይ ውሳኔ ከሰጠ በኋላ በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ 358 መሰረት መቃወሚያ ማቅረባቸው ክርክር መኖሩን በሚገባ በተገነዘቡበት ሁኔታ ስለሆነ በዚህ መልኩ የሚቀርብ አቤቱታ ከሕጉ ዓላማ ጋር ስለማይጣጣም የሥር ፍ/ቤቶች አቤቱታው ተቀባይነት የለውም በማለት የሰጡት ውሳኔ በአግባቡ እንጂ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ አላገኘነውም።
የፋዳራል መ/ደ/ፍ/ቤት በመ. በ20/8/2000 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ እንደዚሁም የፋዳራል ከ/ፍ/ቤት በመ. በ21/11/2000 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ በአግባቡ ስለሆነ አጽንተነዋል።
ግራ ቀኙ ወጭና ኪሳራ ይቻቻለ ብለናል።
መዝገቡ ተዘግቶ ወደ መ/ቤት ተመልሷል።