No summary available.
ታህሣሥ 06 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ሐጏስ ወልደ ሑሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ አልማው ወላ አመልካች፡- ንግድ ማተሚያ ድርጅት - ነ/ፈጅ ጌታቸው ብርሃኑ ተጠሪ፡- አቶ ካሱ ሙላት - ቀረቡ
በዚህ መዝገብ የተያዘው ጉዲይ የስራ ክርክርን የሚመለከት ነው። የአሁኑ ተጠሪ በፋ/መ/ደረጃ ፍ/ቤት ተጠሪ ያለ አግባብ ከስራ ያሰናበታቸው መሆኑን በመግለጽ ውዝፍ ደሞዝ ተከፍሎቸው ወደ ስራ እንዱመለሱ ጠይቀዋል። አመልካች ለቀረበው ክስ በሰጠው መልስ ተጠሪ ለ6 ተከታታይ ቀናት ከስራ በመቅረታቸው ከስራ እንደተሰናበቱ በመግለጽ ክሱ ውድቅ እንዱሆንለት አመልክቷል። ፍ/ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ መርምሮ ተጠሪ ከስራ ታመው የቀሩ መሆኑን ቢገልፁም ታመው ስለመቅረታቸው ማስረጃ እንዱያቀረቡ በዱሲፔሉን ኮሚቴ ተጠይቀው ማቅረብ አልቻለም፣ ያቀረቡት የሕክምና ማስረጃ በወቅቱ ያልቀረበና ከስራ ከተሰናበቱ በኋላ የተፃፈ ስለሆነ ከስራ የተሰናበቱት በአግባቡ ነው በማለት ውሳኔ ሰጥቷል። ተጠሪ በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኛቸውን ለፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት አቅርበው ፍ/ቤቱ ተጠሪ ከስራ ስለመቅረታቸው ለማስረዲት የቀረበው አንደኛው ማስረጃ ከጉዲዩ ጋር አግባብነት የላለው የትርፍ ሰአት ክፍያ የሚመለከት ነው። ሁለተኛው ማስረጃ የዱሲýሉን ኮሚቴ ቃለ-ጉባኤ ሲሆን አንድ ሰራተኛ ቀሪ መሆኑን ለማስረዲት ላቀርብ የሚገባው የሰነድ ማስረጃ እንጂ የዱሲýሉን ኮሚቴ ቃለ-ጉባኤ ስላልሆነ ተጠሪ ከስራ ስለመቅረታቸው በማስረጃ አልተረጋገጠም በማለት የስር ፍ/ቤትን ውሳኔ በመሻር ተጠሪ የ6 ወር ደሞዝ ተከፍሎቸው ወደ ስራ እንዱመለሱ ወስኗል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሳኔ ላይ ነው። ይህ ችልትም ተጠሪ ከስራ የተሰናበቱት በህገ-ወጥ መንገድ ነው በሚል የተሰጠውን ውሳኔ አግባብነት ለመመርመር አቤቱታው ለሰበር ችልት ላቀርብ ይገባል በማለቱ ግራ ቀኙ ክርክራቸውን በጽሁፍ አቅርበዋል። መዝገቡም እንደሚከተለው ተመርምሯል።
ተጠሪ በስር ክሳቸው በህመም ምክንያት ከስራ በመቅረታቸው አመልካች ያለአግባብ ከስራ ያሰናበታቸው መሆኑን ገልፀዋል። አመልካች በበኩለ ከስራ የተሰናበቱት ለ6 ተከታታይ ቀናት ከስራ ስለቀሩ መሆኑን ተከራክሯል። ከክርክሩ ሂደት እደተረዲነው ተጠሪ ከስራ መቅረታቸውን አልካደም። ክርክራቸው የቀሩት በህመም ምክንያት ነው የሚል ነው። ከስር ፍ/ቤት መዝገብ ግልባጭ በህመም ምክንያት ከስራ ለመቅረታቸው ለዱሲፔሉን ኮሚቴ ማስረጃ እንዱያቀርቡ ተጠይቀው ማቅረብ አለመቻላቸውን ተረድተናል። የፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤትም ቢሆን ተጠሪ ማስረጃቸውን ለዱሲፔሉን ኮሚቴ አቅርበዋል አላለም።
ለውሳኔው መሰረት ያደረገው የአንድን ሰራተኛ ከስራ መቅረት ማስረዲት የሚቻለው በሰነድ ማስረጃ እንጂ በዱሲፔሉን ኮሚቴ ቃለ-ጉባኤ አይደለም የሚል ነው። በመሰረቱ ተጠሪ ከስራ ስለመቅረታቸው ክደው አልተከራከሩም። የሚከራከሩት ከስራ የቀሩት በህመም መክንያት መሆኑን ነው። በመሆኑም በህመም ምክንያት ስለመቅረታቸው የማስረዲት ሸክም ያለባቸው ተጠሪው ናቸው። ተጠሪ በዱሲፔሉን ኮሚቴ ማስረጃ እንዱያቀርቡ ሲጠየቁ ማቅረብ አለመቻላቸው በስር ፍ/ቤት የተረጋገጠ ፍሬ ነገር ነው። ከዛ በኋላ ደግሞ ያቀረቡት ማስረጃ ከስራ ከተሰናበቱ በኋላ የተፃፈና እጅግ ዘግይቶ የቀረበ ማስረጃ ነው። በልላ በኩል አንድ ፍሬ ነገር ለማስረዲት ተለይቶ የተመለከተ ማስረጃ እንዱቀርብ ህጉ ካላስገደደ በቀር ይህን ፍሬ ነገር በማንኛውም የማስረጃ አይነት ከማስረዲት የሚከለክል ሕግ የለም። የይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት ተጠሪ ከስራ ስለመቅረታቸው የዱሲፔሉን ኮሚቴ ቃለ ጉባኤ በማስረጃነት ላቀርብ የማይገባበትን የሕግ መሰረት አልገለፀም። ቢያንስ ማስረጃንውን መዝኖ ተጠሪ ከስራ ስለመቅረታቸው በበቂ ሁኔታ ማስረዲት የሚችል መሆን አለመሆኑን ሉመዝን ይገባ ነበር። በመሆኑም በማስረጃነት ላቀርብ የማይችልበትን ምክንያት ሳይገልጽ በድፍኑ ቃለ-ጉባኤው ላቀርብ የማይችል ማስረጃ ነው በሚል ውድቅ ማድረጉ መሰረታዊ ሕግ ስህተት ሆኖ አግኝተነዋል። በመሆኑም ተጠሪ ከስራ የቀሩት በህመም ምክንያት መሆኑን ቢገልፁም ይህን ሳያስረደ ስንብቱ ህገ-ወጥ ነው በሚል የተሰጠው ውሳኔ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው።
የፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 79174 ሰኔ 12 ቀን 2001 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ ተሽሯል።
የፋ/መ/ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 27244 መጋቢት 14 ቀን 2001 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ ፀንቷል።
No topics extracted.
ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።