No summary available.
የሰ/መ/ ህዲር 30 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ሐጎስ ወልደ ሂሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ አልማው ወላ አመልካች፡- የኢትዮጵያ ልማት ባንክ - ነ/ፈጅ አሰገደች ጎርፋ ተጠሪ፡- ሰላም የቴክኒክና የሙያ ማሰልጠኛ ማዕከል - አልቀረበም
በዚህ መዝገብ የቀረበው ጉዲይ የስነ-ስርዓት ህግን የሚመለከት ነው። አመልካች የፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት በሰጠው ውሳኔ ላይ ለፋ/ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ አቅርቦ የግራ ቀኙ ክርክር በሚሰማበት ቀነ-ቀጠሮ አመልካች ባለመቅረቡና ተጠሪ ቀርበው መዝገቡ እንዱዘጋ በመጠየቃቸው ፍ/ቤቱ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 69(2) መሰረት መዝገቡን ዘግቶታል። ከዚህ በኋላ አመልካች ለፍ/ቤቱ በታህሣሥ 14 ቀን 2001 ዓ.ም በተፃፈ ማመልከቻ መዝገቡ እንደገና እንዱከፈትለት የቃል ክርክር በሚሰማበት ቀነ-ቀጠሮ ያልቀረበበት ምክንያት በቂ ባለመሆኑ መዝገቡ ሉከፈት አይገባም በማለት ጥያቄውን ውድቅ አድርጎታል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ትዕዛዞች ላይ ነው። አመልካች በቅሬታው የቃል ክርክር በሚሰማበት ቀነ-ቀጠሮ አመልካች ሳይቀርብ ተጠሪ ከቀረበ መዝገቡ ሉዘጋ የሚገባው በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 73 መሰረት እንጂ በቁጥር 62(2) አይደለም፣ በቀነ-ቀጠሮው የቀረንበት ምክንያትም የብሓር ብሓረሰቦች በዓል የሚከበርበት ቀን ስለነበር መንገድ በመዘጋጋቱ አርፍደን ስለደረስን ስለሆነ መዝገቡ እንዱከፈት ይወሰንልን በማለት ጠይቋል። አቤቱታውም ለሰበር ችልት ያስቀርባል በመባለ ግራ ቀኙ ክርክራቸውን በፁሁፍ አቀርበዋል። መዝገቡም እንደሚከተለው ተመርምሯል።
አመልካች ቃል ክርክር በሚሰማበት ቀነ-ቀጠሮ ሳይቀርብ ተጠሪ መቅረቡ አልተካደም። የባለጉዲዮች ወደ ፍ/ቤት መቅረብና አለመቅረብ የሚያስከትለውን ውጤት ምን እንደሆነ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕጉ ከቁጥር 65 እና ተከታዮች ባለት ድንጋጌዎች ተዘርዝረው ተቀምጠዋል። በዚህ መሰረት ክስ ያቀረበ ሰው ክርክሩ በሚሰማበት ቀነ-ቀጠሮ ሳይቀርብ ተከሳሹ ቀርቦ ክሱን በከፉል ወይም በሙለ ያመነ ከሆነ ላመነው ጉዲይ ፍ/ቤቱ ውሳኔ ለመስጠት እንደሚችልና ከካደ ደግሞ መዝገቡ እንደሚዘጋ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 73 ያመለክታል። በዚህ አንቀፅ ከሳሽና ተከሳሽ የሚለው አነጋገር ይግባኝ ባይ መልስ ሰጪ እንደሚጨምር ከሥነ-ሥርዓቱ ድንጋጌ አንቀጽ 32(2) ሥር መመልከት ይቻላል። በልላ በኩል የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 69(2) አግባብነት የሚኖረው ክርክር በሚሰማበት ቀነ-ቀጠሮ ሁለቱም ተከራካሪዎች ያልቀረቡ ከሆነ ነው። በተያዘው ጉዲይ ክርክር በሚሰማበት ቀነ-ቀጠሮ ይግባኝ ባይ የነበረው አመልካች ሳይቀርብ ተጠሪ ቀርቧል። በዚህም ምክንያት አግባብነበት የሚኖረው የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 73 እንጂ ቁጥር 69(2) አይደለም። በመሆኑም ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 69(2)“ን” መሰረት አድርጎ መዝገቡን መዝጋቱ ተገቢ አለመሆኑን ተገንዝበናል። ነገር ግን ተጠሪ ከስር ፍ/ቤት ጀምሮ ከአመልካች ጋር ሲከራከር የነበረ በመሆኑና ክርክር በሚሰማበት እለት አመልካች ባለመቅረቡ ተጠሪ መዝገቡ እንዱዘጋለት መጠየቁ ተጠቃል ሲታይ አቤቱታውን ያላመነ መሆኑን ያመለክታል። በልላ በኩል አመልካች በቀነ-ቀጠሮው ያልቀረበው በበቂ ምክንያት ነው ቢልም ፍ/ቤቱ ምክንያቱን መዝኖ በቂ አይደለም የሚለው መደምደሚያ ላይ ደርሷል። የምክንያቱ በቂ መሆን አለመሆን ደግሞ የማስረጃ ምዘና እንጂ የህግ ክርክር ባለመሆኑ ለሰበር አቤቱታ የሚቀርብበት ነጥብ ነው ልባል አይችልም። በአጠቃላይ ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት መዝገቡን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 73 መሰረት መዝጋት ሲገባው በቁጥር 69(2) መሰረት መዝጋቱ ትክክል ባይሆንም መዝገቡ በመዘጋቱ ግን መሰረታዊ የህግ ስህተት ፈፅሟል ማለት አልተቻለም።
የፋ/ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ/ ህዲር 30 ቀን 2001 ዓ.ም እና ጥር 18 ቀን 2001 ዓ.ም የሰጣቸው ትዕዛዞች ፀንተዋል።
ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የቻቻለ።
No topics extracted.