No summary available.
ጥቅምት 10 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ሐጏስ ወልደ ሂሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ አልማው ወላ አመልካች፡- የኢትዮጵያ መንገድች ባለሥልጣን ተጠሪ፡- እነ አቶ መስፍን ጀምበሩ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ የንብረት ግምት ይከፈለን ጥያቄ ሲሆን፤ ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ ተጠሪዎች አመልካች ከቡታጅራ ሆሣእና በሚያሰራው መንገድ ምክንያት በሆሣእና ከተማ የሚገኙ ንብረቶቻቸው እንዱነሱ የግምት ስራ ተሰርቶላቸው በዚሁ መጀመሪያ ግምት የከተማው አስተዲደር ንብረቶቻቸውን ያስነሳቸው መሆኑን፣የንብረቶቻቸው ዓይነትና ግምት ምን ያህል እንደሆነ ዘርዝረው አመልካች ካሣ እንዱከፈለን ይወሰንልን በማለት ዲኝነት ጠይቀው በአሁኑ አመልካች ላይ በሐድያ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመሰረቱት የተናጠል ክስ ሲሆን የአሁኑ አመልካችም በተከሣሽነቱ ቀርቦ ለመንገድ ሥራው የዱዛይን ለውጥ ማድረጉንና በተለወጠው ዱዛይን መሰረትም ንብረቶቹ መነሳት የማያስፈልጋቸው በመሆኑ ኃላፉነት እንደላለበት፣ተነሱ ወይም እንዱፈርሱ የተደረጉ ንብረቶች በአዋጅ ቁጥር 455/97 አንቀጽ 3/1/ እና 4/1/ ድንጋጌዎች ስር የተመለከተውን ሥርአት ባልተከተለ መልኩ የተከናወነ በመሆኑ ሉጠየቅ የማይገባ መሆኑን፣እንዱሁም አዋጁን ባልተከተለ መንገድ የራሱን ሥራ ለመስራት ንብረቶችን አስነሳ የተባለው የሆሳእና ከተማ አስተዲደር በክርክሩ ጣልቃ ገብቶ እንዱከራከር ይታዘዝለት ዘንድ በመግለጽ ተከራክሯል። የስር ፍርድ ቤትም የተጠሪዎችን ክርክርና የተለያዩ መዛግብት መርምሮ የሆሳእና ከተማ አስተዲድር ወደ ክርክሩ ይግባልኝ የሚለውን የአመልካችን አቤቱታ ውድቅ አድርጏ አመልካች ካሣ የመክፈል ኃላፉነት ያለበት መሆኑን በመግለጽ ተጠሪዎች በጠየቁት ዲኝነት መሰረት ወስኖላቸዋል። በዚህ ውሣኔ አመልካች ባለመስማማት ይግባኙን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርቦ ይኸው ፍርድ ቤትም ግራ ቀኙን ካራከረ በኋላ መዛግብትን በአንድ ላይ በማጣመር መርምሮ የስር ፍርድ ቤትን ውሣኔ ሙለ በሙለ አጽንቶታል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይሁንኑ የስር ፍርድ ቤቶችን ውሣኔ ለማስቀየር ነው።
የአመልካች ነገረ-ፈጅ የካቲት 06 ቀን 2001 ዓ.ም በፃፈት 3(ሦስት) ገጽ የሰበር አቤቱታ በስር ፍርድ ቤቶች ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል የሚለበትን ምክንያት ዘርዝረው አቅርበዋል። ይዘቱም ባጭሩ፡በመጀመሪያ መንገደ ሉሰራበት በታሰበው ስፊት መሰረት የተሰራው ግምት እጅግ የተጋነነ በመሆኑ ተቀባይነት እንደላለው ለከተማ አስተዲደሩ አመልካች ከገለጸለት በኋላ አስተዲደሩም ይህንን አውቆ የዱዛይን ክለሳ እና በዚህም መሰረት የግምት ስራ ከተጠናቀቀ በኋላ በቀድሞው ዱዛይን መሰረት ተነስቷል ለሚባል ንብረት ቦታው ለሕዝብ ጥቅም ባልዋለበትና በሕጉ አግባብ ላልተነሳ ንብረት ካሣ ለመክፈል ሕጋዊ ግዳታ የላለበት መሆኑን በመዘርዘር የስር ፍርድ ቤቶች ውሣኔ ሙለ በሙለ እንዱሻር ዲኝነት መጠየቁን የሚሣይ ነው። አቤቱታው ተመርምሮም በሰበር ችልቱ ላታይ ይገባዋል በመባለ ተጠሪዎች ቀርበው መጋቢት 09 ቀን 2001 ዓ.ም በዋለው ችልት የግራ ቀኙ የቃል ክርክር ተሰምቷል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሣኔና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
እንደመረመረውም አመልካች የሆሳእና ከተማ አስተዲደር ወደ ክርክሩ ጣልቃ እንዱገባ ያቀረበው ጥያቄ መታለፈ ባግባቡ ነው ወይስ አይደለም? የሚለው ነጥብ በጭብጥነት ላታይ የሚገባው ሆኖ አግኝቶታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው አመልካች በመጀመሪያ መንገደ ሉሰራበት በታሰበው ስፊት መሰረት የተሰራው የንብረቶች ግምት ባልተለመደ ሁኔታ እጅግ የተጋነነ በመሆኑ እንደማይቀበለው ለከተማ አስተዲደሩ ገልጾና አሳውቆ የዱዛይን ክለሳና የግምት ስራ ተጠናቅቆ ከአለቀ በኋላ ንብረቶቹ እንዱነሱ ወይም እንዱፈርሱ ለተደረገው ሁኔታ አመልካች ኃላፉነት እንደላለበትና ይህንን ድርጊት የከተማው አስተዲደር ለራሱ ሥራ ሲል ስለአከናወነው ኃላፉነት ሉወሰድ ስለሚገባ ወደ ክርክሩ ጣልቃ እንዱገባ ሉታዘዝ ይገባል በማለት የሥነ-ሥርአት ጥያቄ ማንሳቱን ነው። ይህ የአመልካች ጥያቄ የስር ፍርድ ቤቶች ተቀባይነት ሳያገኝ የቀረበው የተጠሪዎች አመልካች የመንገደን ስፊት በመቀነስ ዱዛይኑን ስለማስተካከለ ለማወቃቸው ወይም የከተማው አስተዲደር ንብረታቸውን ያፈረሰው አዱስ በተስተካከለው ዱዛይን ለመሆኑ አመልካች ያቀረበው ማስረጃ የለም፣አስተዲደሩ እውነታውን እያወቀ አፍርሶ ከሆነ አመልካች ከሦስተኛ ወገን ጋር በሚያደርገው ክርክር ተጠሪዎች መጏዲት የለባቸውም፣አመልካች በውል ወይም በሕግ ከአስተዲደሩ ጋር ግንኙነት ወይም ስምምነት ካለው ከሶ ማስከበር ከሚችል በስተቀር ተጠሪዎችን ሉጏዲ አይገባም በሚል ምክንያት ነው።
በመሰረቱ በአንድ ጉዲይ ላይ ክስ ሲቀርብና የክሱም ምክንያት የብዙ ሰዎችን መብትና ጥቅም የሚነካ ሆኖ ከእነሱ አንደ ወይም ከፉለ ክስ በቀረበ ጊዜ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ በጉዲዩ ላይ በሚሰጠው ውሳኔ ወይም ፍርድ መብትና ጥቅም የሚነካ ሲሆን በክሱ ውስጥ ተካፊይ ያልሆኑ ሰዎች የክርክሩ ተካፊይ እንዱሆኑ ፍርድ ቤቱ ትእዛዝ መስጠት ያለበት ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 39/1/ እና 40/2/ ድንጋጌዎች ይዘት ያስገነዝባል። እነዚህ ወገኖች ተካፊይ ሳይሆኑ የሚሰጠው ውሣኔ ወይም ፍርድ ውጤት የማይኖረው ስለመሆኑም የተጠቃሽ ድንጋጌዎች መንፈስ ያስረዲል። በመሆኑም በክሱ መግባት ያለበት ተከሣሽ የሆነ እንደሆነ ፍርድ ቤቱ የክርክር ተካፊይ እንዱሆንና በቀረበው ክስ የመልስ መከላከያውን እንዱያቀርብ ሉያዘው የግድ የሚል ስለመሆኑ ሥነ ሥርአቱ ያሳያል። በክርክሩ ውስጥ የግድ ተካፊይ መሆን የሚገባቸው ወገኖች ማለት ደግሞ ክስ በቀረበበት ጉዲይ ላይ በሚሰጠው ውሳኔ ጥቅማቸው፣መብታቸው ወይም ግዳታቸው የሚነካ፣በክርክሩ ውስጥ ተካፊይ ያልሆኑ ሰዎች ስለመሆናቸውም ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 40 ድንጋጌ ይዘት የምንገነዘበው ጉዲይ ነው።
በተያዘው ጉዲይም የሆሳእና ከተማ አስተዲደር ከተማውን የማስተዲደር ኃላፉነትና ተግባር ያለበት ሲሆን በከተማው ውስጥ በሚካሄደው የልማት እንቅስቃሴ ቀጥተኛ የሆነ ተሳታፉነት፣ቁጥጥር የማድርግ እና ላልች ተዛማጅ ተግባራትን እንደሚያከናውን የሚታመን ነው። በተለይም በሚያስተዲድረው ከተማ በአመልካች የሚሰራው ዓይነት ሥራ ሲሰራ በመንገደ ስራ ለሚነሱም ሆነ ለሚፈርሱ ንብረቶች ተገቢው ካሣ የሚከፈልበትን ሁኔታ በግምት ወቅትም ሆነ በአከፊፈለ ጊዜ ተሣታፉነት ያለበት ስለመሆኑ በዚህ ረግድ የተደነገጉት ሕጏች ያሳያለ። በሕጏቹ የተጣለበትን ግዳታዎችን መወጣት ደግሞ የግድ ይሎል። አመልካች ለሆሳእና ከተማ አስተዲደር የተጠሪዎች ንብረቶች ሉነሱ ወይም ሉፈርሱ የማይገባ መሆኑን ከዱዛይን ክለሳ በኋላ ማሳወቁን ገልጾ ተከራክሯል። እንዱህ ከሆነም ደግሞ ንብረቶቹ የተነሱት ወይም የፈረሱት በመንገድ ስራ ምክንያት መሆን አለመሆኑን፣ኃላፉነቱ የየትኛው ወገን እንደሆነ አከራካሪ የሚያደርገውና የከተማ አስተዲደሩን ወደ ክርክሩ እንዱገባ የግድ የሚል ጉዲይ ነው። ለክርክር ማስረጃ የማቅረብ ጉዲይ ደግሞ ይኸው ሥነ-ሥርአት ከተከናወነ በኋላ የሚከተል ጉዲይ ነው። የስር ፍርድ ቤቶች ተገቢ ባልሆነ የክርክር ደረጃ አመልካች ማስረጃ አላቀረበም በሚል ምክንያት የከተማው አስተዲደር ወደ ክርክሩ ይግባልኝ የሚለውን የአመልካች ጥያቄ ውድቅ ማድረጋቸው ተገቢ ነው ለማለት አልተቻለም። ስለሆነም የሆሳእና ከተማ አስተዲደር ወደ ክርክሩ ሳይገባ የተሰጠው ውሣኔ ሥነ-ሥርአታዊ ባለመሆኑ ተቀባይነት ሉሰጠው የሚገባ ሆኖ አልተገኘም። በዚህም ምክንያት በጉዲይ ላይ የተሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሉታረም የሚገባው ነው።
ው ሣ ኔ
በሐድያ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ. 03332፣03388፣02797 ተሰጥቶ በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት መ/ ተከፍቶና በመዝገብ ተጣምሮ ታይቶ ጥር 19 ቀን 2001 ዓ.ም የፀናው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ሙለ በሙለ ተሽሯል።
የሆሳእና ከተማ አስተዲደር በክርክሩ ውስጥ የግድ ተካፊይ መሆን ያለበት ወገን በመሆኑ ለቀረበው ክስና መልስ መከላከያውን እንዱያቀርብ የሐድያ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ትእዛዝ ሰጥቶ ጉዲዩን እንደገና በመመልከት ተገቢውን ውሣኔ እንዱሰጥበት ዘንድ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 343/1/ መሰረት መልሰንለታል።
ለክርክር የወጣን ወጪና ኪሳራ የየራሣቸውን ይቻለ ብለናል።
መዝገቡ ተዘግቷል፤ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.