No summary available.
ሐምል 8 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ሒጏስ ወልደ ኂሩት መለሰ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- የቅድሰተ ማሪያም አፀደ ሕፃናትና የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት - የቀረበ የለም ተጠሪ፡- መ/ት ሲሳይ ሙለጌታ - የቀረበ የለም መዝገቡን መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል።
በዚህ መዝገብ የቀረበው ጉዲይ የሥራ ውል ማቋረጥን የሚመለከት ነው። ሥር ፍ/ቤት ተጠሪ ከሳሽ አመልካች ተከሳሽ ሆነው ተከራክረዋል። የተጠሪ የክስ ምክንያት አመልካች ያለአግባብ የሥራ ውል አቋርጦብኛል ተገቢው ካሣና ጥቅማጥቅም ይክፈለኝ የሚል ነው። አመልካች በበኩለ ተጠሪ የክረምት ሥራ እንድትሰራ መመሪያ ተሰጥቷት እያለ ያለፈቃድ ወይም በቂ ምክንያት ከሐምል 11 ቀን 2000 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ነሐሴ 5 ቀን 2000 ዓ.ም ሥራ ላይ ባለመገኘቷ የሥራ ውል የተቋረጠው በአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 27/1//ለ/ መሰረት ነው ሲል ስንብቱ ሕጋዊ ስለመሆኑ ተከራክሯል። ጉዲዩ በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው የፋዳራል የመ/ደረጃ ፍ/ቤት የግራ ቀኙን ክርክር እና ማስረጃ ከመረመረ በኋላ ተጠሪ ጊዜው የመምህራን የዓመት እረፍት ጊዜ ነው በማለት ከሥራ መቅረቷን የተቀበለች ቢሆንም መምህራን በክረምት ወራት ሙለ ለሙለ እረፍት ስለመሆናቸው በአዋጅ፣በደንብ ወይም በመመሪያ የተደነገገ የለም፣አሰሪ ስራ እንዱሰራ መመሪያ ከሰጠ መሥራት ይጠበቅበታል በሚለ ምክንያቶች የተጠሪ የሥራ ውል የተቋረጠው በአግባቡ ነው ሲል ወስኗል። ተጠሪ በውሳኔው ቅር በመሰኘት ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ አቅርባለች።
ከፍተኛው ፍ/ቤትም ግራ ቀኙን አስቀርቦ ካከራከረ በኋላ መምህራን በክረምት ወራት እረፍት እንደሚያደርጉ ሲሰራበት የቆየ ልምድ ነው በዚህ መዝገብም የቀረቡት ማስረጃዎች ይህንኑ ያረጋግጣለ ተጠሪም በእረፍት ወቅት ሥራ ላይ አለመገኘታቸው የሥራ ውል ለማቋረጥ በቂ ምክንያት ላሆን አይገባም የሚለ ምክንያቶችን በመዘርዘር የሥራ ውል ያለአግባብ ተቋርጧል በማለት የሥር ፍ/ቤት ውሳኔ በመሻር ለተጠሪ የካሣ፣የማስጠንቀቂያ ጊዜ እና ክፍያ የዘገየበት ጊዜ እንዱከፈል ወስኗል።
ለዚህ ሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚሁ ላይ ነው። የአመልካች የሰበር አቤቱታ ይዘት ባጭሩ የሰራተኛ የዓመት እረፍት በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ በተደነገገው አግባብ በአሰሪና ሰራተኛ ስምምነት የሚወሰን እንጅ ሰራተኛው በዘፈቀደ የሚወስነው አይደለም፣በት/ቤቱ ደንብ መሰረት የዓመት እረፍቷን በነሐሴ ወር ወስዲለች እንዱሁም የ2000 ዓ.ም የዓመት እረፍት በገንዘብ ተለውጦ ተከፍሎል በሚለ ምክንያቶችን በመጥቀስ የሥር ከፍተኛው ፍ/ቤት ውሳኔ እንዱታረም አመልክቷል።
ሰበር ችልቱም የአመልካችን አቤቱታ ከአዋጅ አንቀጽ 13/1/ አንፃር ለመመርመር ተጠሪን አስቀርቧል። ተጠሪም ሐምል 21 ቀን 2001 ዓ.ም የተፃፈ መልስ አቅርባለች በይዘቱም የሥር ፍ/ቤት ክርክር በማጠናከር የክረምት ወራት ለመምህራን በተለየ ሁኔታ የእረፍት ጊዜ እንደመሆኑ በዚህ ጊዜ ውስጥ ለመሥራት ግዳታ የለብኝም በማለት የሥር ፍ/ቤት ውሳኔ እንዱፀና ጠይቃለች፡ የጉዲዩ አመጣጥ እና የግራ ቀኙ ክርክር ከፍ ሲል በአጭሩ ለማየት የተቻለው ሲሆን እኛም ከተያዘው ጭብጥ አንፃር ጉዲዩን ከሕጉ አገናዝበን መርምረናል። አመልካች አጥብቆ የተከራከረው ተጠሪ በክረምት ወቅት እንድታስተምር መመሪያ ተሰጥቷት ፈቃደኛ ሳትሆን ቀርታለች በሚል ነው። በዚህ ረገድ ከመዝገቡ መረዲት የተቻለው የክረምት ትምህርት ለመስጠት አመልካች ከተወሰኑ መምህራን ጋር ውይይት በማድረግ በስምምነት የማስተማር ሥራ ሲያከናውኑ እንደነበር ተመልክቷል። ይህውም ሐምል 4 ቀን 2000 ዓ.ም በተደረገ ስብሰባ የተወሰነ ስለመሆኑ ተገልጧል። ስለሆነም በዚህ መልክ ተጠሪ ፈቅዲ ግዳታ የገባች ስለመሆኑ በዚሁ ክርክር የተረጋገጠ ፍሬ ነገር አላገኘንም። ከዚህም ላላ ተጠሪን የሚያስገድድ ግልጽ መመሪያ ወይም ደንብ ስለመኖሩ አመልካች አላስረዲም።
ስለሆነም ግልጽ ደንብ ወይም መመሪያ መኖሩ ባልተረጋገጠበት ሁኔታ ተጠሪ በክረምት ወቅት ሥራ ለመሥራት ፈቃደኛ አልሆነችም ተብል የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 13/1/ የተመለከተውን ግዳታ ጥሳለች ለማለት የሚቻል ሆኖ አላገኘንም።
ስለሆነም በሥር ፍ/ቤት የተሰጠው ፍርድ በፍሬ ነገርም ሆነ በሕግ ረገድ መሰረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈፀመበት ነው ለማለት አልተቻለም።
በዚሁ ምክንያት ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 04326 በ01/07/2001 ዓ.ም የሰጠው ፍርድ ፀንቷል።
በዚህ መዝገብ ሚያዝያ 14 ቀን 2001 ዓ.ም የተሰጠው የእግድ ትእዛዝ ተነስቷል። ይፃፍ።
No topics extracted.