No summary available.
ሐምል 16 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ሐጎስ ወልደ ሂሩት መለሰ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- እነ ወ/ሮ ሙለ ታደሰ - ቀረቡ ተጠሪ፡- አለሙ መራ ኮንስትራክሽንና ጠቅላላ ብረታ ብረት ስራ ድርጅት
የአንደኛ አመልካች ባለቤትና የቀሪዎቹ አመልካቾች አባት በተጠሪ ድርጅት ሲሰሩ ከዚህ አለም በሞት ስለተለዩ የስንብት ክፍያና የአመት እረፍት በገንዘብ ተቀይሮ እንዱከፈላቸው ያቀረቡት ጥያቄ ውድቅ ስለተደረገባቸው የቀረበ የሰበር አቤቱታ ነው።
አመልካቾች በፋ/መ/ደረጃ ፍ/ቤት የአንደኛ አመልካች ባለቤትና የቀሪዎቹ አመልካቾች አባት በተጠሪ ድርጅት ከ1984 ዓ.ም ጀምሮ በዘበኛነት ተቀጥረው ሲሰሩ የካቲት 21 ቀን 2000 ዓ.ም ከዚህ አለም በሞት በመለየታቸው የሚገባቸው የአገልግልት ክፍያና የአመት እረፍት በገንዘብ ተቀይሮ እንዱሰጣቸው ጠይቀዋል። የተጠሪ ድርጅት ባለቤት ቀርበው በሰጡት መልስ የጋራዥ ስራውን መስራት ባለመቻላቸው ለላላ ሰው በኮንትራት የሰጡ መሆኑንና ሟች ከሳቸው ጋር ያለውን ስራ ውል ከሰኔ 1 ቀን 1994 ዓ.ም ጀምሮ ተቋርጦ ስራውን በኮንትራት ከያዘው ሰው ጋር ተዋውለው ይሰሩ ስለነበር ጥያቄው ተቀባይነት የላለው መሆኑን በመግለፅ ተከራክረዋል። ፍ/ቤቱም የአንደኛ አመልካች ባለቤትና የቀሪዎቹ አመልካቾች አባት የስራ ውል የተቋረጠው በሞት ምክንያት በመሆኑና በዚህ ሁኔታ የስራ ውል ሲቋረጥ የስንብት ክፍያ እንዱከፈል የሚያስገድድ ህግ ስለላለና የአመት እረፍትም ቢሆን በሞት ምክንያት የስራ ውለ ለተቋረጠ ሰራተኛ ስለማይሰጥ ጥያቄውን ተቀባይነት የለውም በማለት ክሱን ውድቅ አድርጎታል። አመልካቾች በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት ያቀረቡ ቢሆንም ፍ/ቤቱ ይግባኙን ሰርዞታል።
ይህ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሳኔ ላይ ነው። አመልካች በቅሬታቸው የስር ፍ/ቤት የሟች አገልግልት ክፍያም ሆነ የአመት እረፍት ለሚስታቸውና ለልጆቻቸው አይከፈልም መባለ ስህተት በመሆኑ እንዱታረምላቸው አመልክተዋል። ይህ ችልትም የሟች የአመት እረፍት በገንዘብ ተለውጦ ለአመልካቾች ሉከፍል አይገባም የመባለን አግባብነት ለመመርመር አቤቱታው ለሰበር ችልት ያስቀርባል ብሎል። ተጠሪም ቀርበው በሰጡት መልስ የሟች ስራ ውል የተቋረጠው ከሞታቸው በፉት በመሆኑ ጥያቄው ተቀባይነት የለውም ሲለ ተከራክረዋል። ችልቱም መዝገቡን ከተያዘው ጭብጥ አኳያ መርምሯል።
አመልካቾች የጠየቁት የሟቹ አገልግልት ክፍያና አመት እረፍት በገንዘብ ተለውጦ እንዱከፈላቸው ነው።
የአገልግልት ክፍያ ጥያቄን በተመለከተ ለሰበር ችልት ያስቀርበዋል ያልተባለ ከመሆኑም በላይ ይህን ነጥብ አስመልክቶ የስር ፍ/ቤት የሰጠው ውሳኔ ይህ ሰበር ችልት በመ/ ከሰጠው ትርጉም ጋር የሚጣጣም በመሆኑ ይህንኑ ቅሬታ የምንመለከተው አይሆንም። ሁለተኛው የክፍያ ጥያቄ የአመት እረፍትን የሚመለከት ነው። በአ/ቁ 377/1996 አንቀፅ 77(5) በአዋጁ መሰረት የስራ ውለ የተቋረጠ ሰራተኛ ያልወሰደው የአመት ፈቃድ ታስቦ በገንዘብ ተለውጦ እንደሚሰጠው ይደነግጋል። ይህ ድንጋጌ የአመት ፈቃድ በገንዘብ ተለውጦ የሚሰጠው በአዋጁ ከተደነገጉት የስራ ማቋረጫ ምክንያቶች በተወሰኑት ምክንያቶች ብቻ የስራ ውለ ሲቋረጥ ነው የሚል ገደብ አላስቀመጠም። በመሆኑም በማንኛውም በአዋጁ በተመለከቱ ድንጋጌዎች የስራ ውለ ከተቋረጠ የሰራተኛው የአመት እረፍት በገንዘብ ተለውጦ ሉሰጠው የሚገባ መሆኑን መገንዘብ ይቻላል። በአዋጁ መሰረት የስራ ውል ከሚቋረጥባቸው መንገድች አንደ ደግሞ የሰራተኛው መሞት እንደሆነ ከአንቀፅ 24(2) የምንገነዘበው ነው። በመሆኑም የሰራተኛው የስራ ውል በሰራተኛው ሞት ምክንያት ከተቋረጠ የአመት እረፍት በገንዘብ ተለውጦ ለወራሾቹ ሉከፈል የማይገባበት የህግ ምክንያት አይኖርም። በተያዘው ጉዲይ የስር ፍ/ቤት የስራ ውለ በሞት ምክንያት ሲቋረጥ የአመት ዕረፍት በገንዘብ ተለውጦ ሉከፈል አይገባም ሲል የደረሰበት መደምደሚያ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ነው።
በልላ በኩል ግን ተጠሪ ከስር ጀምሮ በተጠሪና በአንደኛ አመልካች ባለቤት እና በቀሪዎቹ አመልካቾች አባት መሃከል የነበረው የስራ ውል ሰኔ 1994 ዓ.ም የተቋረጠና ሟች ጋራዡን በኮንትራት ከያዙት ሰው ጋር ባደረጉት የስራ ውል የሚሰሩ ስለመሆኑ የሚከራከሩ ቢሆንም የስር ፍ/ቤት ይህን የአመልካች ክርክር ሳይመለከት ማለፈን ተገንዝበናል።
ስለሆነም ምንም እንኳን የሟቹ አመት ፈቃድ በገንዘብ ተለውጦ ሉከፈል የሚገባ ቢሆንም ተጠሪ ክፍያውን የመፈፀም ሃላፉነት ያለባቸው መሆን አለመሆኑ ተጣርቶ ሉወሰን ይገባል።
ው ሣ ኔ
የፋ/መ/ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ ህዲር 7 ቀን 2002 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ እና የፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ ጥር 12 ቀን 2002 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ ተሻሽሎል።
አመልካቾች የሟች የስራ ስንብት ክፍያ እንዱከፈላቸው ያቀረቡት ጥያቄ ውድቅ መደረጉ በአግባቡ ነው። ነገር ግን የስራ ውለ በሞት ምክንያት በመቋረጡ የአመት እረፍት በገንዘብ ተለውጦ ሉከፈል አይገባም የሚለው የውሳኔ ክፍል ተሽሯል።
የስር ፍ/ቤት በሟችና በተጠሪ መሃከል የስራ ውል መኖር አለመኖሩን ግራ ቀኙ ካቀረቡት ማስረጃ አኳያ መርምሮ ተገቢውን ውሳኔ እንዱሰጥ ጉዲዩን ለፋ/መ/ደረጃ ፍ/ቤት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 343(1) መሰረት መልሰናል። ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ ይቻቻለ። መዝገቡ ተዘግቷል። ለመዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.