No summary available.
ሰኔ 22 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ሐጎስ ወልደ ሑሩት መለሰ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካቾች፡-
እንደገና ተሾመ - ቀረቡ።
ዲንኤል ባለ - አልቀረቡም።
ተጠሪ፡- ኒው ጄኔሬሽን ዩኒቨርሲቲ ኮላጅ ነቀምቴ ቅርንጫፍ - አልቀረበም።
መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ በአሰሪና ሰራተኞች መካከል የተደረገውን ክርክር የሚመለከት ነው። ክርክሩ ሲጀመር አመልካቾች ከሣሾች የነበሩ ሲሆን፣ በተጠሪ ላይ ክስ የመሰረቱት የሥራ ውላችን ከሕግ ውጪ ስለተቋረጠብን ልዩ ልዩ በአዋጁ የተመለከቱት ክፍያዎች ይክፈለን በማለት ነው። ተጠሪም በበኩለ ለክሱ በሰጠው መልስ ውለ የተቋረጠው ዘመኑ በማብቃቱ ነው በማለት ሲከራከር፣ ፍ/ቤት ደግሞ ውለ የተደረገው ለተወሰነ ጊዜ ነው የሚለውን የተጠሪ ክርክር በመቀጠል የአመልካቾች የውለ ዘመን ከማብቃቱ በፉት ለሚሰሩበት ጊዜ የሥራ ስንብት ክፍያ ይከፈላቸው በማለት ወስኖአል። በልላ በኩል ደግሞ አመልካቾች በውሣኔው ባለመስማማት ይግባኝ ለሚሰማው የበላይ ፍ/ቤት ይግባኝ አቅርበው ክርክሩ በድጋሚ ተሰምቶአል።
ፍ/ቤቱም ውለ በአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 1ዐ የተመለከተውን ድንጋጌ መሰረት በማድረግ የተገባ ስለመሆኑ አሰሪው /ተጠሪ/ አላስረዲም የሚል ምክንያት በመስጠት ውለ ላልተወሰነ ጊዜ የተደረገ ነው በማለት ደምድሟል። በዚህ መሰረትም በሥር ፍ/ቤት የተሰጠውን ውሣኔ በማሻሻል የሥራ ውል ከሕግ ውጪ ሲቋረጥ ሉከፈለ የሚገባቸውን ክፍያዎች በሙለ አመልካቾች ይከፈላቸው በማለት ወስኖአል። በመጨረሻም ተጠሪ ለኦሮሚያ ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ችልት አቤቱታ በማቅረቡ በዚህ ደረጃም ክርክሩ የተሰማ ሲሆን፣ በመቀጠልም የሰበር ችልቱ በሥር ፍ/ቤቶች የተሰጡትን ውሣኔዎች ሽሮአል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ላይ ነው።
እኛም አመልካቾች ጥር 27 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም. በፃፈት ማመልከቻ ያቀረቡትን አቤቱታ መሰረት በማድረግ ክርክሩን ሰምተናል። ተጠሪ አቤቱታው ላይ ያለውን መልስ እንዱያቀርብ በተደጋጋሚ እድል የተሰጠው ቢሆንም፣ የሰጠው መልስ የለም። በመሆኑም ከሥር ጀምሮ የተደረገውን ክርክር አቤቱታ ከቀረበበት ውሣኔ እና ከሕጉ ጋር አገናዝበን መርምረናል።
በግራ ቀኝ ወገኖች ክርክር እንደተመለከተው ተጠሪ በከፍተኛ ትምህርት መስጠት የተሰማራ ሲሆን፣ አመልካቾችን ቀጥሮ ሲያሰራ የነበረው በመምህርነት ነው። እንደሚታወቀው የመማር ማስተማር ሥራ ቀጣይነት ያለው ማለትም የማያቋርጥ ባሕርይ ያለው ሥራ ነው። አመልካቾች የሥራ ውላችን ያለአግባብ ተቋርጦብናል በማለት ክስ በመሰረቱበት ጊዜ ተጠሪ ሥራውን ሲቀጥል እንደነበረም አላከራከረም። አመልካቾችን የቀጠርኩት ለተወሰነ ጊዜ ነው በማለት ሲከራከር የቆየው ሥራው የለም የሚል ምክንያት በመስጠት ሳይሆን፣ ውለ የተፈረመው ለተወሰነ ጊዜ ተብል ነው በማለት ነው። በዚህ መልክ ያቀረበው ክርክር ግን በአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀጽ 1ዐ የተመለከተውን ድንጋጌ መሰረት በማድረግ በፍሬ ነገር ረገድ ሉያስረዲ አልቻለም። አንድ የሥራ ውል ለተወሰነ ጊዜ ወይም ለተወሰነ ሥራ የተደረገ ነው ልባል የሚችለው በአንቀጽ 1ዐ ከተመለከቱት ሁኔታዎች በአንደ ምክንያት የተደረገ ከሆነ ስለመሆኑ በአንቀጽ 9 ተደንግጎአል። በመሆኑም ውለ ለተወሰነ ጊዜ ተብል ተፈርሞአል የሚለው የተጠሪ ክርክር የሕግ መሰረት ያለው አይደለም። አቤቱታ የቀረበበት ውሣኔም ከዚህ አንፃር ስናየው በሕጉ አተረጓጎም ረገድ መሰረታዊ ስህተት ያለበት ነው ለማለት ችለናል።
ው ሣ ኔ
የኦሮሚያ ጠ/ፍ/ቤት በመ/ቁ. 65ዐ98 ኀዲር 1 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም. የሰጠው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽሮአል።
የምስራቅ ወለጋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 13964 ሚያዝያ 24 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. የሰጠው ውሣኔ ፀንቶአል።
ግራ ቀኙ ወገኖች ወጪና ኪሣራቸውን ይቻቻለ ብለናል።
No topics extracted.