No summary available.
ሰኔ 18 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ሒጏስ ወልደ ሂሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ አመልካች፡- የኢትዮጵያ ፕስታ አግልግልት ድርጅት - ማስረሻ በለጠ ቀረቡ ተጠሪ፡- ጥላሁን ኩማ - ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ በአሰሪና ሰራተኛ መካከል የተነሳውን የሥራ ክርክር የሚመለከት ነው። ክርክሩ በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲጀመር ከሣሽ የነበረው ተጠሪ ሲሆን፣አመልካችን የከሰሰው የሥራ ውላ ከሕግ አግባብ ውጪ አቋርጦብኛል በማለት ነው። አመልካችም ለክሱ በሰጠው መልስ የሥራ ውለን ሉያቋርጥ የቻለው ተጠሪ በፈጸመው ከሥራ የሚያሰናብት ጥፊት ምክንያት እንደሆነ በመግለጽ የተከራከረ ቢሆንም፤ፍ/ቤቱ ግን የሥራ ውል ማቋረጥ እርምጃውን የወሰድከው እርጃውን ለመውሰድ በሕጉ የተፈቀደልህ የይርጋ ጊዜ ካበቃ(ካለፈ) በኋላ ነው የሚል ምክንያት በመስጠት ክርክሩን ውድቅ አድርጏአል። በዚህ መሰረትም ተጠሪ ውዝፍ ደመወዝ ተከፍልት ወደሥራው እንዱመለስ ወስኖአል።
ጉዲዩ በይግባኝ የቀረበለት የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤትም ውሳኔው ጉድለት የለበትም በማለት የአመልካችን ይግባኝ ሰርዞአል። የሰበር አቤቱታው የቀረበው በዚህ ላይ ነው።
አመልካች የካቲት 26 ቀን 2002 ዓ.ም በፃፈው ማመልከቻ በሥር ፍ/ቤቶች ውሳኔ ተፈጸመ የሚለውን ስህተት በመግለጽ አቤቱታውን አቅርቦአል። እኛም አቤቱታውን መሰረት በማድረግ ተጠሪን አስቀርበን ክርክሩን ሰምተናል።
አቤቱታው በሰበር ችልት እንዱታይ የተደረገው ተጠሪ ፈጽሞታል የተባለውን ጥፊት በዱሲፔሉን ኮሚቴ ለማጣራት የወሰደው ጊዜ እግምት ውስጥ ሳይገባ ድርጊቱ በይርጋ ቀሪ ነው የመባለን አግባብነት ለመመርመር ሲባል ነው።
በመሆኑም በዚህ ረግድ ግራ ቀኝ ወገኖች ያሰሙትን ክርክር አቤቱታ ከቀረበበት ውሳኔ እና ከሕጉ ጋር አገናዝበን መርምረናል።
እንደምንመለከተው በዚህ ሰበር ችልት ሉወሰን የሚገባው የሕግ ጭብጥ የይርጋው ጊዜ መቆጠር የሚጀምረው ጉዲዩ በዱሲፔሉን ኮሚቴ ተጣርቶ ጥፊቱ ከታወቀበት ቀን ጀምሮ ነው ወይንስ ጥፊቱ ተፈጽሞአል ከተባለበት ቀን ጀምሮ ነው? የሚለው ነው። ለዚህ ጭብጥ አወሳሰን ተገቢነት ያለው ድንጋጌ በአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 27/3/ የተመለከተው ነው። አንቀጽ 27 ያለማስጠንቀቂያ የሥራ ውል ለማቋረጥ የሚያስችለ ምክንያቶችን በዝርዝር የያዘ ሲሆን፣ በልላ በኩል ደግሞ አሰሪው ወገን ምክንያቶቹን መሰረት በማድረግ የሚወስደው የሥራ ውል የማቋረጥ እርምጃ በጊዜ ውስጥ የተገደበ መሆኑን የሚያመላክት ድንጋጌ ይዞአል። ድንጋጌው ከፍ ሲል የተጠቀሰው በንኡስ አንቀጽ /3/ የተቀመጠው ሲሆን፣ይዘቱም አሰሪ የሥራ ውለን ለማቋረጥ ያለው መብት ውለ የሚቋረጥበት ምክንያት መከሰቱን ካወቀበት ከ30/ሰላሣ/ የሥራ ቀናት በኋላ በይርጋ ይታገዲል የሚል ነው። እንግዱህ እዚህ ላይ በቁልፍነት መታየት የሚገባው “… ውለ የሚቋረጥበት ምክንያት መከሰቱን ካወቀበት …” የሚለው የሕጉ አግባብ ነው። ከዚህ አባባል መገንዘብ የሚቻለው የመጀመሪያው ሁኔታ አሰሪው ውለን ለማቋረጥ የማቋረጫ ምክንያቱን ማወቅ ይኖርበታል የሚለው ነው። የሥራ ውለን ለማቋረጥ ምክንያት መኖሩን ማወቅ የግድ ነው ከተባለ ደግሞ መቼ ነው ያወቀው የሚለው በሁለተኛ ደረጃ የሚታይ ይሆናል። ጥፊቱ ወይም የሥራ ውል ማቋረጫ ምክንያቱ መከሰቱን ለማረጋገጥ የተወሰነ የማጣራት ሥራ የሚያስፈልግ ከሆነ ይህ የማጣራት ሥራ ከተከናወነ በኋላ ነው አሰሪው ምክንያት ወይም ጥፊት መኖሩን አውቆአል ልባል የሚችለው።
ወደያዝነው ጉዲይ ስንመለስ አመልካች ምክንያቱ በእርግጠኝነት ያወቀው ጉዲዩን በዱሲፔሉን ኮሜቴ አማካይነት ካጣራ በኋላ እንደሆነ በፍሬ ነገር ረገድ ተረጋግጦአል። ከተረጋገጠ በኋላም የሥራ ውለን አቋርጧል። በዚህ መሃልም በተመለከተው ድንጋጌ የተቀመጠው የ30/ሰላሳ/ የሥራ ቀናት ጊዜ አልፍአል አልተባለም። ሁኔታው ይህ ከሆነ ደግሞ አመልካች የሥራ ውለን የማቋረጥ እርምጃ የወሰደው የይርጋው ጊዜ ካበቃ በኋላ ነው ለማለት የሚቻልበት የሕግ አግባብ የለም። የሥር ፍ/ቤቶች የሰጡት ውሳኔ ከዚህ አንፃር ሲታይ በሕጉ አተረጓጏም ረገድ መሰረታዊ ስህተት የተፈጸመበት ነው ለማለት ችለናል።
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 32585 ጥር 14 ቀን 2002 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ እና የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 89003 የካቲት 16 ቀን 2002 ዓ.ም የሰጠው ትእዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽረዋል።
አመልካች የሥራ ውል የማቋረጥ እርምጃውን የወሰደው የይርጋ ጊዜው ከማለፈ በፉት ነው ብለናል።
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ወደ ጉዲዩ ሥረ ነገር በመግባት የሥራ ውለ የተቋረጠው በአግባቡ ነው ወይስ አይደለም? የሚለው ጭብጥ ላይ ግራ ቀኝ ወገኖችን እንዱያከራክር እና ተገቢውን እንዱወስን ጉዲዩ በፍ/ብ/ሥነ-ሥርአት ሕግ ቁጥር 341/1/ መሰረት ይመለስለት ብለናል።
ግራ ቀኝ ወገኖች ወጪና ኪሣራቸውን ይቻቻለ።
No topics extracted.