No summary available.
ሰኔ 30 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ሂሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- አዱስ አበባ ሂልተን ሆቴል - ጠ/ ሃሣብ ከፊይ - ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ዘላለም መንግስቱ - ጠ/ ሻምበል የሥጋት - ቀረቡ
በዚህ መዝገብ የቀረበው ጉዲይ የስራ ክርክርን የሚመለከት ነው። ተጠሪ ለፋ/መ/ደረጃ ፍ/ቤት በመሰረቱት ክስ አመልካች ያለአግባብ ከስራ ያሰናበታቸው በመሆኑ ደሞዝና ጥቅማ ጥቅም ከፍል ወደ ስራ እንዱመልሳቸው አመልክተዋል። አመልካችም ለክሱ በሰጠው መልስ ተጠሪ ከስራ የተሰናበቱት የተለያዩ ጥፊቶች በመፈፀማቸው ስለሆነ ስንብቱ ህጋዊ ነው በማለት ተከራክሯል። ፍ/ቤቱም የግራቀኙን ክርክርና ማስረጃ ከሰማ በኃላ አመልካች ተጠሪን ከሰራ ለማሰናበት ምክንያት ናቸው በማለት በስንብት ደብዲቤው ላይ የዘረዘራቸውን ጥፊቶች ለመፈፀማቸው ያቀረባቸው ምስክሮች ስላላስረደ ስንብቱ ህገ-ወጥ ነው በማለት ተጠሪ የ3 ወር ደሞዝ ተከፍሎቸው ወደ ስራ እንዱመለሱ ወስኗል።
አመልካች በዚህ ውሣኔ ላይ ይግባኝ ለፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት አቅርቦ ፍ/ቤቱ ይግባኙን ሰርዞታል።
የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሣኔ ላይ ሲሆን አመልካች በቅሬታው ተጠሪ ከስራ የተሰናበቱት በፈፀሙት ጥፊቶች መሆኑን በበቂ ሁኔታ አስረድቶ እያለ ስንብቱ ህገ-ወጥ ነው መባለ ስህተት መሆኑን ስንብቱ ህገ-ወጥ ነው ቢባል እንኳን ተጠሪ ወደ ስራ ቢመለሱ መልካም የስራ ግንኙነት ስለማይኖር በአ/ቁ 377/96 በአንቀጽ 43/3/ መሰረት ካሳ ተከፍሎቸው ከስራ ሉሰናበቱ ሲገባ ወደ ስራ መመለሳቸው ተገቢ አይደለም በማለት የስር ፍ/ቤት ውሣኔ እንዱሻር ጠይቋል። ይህ ችልትም ተጠሪ ወደ ስራ ቢመለሱ መልካም የስራ ግንኙነት አይኖርም በማለት የቀረበውን አቤቱታ ከአ/ቁ 377/96 አንቀጽ 43/3/ አንፃር ለመመርመር አቤቱታው ለሰበር ችልት እንዱቀርብ አድርጓል። ተጠሪም ቀርበው በሰጡት መልስ አመልካች ያቀረበው የሰበር አቤቱታ ፍሬ ነገርን የሚመለከት እንጂ የህግ ስህተትን የሚመለከት ባለመሆኑ ተቀባይነት ሉኖረው አይገባም በማለት ተከራክረዋል። ችልቱም መዝገቡን ከተያዘው ጭብጥ አኳያ መርምሯል።
አመልካች ተጠሪን ከስራ ማሰናበቱን ሳይክድ የሚከራከረው ተጠሪ ከስራ የተሰናበቱት በፈፀሙት ጥፊት በመሆኑ ስንብቱ ህጋዊ ነው በማለት ነው። አመልካች ለስር ፍ/ቤት በሰጠው መልስ ተጠሪ ፈፀሙ ያላቸውን ጥፊቶች ዘርዝሮ ገልጿል። ጥፊቶቹንም ስለመፈፀማቸው ያስረዲለ ያላቸውን ምስክሮች ቆጥሮ ተሰምተዋል። ፍ/ቤቱም የምስክሮች ቃል መዝኖ አመልካች በተለይ ተጠሪን ከስራ ሲያሰናብት በስንብት ደብዲቤው ላይ የገለፃቸውን ጥፊቶች ስለመፈፀማቸው እንዲላስረደ በፍሬ ነገር ረገድ አረጋግጧል። ይህ ችልትም በስር ፍ/ቤት የተረጋገጠን ፍሬ ነገር እንዲለ የሚቀበለው ከሚሆን በቀር ማስረጃውን በድጋሚ ሉመዝን የሚችልበት ስልጣን የለውም። ስለሆነም ተጠሪ ከስራ የሚያሰናብታቸው ጥፊት መፈፀማቸው ባለመረጋገጡ ስንብቱ ህገ-ወጥ ነው በመባለ መሰረታዊ የህግ ስህተት ተፈፃሟል ማለት አይቻልም።
ላላው ተጠሪ ከስራ የተሰናበቱ በህገ-ወጥ መንገድ ነው ቢባል እንኳን ወደ ስራ ቢመለሱ መልካም የስራ ግንኙነት ስለማይኖር ካሣ ተከፍሎቸው ሉሰናበቱ ይገባ ነበር በማለት አመልካች ያቀረበው ቅሬታ ነው። በእርግጥ በአ/ቁ 377/96 አንቀጽ 43/3/ ስር የስራ ስንብቱ ህገ-ወጥ ቢሆን እንኳን ከስራ ግንኙነቱ ፀባይ የተነሳ ከፍተኛ ችግር የሚፈጥር ከሆነ ሰራተኛውን ወደ ስራ ከመመለስ ይልቅ ካሣ ተከፍልት እንዱሰናበት ማድረግ ይቻላል። ይህ የህጉ ድንጋጌም ሉተረጎም የሚገባው በአንድ በኩል የሰራተኛውን የስራ ዋስትና በልላ በኩል ደግሞ ኢንደስትሪን ሰላም በማመዛዘን ላሆን ይገባል።
በመሆኑም ሰራተኛው ወደ ስራ መመለሱ የአሰሪውን ስራ በከፍተኛ ደረጃ ሉጎዲ የሚችል መሆኑ ካልተረጋገጠ በቀር ሰራተኛው በሆነው ባልሆነው ከስራ እንዱሰናበቱ ማድረግ ተገቢ አይሆንም። የህጉም አላማ ይህ አይደለም። በተያዘው ጉዲይ የተጠሪ ጥፊቶች ናቸው ከሚባለት ውስጥ አንደና አመልካች ተጠሪ ስራ ቢቀጥለ መልካም የስራ ግንኙነት ሉኖር አይችልም በማለት የሚከራከረው የተጠሪ የስራ አፈፃፀም ዝቅተኛ መሆኑን ነው። ነገር ግን ይህን ለማስረዲት በአመልካች በኩል የቀረቡ ምስክሮች ደግሞ ከፍ ሲል እንደተጠቀሰው እንደአመልካች ክስ አቀራረብ አላስረደም። ከዚህ ውጪ ግንኙነቱ ቢቀጥል የአሰሪና ሰራተኛ ግንኙነቱ ከፍተኛ ችግር ላይ ሉጥል የሚችል ሁኔታ ስለመኖሩ አመልካች ያስረዲው ነገር የለም። የአመልካች የስራ አፈፃፀም ዝቅትኛ መሆኑ ካልተረጋገጠ ደግሞ ተጠሪ ወደ ስራ ቢመለስ የስራ ግንኙነቱ ከፍተኛ ችግር ላይ ሉወድቅ ይችላል ለማለት ስለማይቻል ተጠሪ ወደስራ ከሚመለሱ ይልቅ ካሣ ተከፍሎቸው ሉሰናበቱ ይገባል በማለት አመልካች ያቀረበውን ክርክር ችልቱ የሚቀበለው አይደለም። በመሆኑም በስር ፍ/ቤት ተጠሪ ወደ ስራ እንዱመለሱ የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት አለው ለማለት አልተቻለም።
ው ሣ ኔ
የፋ/መ/ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ መጋቢት 20 ቀን 2002 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔና የፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ ሚያዚያ 6 ቀን 2002 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ ፀንቷል።
ወጪና ኪሣራ ግራቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።
ይህ ሰበር ችልት ሚያዚያ 19 ቀን 2002 ዓ.ም የሰጠው የዕግድ ትዕዛዝ ፀንቷል። ለሚመለከተው ክፍል ይፃፍ።
No topics extracted.