No summary available.
ሰኔ 07 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ሐጏስ ወልደ ታፈሰ ይርጋ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- የኢትዮጵያ ኤርፕርቶች ድርጅት - ነ/ፈጅ ስዩም ጌራወርቅ - ቀረቡ ተጠሪ፡- ወ/ሮ ሶፊኒት አጥናፈ - አልቀረቡም መዝገቡን መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል።
በዚህ መዝገብ የቀረበው ክርክር የሥራ ውል ማቋረጥን የሚመለከት ነው። ለዚህ ሰበር አቤቱታ መነሻ የሆነው ተጠሪ ያቀረቡት ክስ ነው። ጉዲዩ የተጀመረው ጅጅጋ ወረዲ ፍ/ቤት ላይ ነው። የተጠሪ የዲኝነት ጥያቄ አመልካች ያለአግባብ ከሥራ እንዲሰናበታቸው ገልፀው የሥራ ስንብት እና ልዩ ልዩ ክፍያዎች እንዱከፈላቸው እንዱወሰን የሚል ነበር። በአመልካች በኩል በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያነት ያቀረበው ፍ/ቤቱ ስልጣን የላለው ስለመሆኑ እና ክሱ የቀረበው ስድስት ወር ጊዜ ካለፈ በኋላ በመሆኑ በይርጋ ሉታገድ እንደሚገባ በሚል ሲሆን በፍሬ ነገር ረገድም በአማራጭ ክርክር አቅርቧል።
ክርክሩን በመጀመሪያ የተመለከተው የጅጅጋ ወረዲ ፍ/ቤት በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 138 መሰረት ጉዲዩን የመዲኘት ሥልጣን እንዲለው አረጋግጦ የይርጋ ክርክርን በተመለከተ ተጠሪ ከሥራ የተሰናበቱት ሐምል 1 ቀን 2000 ዓ.ም ሆኖ ጉዲዩ በሶማላ ብ/ክ/መንግሥት ሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዲይ ጽ/ቤት እንዱታይ ተጠሪ አመልክተው ጽ/ቤቱ በ24/11/2000 ዓ.ም ውሳኔ የሰጠ በመሆኑ ክሱ የቀረበው በ10/05/2001 ዓ.ም ጊዜ ድረስ ያለው ሲታይ የስድስት ወር /6/ ጊዜ አላለፈበትም ሲል በብይን መቃወሚያውን ውድቅ አድርጓል። በፍሬ ነገር ረገድም የግራ ቀኙን ክርክር እና ማስረጃ ሰምቶ ውሳኔ ሰጥቷል።
አመልካች በውሳኔው ቅር ተሰኝቶ ለከፍተኛው ፍ/ቤት ይግባኝ ያቀረበ ሲሆን ከፍተኛው ፍ/ቤትም መቃወሚያውን ባለመቀበል በፍሬ ነገር ረገድ ለተጠሪ ሉከፈል የሚገባውን ክፍያ መጠን ብቻ በማሻሻል የወረዲውን ፍ/ቤት ውሳኔ አፅንቷል። የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤትም የካሳውን መጠን ብቻ በማሻሻል ወስኗል።
ለዚህ ሰበር ሰሚ ችልት አቤቱታ የቀረበው በዚሁ ላይ ነው። የአመልካች ድርጅት ነ/ፈጅ ጥር 14 ቀን 2002 ዓ.ም ጽፍ ያቀረቡት የሰበር አቤቱታ ክሱ በይርጋ ይታገድ ይገባው እንደነበር እና የሥር ፍ/ቤቶች የይርጋ ክርክሩን ውድቅ ለማድረግ የሰጡት ምክንያት መሰረታዊ የሕግ ትርጉም ስሕተት የተፈፀመበት ስለመሆኑ እንዱሁም በፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ የተሰጠውን ውሳኔ የሚፃረር መሆኑን፣ በፍሬ ነገር ረገድም የሥር ፍ/ቤቶች ውሳኔ በግራ ቀኙ መካከል የተደረገውን ውል በአግባቡ ያላገናዘበ ስለመሆኑ በማብራራት የሥር ፍ/ቤቶች ውሳኔ እንዱታረም አመልክተዋል።
የሰበር ሰሚ ችልት አቤቱታውን ከመረመረ በኋላ የአመልካች ድርጅት የይርጋ መቃወሚያ የታለፈበትን አግባብ ለመመርመር ተጠሪን አስቀርቧል።
የተጠሪ ወኪል ሰኔ 4 ቀን 2002 ዓ.ም በጽሐፍ ባቀረቡት መልስ የሥራ ውል ከተቋረጠው ሐምል 1 ቀን 2000 ዓ.ም ክስ እስከቀረበበት ጥር 10 ቀን 2001 ዓ.ም ድረስ ያለው ጊዜ 6 ወር ከ10 ቀን መሆኑን አምነው ይህ ጊዜ ያለፈው ተጠሪ ክስ ከማቅረባቸው በፉት ጉዲዩ በክልለ ሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዲይ ጽ/ቤት እንዱታይ አመልክተው እንደነበር እና ጽ/ቤቱም ለጉዲዩ እልባት ለመስጠት አለመቻለን ገልፆ በ24/11/2000 ዓ.ም ውሳኔውን ያሳወቃቸው በመሆኑ የይርጋ ጊዜ መቆጠር የሚጀምረው ከ24/11/2000 ዓ.ም ነው በማለት የሥር ፍ/ቤቶች ውሳኔ እንዱፀና አመልክተዋል።
የግራ ቀኙ ክርክር እና የጉዲዩ አመጣጥ ከፍ ሲል የተመለከተው ሲሆን እኛም ከተያዘው ጭብጥ አንፃር ከሕጉ አገናዝበን መርምረናል።
ከፍሲል በዝርዝር እንደተመለከተው በአመልካች እና ተጠሪ መካከል የነበረው የሥራ ውል የተቋረጠው ሐምል 1 ቀን 2000 ዓ.ም መሆኑ እና ክስ የቀረበው ጥር 10 ቀን 2001 ዓ.ም መሆኑ አላከራከረም። ይህ ጊዜ ሲሰላም ስድስት ወር ያለፈው መሆኑን ተጠሪም አምነዋል። በተጠሪ በኩል የቀረበው ክስ የሥራ ውል የተቋረጠው አለአግባብ ነው በሚል ልዩ ልዩ ክፍያዎች እንዱወሰኑ በሚል ነው።
በአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 162 ልዩ ልዩ የመብት ጥያቄዎችን አስመልክቶ ክሱ መቅረብ ያለበትን የጊዜ ገደብ ወስኗል።
ለተያዘው ጉዲይ አግባብነት ያለው የአዋጁ አንቀጽ 162(4) የሥራ ውል በመቋረጡ ምክንያት በሰራተኛውም ሆነ በአሰሪው የሚቀርብ ማንኛውም የክፍያ ጥያቄ የሥራ ውለ በተቋረጠ በስድስት ወር ጊዜ ውስጥ ካልቀረበ በይርጋ እንደሚታገድ በግልፅ ደንግጓል። በዚህ መዝገብ የቀረበው የክፍያ ጥያቄም የሥራ ውል ከተቋረጠበት ከሐምል 1 ቀን 2000 ዓ.ም ክስ እስከቀረበበት ጥር 10 ቀን 2001 ዓ.ም ድረስ ያለው ጊዜ ሲሰላ ስድስት ወር ያለፈው ስለመሆኑ ተረጋግጧል የሥር ፍ/ቤቶች የአመልካችን የይርጋ ክርክር ውድቅ ለማድረግ የሰጡት ምክንያቶች ሁለት ናቸው። እነሱን አንድ በአንድ እንመረምራለን። አንደኛው ምክንያት ተጠሪ የሥራ ውል እንደተቋረጠባቸው አቤቱታቸውን ለክልለ ሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዲይ ጽ/ቤት አመልክተው ጽ/ቤቱ በጉዲዩ ላይ ውሳኔ የሰጠው ሐምል 24 ቀን 2000 ዓ.ም ስለሆነ የይርጋ ጊዜ መቆጠር ያለበት ከሐምል 24 ቀን 2000 ዓ.ም ጀምሮ ነው የሚል ነው። በግራ ቀኙ መካከል ያለው ክርክር የሥራ ውል በማቋረጡ ሉከፈል የሚገባ ልዩ ልዩ ክፍያን የሚመለከት ስለመሆኑ መዝገቡ ያስረዲል። በአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ ላይ የሥራ ውል አመሰራረት እና በግኙኝነት ሂደት የሚፈጠሩት ክርክሮች ለመፍታት የተለያዩ አካላት ሥልጣን የተሰጣቸው ስለመሆኑ የአዋጁን ክፍል ዘጠኝ አንቀጽ 136 እና ተከታዮችን ድንጋጌዎች ይዘት መረዲት ይቻላል። አሁን ለተያዘው ጉዲይ የሥራ ውል በመቋረጡ ሉከፈል የሚገባ ክፍያን አስመልክቶ ሥልጣን የተሰጠው አካል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤቶች ስለመሆኑ ከአዋጁ አንቀጽ 138 ድንጋጌ ይዘት መረዲት ይቻላል።
ተጠሪ ይህንኑ ጥያቄ ለክልለ ሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዲይ ጽ/ቤት አቅርበውም ቢሆን በተያዘው ጉዲይ ላይ ለመወሰን በህግ ስልጣን ያልተሰጠው አካል እንደመሆኑ አግባብነት ያለው አይደለም። በዚህ ረገድ ይህ ሰበር ሰሚ ችልት በተመሳሳይ ጉዲይ ላይ በመ/ የሰጠው የሕግ ትርጉም ይህንኑ ያስገነዝባል። ስለሆነም የሥር ፍ/ቤቶች ተጠሪ ለክልለ ሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዲይ ጽ/ቤት አቤቱታ አቅርበው ነበር በሚል የይርጋው ጊዜ ከሐምል 24 ቀን 2000 ዓ.ም ጀምሮ ሉቆጠር ይገባል ያለት የፋዳራል ጠቅላይ ሰበር ችልት ፍ/ቤት በመ/ የሰጠው አስገዲጅ የሕግ ትርጉም ያላገናዘበ ነው። ሁለተኛው ምክንያት የይርጋ ጊዜው አቆጣጠር የሥራ ቀናትን ብቻ መሰረት ያደረገ ነው የሚል ሲሆን ለዚህም የጠቀሱት የአዋጁን አንቀጽ 163 ነው። ተጠቃሽ ድንጋጌ የይርጋ ጊዜ አቆጣጠር የሚመለከት መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ የቀናት አቆጣጠር የመጀመሪያው እና የመጨረሻውን ቀን የሚያመለክት ነው። የመጨረሻው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በተከታዩ የሥራ ቀን እንደሚወሰድ የሚያመለክት ቢሆንም ሙለ ጊዜው የሚሰላው የሥራ ቀናትን ብቻ በመለየት ነው የሚል ይዘት ያለው ስለመሆኑ የድንጋጌው አንቀጽ 163(2) አያመለክትም። ስለሆነም በዚህ ረገድም የሥር ፍ/ቤቶች የሰጡት ትርጉም የሕጉን መንፈስ የያዘ ሆኖ አላገኘነውም። ባጠቃላይ የሥር ፍ/ቤቶች ይርጋ ጊዜው ክሱን አያስቀረውም ለማለት የሰጡት ምክንያቶች በሕግ ረገድ የተሳሳተ ትርጉም የሰጡበት ስለሆነ ሉታረም ይገባል ብለናል።
ስለዚህ ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
ው ሣ ኔ
የጅጅጋ ወረዲ ፍ/ቤት የጅጅጋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ 23/2002 የሰጡት ውሳኔ እና የሱማላ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍ/ቤት የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 348(1) መሰረት ተሽሯል።
የተጠሪ የክፍያ ጥያቄ በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 162(4) መሰረት በይርጋ ታግዶል።
የዚህን ፍ/ቤት ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል። ይፃፍ።
No topics extracted.