No summary available.
ግንቦት 19 ቀን 2002 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ሂሩት መለሰ ተሻገር ገ/ሥላሴ ታፈሰ ይርጋ አልማው ወላ ዓሉ መሀመድ አመልካች፡- ፊውንዳሸን አፍሪካ -ጠበቃ መላኩ ካሰኝ - ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ዓለሙ ታደሰ- ጠበቃ አብደላ ዓሉ - ቀረቡ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ አዋጅ ቁጥር 377/96 “ን” መሰረት ያደረገ ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነው። ክርክሩ ሲጀመር ከሣሸ የነበሩት የአሁኑ ተጠሪ ሲሆኑ የአሁኑ አመልካች ደግሞ ተከሣሸ ነበር። የስር ከሣሸ ክስ ይዘት ሲታይም በአመልካች ድርጅት ከጥር 1 ቀን 1977 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ታህሳስ 22 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም. ድረስ ለሃያ አራት አመታት ሲሰሩ እንደቆዩ፣ ከሣሽና ተከሣሽ ታህሳስ 22 ቀን 1996 ዓ.ም. በተፈራረሙት ውል አለመግባባት ከተፈጠረ በኔዘርላንድስ ሕግና ፍርድ ቤቶች ለመዲኘት የተፈራረሙ ቢሆንም ውለን የተፈራረሙት በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚሰራ ስራና ስራው የተሰራውም በኢትዮጵያ ውስጥ በመሆኑ፣ ተከሣሽም በኢትዮጵያ ውስጥ ተመዝግቦ የሚሰራ መሆኑን ገልፀው ጉዲዩን ለማየት ስልጣን ያለው የኢትዮጵያ ፍርድ ቤት መሆኑን ገልፀው የስራ ውለ ያለምንም ጥፊት ስለተቋረጠ ካሣ፣ የስራ ስንብት ክፍያ፣ የማስጠንቀቂያ ጊዜ ክፍያ፣ የዓመት እረፍት፣ ክፍያ ለዘገዬበት ክፍያ ከተለያዩ ክፍያዎች ጋር እንዱከፍለ ይወሰንላቸው ዘንድ ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው። የአሁኑ አመልካች ለክሱ በሰጠው መልስም፣ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያና የፍሬ ነገር ክርክር አቅርቧል። ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው የፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤትም በአመልካችና በተጠሪ መካከል የተደረገው ስምምነት ሕጋዊ አለመሆኑን ገልጾ ጉዲዩ በአዋጅ ቁጥር 377/96 መሰረት መታየት ያለበት ነው ብል በዚሁ አንፃር ተመልክቶ ስንብቱን ሕገ ወጥ ነው ሲል ለተጠሪ የተለያዩ ክፍያዎች እንዱከፍሎቸው ወስኖአል። በዚህ ውሣኔ አመልካች ባለመስማማት ይግባኙን ለፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቢያቀርብም ችልቱ ጉዲዩ ለሰበር ችልቱ ላቀርብ ከሚችል በስተቀር በይግባኝ ላታይ የሚችል አይደለም በማለት ዋናውን ጉዲይ ሳይመረምር አልፍታል። የሰበር አቤቱታው የቀረበውም የፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሰጠው ውሣኔ ላይ ነው።
የአመልካች ጠበቃ ታህሳስ ዐ5 ቀን 2002 ዓ.ም. በፃፊት የሰበር ማመልከቻ በበታች ፍርድ ቤቶች ውሣኔ ላይ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል የሚለበትን ምክንያት ዘርዝረው አቅርበዋል። ይዘቱም ባጭሩ፡- ጉዲዩ የግለሰብ ዓለም አቀፍ ሕግ የሚያስነሳ ስለሆነ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተመልክቶ ብይን ይስጥበት ተብል በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ተሰጥቶ ይኽው ትዕዛዝ በይግባኝ ፀንቶ ባለበት ሁኔታ ከፍተኛው ፍርድ ቤት በዚህ ረገድ በቀረበለት ጉዲይ ብይን ሳይሰጥ ጉዲዮ በአዋጅ ቁጥር 377/96 መሰረት የሚታይ ነው ብል ራሱ በመጀመሪያ ደረጃ አይቶ መወሰኑ ያላግባብ ስለሆነ ሉታረም ይገባዋል በማለት መከራከራቸውን የሚያሣይ ነው። አቤቱታቸውም ተመርምሮ በሰበር ችልቱ ላታይ ይገባዋል ተብል የተጠሪ ጠበቃ ቀርበው የካቲት 25 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም. በተፃፈ ሶስት ገፅ ማመልከቻ መልሣቸውን ሰጥተዋል። የአመልካች ጠበቃ በበኩላቸው ግንቦት 12 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም. የመልስ መልሳቸውን ሰጥተዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሣኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዮን በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። እንደመረመረውም የፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጉዲዩ የሚገዛው ግራ ቀኙ ባደረጉት ስምምነት መሰረት ሳይሆን በአዋጅ ቁጥር 377/96 መሰረት ነው ካለ በኃላ ጉዲዩን ራሱ በመጀመሪያ ደረጃ ሥልጣን ማየቱ ተገቢ ነው ወይስ አይደለም? የሚለው ነጥብ ምላሽ የሚያስፈልገው ሆኖ አግኝቶታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው ግራ ቀኙ ታህሳስ 22 ቀን 1996 ዓ.ም. ባደረጉት ስምምነት መሰረት በመካከላቸው የሚነሣው አለመግባባት በኔዘርንላድስ ሕግና ፍርድ ቤቶች የሚታይ መሆኑን መስማማታቸውን፣ በመካከላቸው ያለው ግንኙነትም የአሰሪና ሰራተኛ ግንኙነት መሆኑን፣ ተጠሪ ኢትዮጵያዊ ሆነው የሚኖሩትና ስራውን ለመስራት ግዳታ የገቡት በኢትዮጵያ ውስጥ መሆኑን፣ አመልካች የውጪ ድርጅት ሆኖ የተመዘገበውና ስራውን የሚሰራው በኢትዮጵያ ውስጥ መሆኑን ነው።
በመሰረቱ በአዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 11/2(ሀ) ስር የግለሰብ ዓለም አቀፍ ሕግ (Private international law) የሚመለከቱ ጉዲዮች በሚኖሩ ጊዜ የፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የመጀመሪያ ደረጃ የፍትሐብሕር የዲኝነት ሥልጣን እንደሚኖረው ተደንግጓል። አዋጁ ይህን ድንጋጌ ሲያስቀምጥ የራሱ የሆነ ምክንያት አለው ተብል ይታሰባል።
በዚህም መሰረት ሕግ አውጪው ይህንን ድንጋጌ ያስቀመጠው አንድም ወደፉት በስራ ላይ የሚውለውን የአገሪቱን የግለሰብ ዓለም አቀፍ ሕግ በሕግ አውጪው አካል ፀድቆ በስራ ላይ ሲውል በዚህ ረገድ የሚነሱ የሕግ ክርክሮችን የፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመጀመሪያ ደረጃ የዲኝነት ሥልጣን አይቶ እንዱወስን ወይም አሁን ባለው ሁኔታ ለኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶች ለዲኝነት በቀረበ አንድ ጉዲይ ላይ ከተከራካሪ ወገኖች አንደ የኢትዮጵያ ሕግ ከአመልካቹ አገር ሕግ ወይም ከላላ አገር ሕግ ጋር ይጋጫል ወይም ይቃረናል በማለት በኢትዮጵያ ሕግ እንዲይዲኝ ወይም በራሱ ወይም በልላ አገር ሕግ ጉዲይ እንዱታይና እንዱወሰንለት ሲያመለክት ነው። በልላ አገላለጽ ለዲኝነት የቀረበው ጉዲይ በባሕርይው ከአንድ በላይ የሆኑ የሕግ ሥርዓቶችን ለጉዲዩ አወሳሰን የሚጋብዝና የየትኛው ሥርዓት ሕግ ተመራጭ ላሆን ይገባል የሚለው ክርክር ሲነሳ የፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመጀመሪያ ደረጃ የፍትሐብሄር የዲኝነት ሥልጣን አይቶ እንዱወስን ከመደረጉ ውጪ በማናቸውም ሁኔታ ተከራካሪዎች የአገሪቱን ሕግ በሚፃረር መልኩ ስምምነት አድርገው ሲገኙ ሁለ ተከራካሪ ወገን ክርክር ስላነሳ ብቻ የግለሰብ አለም አቀፍ ሕግ ጥያቄ የሚያስነሣ ነው ልባል የሚችልበት ሕጋዊ ምክንያት አይኖርም። ከዚህ አንፃር ግራ ቀኙ አደረጉ የተባለትን ስምምነት ስንመለከት የኢትዮጵያ አሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ ሕግ ተፈፃሚነት እንዲይኖረው የሚያደርግ፣ የኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶችም ጉዲዩን እንዲይመለከቱ የሚገልጽ መሆኑ ሲታይ ስምምነቱ ተቀባይነት አለው ልባል የሚችልበት ሕጋዊ ምክንያት አለመኖሩን ከአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ ዓላማ እና መንግሥት አዋጁ ላይ ካለው ጠቅላላ ፍላጎት አንፃር የምንገነዘበው ጉዲይ ነው። የአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ የመንግሥትም ፍላጎት የሚንፀባረቅበት ሕግ ሲሆን ይህን አዋጅ የሚመለከቱ ስምምነቶች ሕጋዊ እና የሕዝብን ጥቅም የማይፃረሩ መሆን ይገባቸዋል። የሚኒስትሮች ምክር ቤት በደንብ ካልወሰነ በስተቀር አዋጅ ቁጥር 377/96 የውጪ አገር ድርጅት ሆኖ በኢትዮጵያ ተመዝግቦ በሚሰራ የበጎ አድራጎት ድርጅት ላይ ተፈፃሚነት ያለው ስለመሆኑ ከአዋጁ ድንጋጌ 3/3/ለ/ ይዘት የምንገነዘበው ነጥብ ነው። በዚህ ረገድ የወጣ ደንብ የለም። እንዱህ ከሆነ አዋጅ ቁጥር 377/96 ለጉዲዮ ተፈጻሚነት ያለው በመሆኑ ጉዲዩ የግለሰብ አለም አቀፍ ሕግ ጥያቄን ስምምነቱን መሰረት አድርጎ ያስነሣል ልባል የሚችልበት ምክንያት የለም። በመሆኑም የፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ለጉዲዩ አዋጅ ቁጥር 377/96 ተፈፃሚነት እንዲለው መወሰኑ አግባብነት ያለው ቢሆንም ጉዲዩ የአለም አቀፍ የግለሰብ ሕግ ጥያቄ እንደማያስነሳ በመግለጽ ጉዲዩን ለፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት መመለስ ሲገባው ራሱ በመጀመሪያ ደረጃ ሥልጣኑ መመልከቱ ተገቢነት የላለውና የአመልካችን የይግባኝ መብት ያጣበበ ሆኖ ስለተገኘ በዚህ ረገድ የተሰጠው የውሣኔው ክፍል መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ አግኝተናል። በዚህም መሰረት ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ጥቅምት 25 ቀን 2002 ዓ.ም. የሰጠው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የዲኝነት ሥልጣን ተመልክቶ የመወሰን ሥልጣን ያለው የፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ነው ብለናል።
ለክርክሩ የወጣውን ወጪና ኪሣራ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
No topics extracted.