No summary available.
መ/ ግንቦት 19 ቀን 2002 ዳኞች፡- ሂሩት መለሰ ተሻገር ገ/ሥላሴ ታፈሰ ይርጋ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- ሣሉኒ ኮንስትሩቶሪ ኤስ ፑ - ኤ - አልቀረቡም ተጠሪ፡- አቶ ትግለ ፍሬህይወት - አልቀረቡም መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው የደቡብ ብሓር ብሓረሰቦችና ሕዝቦች ክልል የየም ልዩ ወረዲ ፍርድ ቤትና የየም ልዩ ወረዲ የከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት አመልካች ሰኔ 1 ቀን 2001 ዓ.ም የተፃፈ የሰበር አቤቱታ በማቅረቡ ነው። ክርክሩ በመጀመሪያ የታየው በየም ልዩ ወረዲ ፍርድ ቤት ነው። በወረዲው ፍርድ ቤት ተጠሪ የአመልካች ሰራተኛ መሆኑን ገልፆ በዋሻ ውስጥ ሥራ በመሥራት ላይ እያለሁ ህዲር 4 ቀን 1999 ዓ.ም በባቡር ግጭት ምክንያት ከፍተኛ የአካል ጉዲት ደርሶብኛል። በአገር ውስጥ ህክምና ስከታተል የቆየሁ ቢሆንም የደረሰብኝ ጉዲት በአገር ውስጥ ከሚሰጠው ሕክምና በላይ መሆኑን በማረጋገጥ አምስት ድክተሮች ውጭ ሄጄ ሕክምና መከታተል ያለብኝ መሆኑን በማረጋገጥ ማስረጃ ሰጥተውኛል። ተከሳሽ /አመልካች/ ውጭ ሉያሣክመኝ ፈቃደኛ ባመሆኑ በውጭ አገር ህክምና እንድከታተል እንዱያደርግ ትእዛዝ ይሰጥልኝ በማለት ክስ አቅርቧል።
አመልካች ተጠሪ በአገር ውሰጥ አስራ ስምንት ጊዜ ኦፔሮሽን ያደረገና ህክምና የተከታተለ መሆኑን ገልፆ የውጭ አገር ሀኪሞች /ድክተሮች/ በሚመጡበት ሆስፑታል በአገር ውስጥ አለ። ተጠሪን ድክተሮቹ ጋር ቀርቦ እንዱታከም ብንጠይቀው ፈቃደኛ አልሆነም የውጭ አገር ህክምና ለመሸፈን በውል ያልተስማማን በመሆኑ የተጠሪ ክስ ውድቅ ይደረግልኝ በማለት ተከራክሯል። የወረዲው ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ማስረጃ ከሰማ በኋላ የአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 105 አሰሪው ሰራተኛ በሥራ ላይ ጉዲት ሲደርስበት የማሣከም ግዳታ እንዲለበት ከሚደነግግ በስተቀር ህክምናው በአገር ውስጥ ወይም በውጭ አገር መሆኑን ስለማይገልጽ አመልካች የሀኪሞች ቦርድ በሰጠው የሙያ አስተያየት መሰረት ውጭ አገር ልኮ የማሣከም ኃላፉነት አለበት በማለት ውሣኔ ሰጥቷል። አመልካች በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለከፍተኛው ፍርድ ቤት አቅርቧል። የየም ልዩ ወረዲ የከፍተኛው ፍርድ ቤት የወረዲው ፍርድ ቤት የሰጠው ውሣኔ የሚነቀፍበት የፍሬ ጉዲይ ወይም የህግ ስህተት የለም በማለት ይግባኙን በፍትሐብሕር ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 337 ሰርዞታል።
አመልካች ተጠሪ ታክሞ እንዱድን ያደረግነውን ጥረት ከግምት ውስጥ ሣያስገባ የህክምና ቦርደ ውሣኔ ግልጽነት ያጏደለው መሆኑን ሣያገናዝብና በአገር ውስጥ የተሻለ ህክምና ላሰጥ የሚችል የውጭ ድክተሮች የሚሰሩበት MCM የተባለ ሆስፑታል ልናሣክመው ፈልገን ተጠሪ እንቢተኛ መሆኑን ሣያገናዝብ አላግባብ ውጭ አገር ወስዲችሁ አሳክሙ በማለት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ ችልቱ ተጨማሪ ማስረጃዎን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.
377(3) መሰረት በመቀበል ውሣኔ እንዱሰጥልን በማለት አመልክቷል። ተጠሪ በበኩለ በአገር ውስጥ ባለ የህክምና ተቋሞች ታክሜ ከህመሜ ለመዲን ያልቻልኩ በመሆኑ በውጭ ሄጄ መታከም እንዲለብኝ የሀኪሞች ቦርድ አረጋግጧል።
ስለዚህ አመልካች ውጭ አገር ወስድ ያሣክመው በማለት የተሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የለበትም በማለት መልስ ሰጥቷል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር የቀረበው የጽሁፍ ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም ጉዲዩን መርምረናል።
ጉዲዩን እንደመረመርነው አመልካች ተጠሪን በውጭ አገር የማሣከም ግዳታና ኃላፉነት አለበት ወይስ የለበትም የሚለውን ጭብጥ መታየት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
ይህንን ጭብጥ እልባት ለመስጠት የአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 105 ድንጋጌ አሰሪው በሰራተኛው ላይ ያደረሰበት ጉዲይ በውጭ አገር የሚደረግ የህክምና ወጭ እንዱሸፍን ያስገድደዋል ወይስ አያስገድድም?
የሚለው ነጥብ መታየት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል። የአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 105 ድንጋጌ ቃልበቃል ሲነበብ “በሥራ ላይ ሚመጣ ጉዲት ለደረሰበት ሰራተኛ ለሚከተለት ህክምና አገልግልት የሚያስፈልግ ውጭ አሰሪው ይከፍላል
ድንጋጌው አሰሪው የመሸፈንና የመክፈል ግዳታ ያለበት በአገር ውስጥ ህክምና ተቋማት የሚደረገውን የህክምና ውጭ ብቻ ነው ወይስ በአገር ውስጥና በውጭ አገር የሚደረግ የህክምና ወጭ የሚለውን በግልጽ ምላሽ የሚሰጥ አይደለም።
አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 105 ድንጋጌ አገላለጽ ጠቅላላ መብቱ የተቀመጠ በመሆኑ አሰሪው ሰራተኛው ላይ በሥራው ላይ የሚደርስበትን ጉዲት የሚያወጣውን የውጭ አገር የህክምና ወጭ መሸፈን አለበት ወይስ የለበትም በሚለው ጥያቄ ግልጽ ምላሽ የማይሰጥ በመሆኑ ድንጋጌውን መተርጏም አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል።
አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 105 ድንጋጌ ለመተርጏም አዋጁን ሳያወጣ ህግ አውጭው የነበረውን ሀሳብና ሉያሣካው የሚፈልገውን ግብ ማገናዘብ አስፈላጊ ነው። ህግ አውጭው አዋጁን ያወጀው በአገሪቱ ውስጥ አሰሪና ሰራተኛ ግንኙነትና መሰረታዊ የሆኑ መብትና ግዳታዎች ለመቆጣጠር እንደሆነ በአዋጁ መግቢያ ገልፅታል። አዋጁ በአገሪቱ ውስጥ በየትኛውም ሥፍራና በማናቸውም ሁኔታ የተመሰረቱ የአሰሪና ሰራተኛ ግንኙነት ላይ እኩል ተፈፃሚነት እንዱኖረው ታስቦ የታወጀ በመሆኑ ሁለም አሰሪዎች ሰራተኛው በሥራ ላይ ለሚደርስበት ጉዲት የውጭ አገር ህክምና ወጭ እንዱሸፍኑ በማሰብ የአዋጁን አንቀጽ 105 ደንግጓል ብል ለመደምደም የሚቻል አይደለም። ስለዚህ ህግ አውጭው ማናቸውም አሰሪና ሰራተኛው በሥራ ላይ ለሚደርስበት ጉዲት በአገር ውስጥ የሚደረገውን የህክምና ወጭ የመሸፈን ግዳታና ኃላፉነት እንዲለበት በማሰብ ህግ አውጭው ድንጋጌውን አውጇል ተብል መተርጏም ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
በሁለተኛ ደረጃ አሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ ቁጥር 377/96 በአሰሪና ሰራተኛ ግንኙነት አሰሪው ለሰራተኛው ሉያከብር የሚገባውን ዝቅተኛ ደረጃ ጥበቃ የሚደነግግ ነው። ሰራተኞች ከአዋጅ ከተደነገገው ጥበቃ በላይ የተሻለ መብትና ጥቅም ለማስከበር ሰራተኞች በአዋጅ ቁጥር 377/96 የሥራ ውል ሲዋዋለ ወይም አንቀጽ 124 በሚደነግግው መሰረት ከአሰሪው ጋር በመደራደር የህብረት ሥምምነት መዋዋል አለባቸው። የውጭ አገር የህክምና ወጭ በአሰሪው የሚሸፈን መሆኑ የአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ ህግ ለሰራተኛው የሰጠው ዝቅተኛው ጥበቃ ነው ብል ለመደምደም አይቻልም። የአዋጁ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 105 አሰሪው ሰራተኛው በሥራ ላይ በሚደርስበት ጉዲት የአገር ወስጥ የህክምና ወጭ መሸፈን እንዲለበት በመደንገግ ዝቅተኛውን ጥበቃ ሰጥቷል። በውጭ አገር የሚደረግ የህክምና ወጭ በከፉል ወይም ሙለ በሙለ በአሰሪው መሸፈን ያለበት መሆኑ ከፍተኛ ጥበቃ ነው። ይኸም በመሆኑ ሰራተኞች ከአሰሪው ጋር በመደራደር በውል ወይም በህብረት ስምምነት ሉያስከብሩት የሚቻለት መብት እንጂ በህግ በሁለም አሰሪዎች ላይ ግዳታና ኃላፉነት ሆኖ ተደነገገ አይደለም። አመልካች ሰራተኞችን በውጭ አገር ለማሣከም ውል ያልተዋዋለ መሆኑ በሥር ፍርድ ቤት ተገልጿል። አመልካች ሰራተኞች ለሚደርስባቸው ጉዲት ከአገር ውጭ የህክምና ወጭ በሙለ ወይም በከፉል የሚሸፈን ግዳታ ያለበት መሆኑን የሚያረጋግጥ የህብረት ሥምምነት በአመልካችና በአመልካች ሰራተኞች መካከል የተደረገ መሆኑን የቀረበ ማስረጃ የለም። ስለሆነም አመልካች በተጠሪ ላይ የደረሰውን ጉዲት በውጭ አገር ለማሣከም ግዳታ ከህግ፣ ከውል ወይም ከህብረት ሥምምነት የመነጨ ሀላፉነት የላለበት በመሆኑ የየም ልዩ ወረዲ ፍርድ ቤትና የከፍተኛ ፍርድ ቤት አመልካች ተጠሪን ውጭ አገር ወስድ እንዱያሣክም የሰጡት ውሣኔና የህግ ትርጉም መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
አመልካች በሰበር አቤቱታውና ለሥር ፍርድ ቤት በቀረበው ክርክር መሰረት MCM ሆስፑታል ላልች የአገር ውስጥ የህክምና ተቋማት የማሣከምና ላልች በአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ ቁጥር 377/96 በሚደነግገው መሰረት የተጠሪን መብትና ጥቅም የመጠበቅ ኃላፉነት ያለበት ሲሆን ከዚህ ውጭ አገር ወስድ የማሣከም ኃላፉነት የለበትም በማለት ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የደቡብ ብሓረሰቦችና ሕዝቦች ክልል የየም ልዩ ወረዲ ፍርድ ቤት እና የየም ልዩ ወረዲ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሣኔ ተሽሯል።
አመልካች ተጠሪ ውጭ አገር የማሣከም ኃላፉነት የለበትም ብለናል።
አመልካች ተጠሪን በ MCM ሆስፑታልና ላልች የአገር ውስጥ የህክምና ተቋማት የማሣከምና የተጠሪን መብትና ጥቅም በአዋጅ ቁጥር 377/96 መሰረት የመጠበቅ ግዳታ አለት ብለናል።
በዚህ ፍርድ ቤት የወጣውን ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ ለየራሳቸው ይቻለ።
ይህ ፍርድ በፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት በሙለ ድምጽ ተሰጠ።
No topics extracted.