No summary available.
ግንቦት 13 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ሂሩት መለሰ ተሻገር ገ/ስላሴ ታፈሰ ይርጋ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- የኢትዮጵያ ኤላትሪክ ኃይል ኮርፕሬሽን - የቀረበ የለም ተጠሪ፡- እነ አቶ ታጁ አባጋሮ( 21 ሰዎች ) - የቀረበ የለም
በዚህ መዝገብ የቀረበው የስራ ክርክርን የሚመለከት ጉዲይ ነው። ተጠሪዎች በስር ፍ/ቤት ባቀረቡት ክስ ከተቀጠሩበት ከ1996 ዓ.ም ጀምሮ መታወቂያ፣የበረሃ አበል፣ነፃ የመብራት አግልግልት፣የደሞዝ ጭማሪ፣የቦነስ መብት፣ጥንድ የስራ ልብስ፣የካሳ መብት፣የአመት እረፍት መብት፣የቅዲሜ ክፍያ መብት፣የጡረታ መብት እንዱሁም በጥር ወር 2000 ዓ.ም የተደረገው 20% የደሞዝ ጭማሪ የማግኘት መብት እንዱጠበቅላቸው ጠይቀዋል። አመልካችም የቋሚነትና የጡረታ መብት ጥያቄ የክስ ምክንያት የለውም፣ክሱ የወል የስራ ክርክር ነው፣ጥያቄው በይርጋ ቀሪ ነው የሚለ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያዎችን ካነሳ በኋላ ተጠሪዎች ለተወሰነ ጊዜ የተቀጠሩ ሰራተኞች በመሆናቸው በህብረት ስምምነቱ መሰረት ጥቅሞችን ማግኘት አይችለም 20% የደሞዝ ጭማሪ ተከለከልን ያለት ሃሰት ነው በማለት መልስ አቅርቧል። ጉዲዩ የቀረበለት የፋ/መ/ደረጃ ፍ/ቤት ጉዲዩን ተመልክቶ ክርክሩ የግል የስራ ክርክር ነው፣ጥያቄውም የክስ ምክንያት አለው፣6 ወር ያለፈው የደሞዝ ጭማሪና አንድ አመት ያለፊቸው ላልች የመብት ጥያቄዎች በይርጋ ቀሪ ይሆናለ ካለ በኋላ ዋናው ጉዲይ በተመለከተ ደግሞ በግራ ቀኙ በተደረገው የቅጥር ውል የጊዜ ገደቡ መቀመጡ ብቻ ተጠሪዎች ለተወሰነ ጊዜ እንደተቀጠሩ አያስቆጥራቸውም በማለት ተጠሪዎች ላልተወሰነ ግዜ የተቀጠሩ ሰራተኞች ስለመሆናቸው ግምት በመውሰድና በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 14 መሰረት በሰራተኞች መሃከል ልዩነት መፍጠር ስለማይቻል ለተጠሪዎች መታወቂያ የማግኘት፣የበረሃ አበል፣ነፃ የመብራት አግልግልት፣የደሞዝ ጭማሪ፣የቦነስ መብት፣የደንብ ልብስና የዓመት እረፍት የማግኘት መብታቸው እንዱጠበቅላቸውና 20% ደሞዝ ጭማሪ እንዱከፈላቸው ወስኗል። አመልካች በዚህ ውሳኔ ላይ ለፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ ያቀረበ ቢሆንም ፍ/ቤቱ ግራ ቀኙን አከራክሮ የስር ፍ/ቤትን ውሳኔ አጽንቷል።
የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሳኔ ላይ ሲሆን የአመልካች ቅሬታ በአጭሩ ሲጠቃለል፣ጥያቄው የወል የስራ ክርክር ነው፣ክሱ በይርጋ ቀሪ ነው፣የአ/ቁ. 377/96 አንቀጽ 14 ለተያዘው ጉዲይ አግባብነት የለውም፣ተጠሪዎች ለተወሰነ ጊዜ የተቀጠሩ በመሆኑ የጠየቁት መብቶችና ጥቅሞች ሉያገኙ አይችለም በመሆኑም የስር ፍ/ቤቶች ውሳኔ ሉሻር ይገባዋል፣የሚል ነው። ችልቱም አመልካች በሰበር አቤቱታው ያነሳቸውን ቅሬታዎች ከስር ፍ/ቤት ውሳኔና ከህጉ ጋር አገናዝቦ ለመመርመር አቤቱታው ለሰበር ችልት እንዱቀርብ አድርጓል። በዚህ መሰረት የግራ ቀኙ የቃል ክርክር የተሰማ ሲሆን ችልቱም መዝገቡን እንደሚመለከተው መርምሯል።
በቅድሚያ የተጠሪዎች ጥያቄ የወል የስራ ክርክር በመሆኑ ፍ/ቤቱ ጉዲዩን ለማየት የስረ-ነገር ስልጣን የለውም የሚለውን የአመልካች ቅሬታ ተመልክተናል። የተጠሪዎች ጥያቄ ላልች ሰራተኞች የሚያገኙት ጥቅማ-ጥቅሞችና መብቶች ይጠበቁልን የሚል ነው። አመልካች የሚከራከረው በሕብረት ስምምነቱ መሰረት በተጠሪዎች የተጠየቁት ጥቅማ ጥቅሞች የሚከፈለው ላልተወሰነ ጊዜ ለተቀጠሩ ሰራተኞች በመሆኑና ተጠሪዎች ለተወሰነ ጊዜ የተቀጠሩ በመሆናቸው ጥያቄው ተቀባይነት የለውም በማለት ነው። ቋሚ ሰራተኞች መሆናቸው ከተረጋገጠ የጠየቁትን መብቶችና ጥቅሞች ሉገኙ የማይገባበትን ላላ ምክንያት አመልካች አልገለጸም። በመሆኑም የክፍያ ጥያቄው በተጠሪዎች የቅጥር ውለ ይዘት የሚወሰን ስለሆነና ውጤቱም በተጠሪዎቹ ላይ ተወስኖ የሚቀር እንጂ ለላልች ሰራተኞች ላይ አለታዊ ወይም አዎንታዊ ተጽኖ የሚያሳድር ስላልሆነ ጥያቄው የወል የስራ ክርክር ነው ለማለት የሚቻል ባለመሆኑ የስር ፍ/ቤት ጉዲዩን የማየት ስልጣን አለኝ በማለት መወሰኑ በአግባቡ ሆኖ አግኝተነዋል።
የይርጋውን መቃወሚያ በተመለከተ ተጠሪዎች የጠየቁት የመብት ጥያቄዎች ቀጣይነት ያላቸው በመሆኑ 6 ወር ያለፈው ደሞዝ ጭማሪና አንድ አመት ያለፊቸው ላልች የጥቅም ጥያቄዎች ብቻ በይርጋ ቀሪ መደረጋቸው ተገቢ ሆኖ አግኝተነዋል።
በመቀጠል ችልቱ የተመለከተው ተጠሪዎች ለተወሰነ ግዜ የተቀጠሩ መሆን አለመሆኑን ነው። ስር ፍ/ቤት በግራ ቀኙ የተደረገው የስራ ውል የጊዜ ገደብ ከማስቀመጡ በቀር በአዋጁ አንቀጽ 10 ስር በተዘረዘሩት ምክንያቶች መቀጠራቸውን ስለማይናገር ተጠሪዎች ላልተወሰነ ጊዜ የተቀጠሩ መሆኑን ግምት ወስዶል። ችልቱም ለትክክለኛ ፍትህ አሰጣጥ እንዱያመቸው ተጠሪዎች የተቀጠሩበትን የቅጥር ውል የስር ፍ/ቤትን መዝገብ በማስቀረብ ተመልክቷል። የቅጥር ውለ በአ/ቁ. 377/96 አንቀጽ 10 መሰረት ለተወሰነ ጊዜ ወይም ለተወሰነ ስራ ለሚቀጠሩ ሰራተኞች ተፈፃሚ የሚሆን ስለመሆኑ በርእሱ አመልክቶ በዝርዝር ውስጥ ተጠሪዎች የተቀጠሩበት የጊዜ ገደብ፣ የተቀጠሩበት ፔሮጀክት እንዱሁም የተቀጠሩት በአዋጅ አንቀጽ 10 መሰረት በጊዜያዊነት በመሆኑ መብቶቻቸውና ጥቅማቸው በቅጥር ውለ የተመለከቱት ብቻ መሆናቸውን ላልችንም ዝርዝር ሁኔታዎች አካቶ የያዘ ነው። አንድ ሰራተኛ የተቀጠረው ላልተወሰነ ጊዜ ስለመሆኑ የአዋጁ አንቀጽ 9 ግምት የሚወስድ ሲሆን አሰሪው የስራ ውለ ለተወሰነ ጊዜ ወይም ስራ ነው የሚል ከሆነ ይህንኑ የማስረዲት ሸክም አለበት። አመልካች ተጠሪዎች ለተወሰነ ጊዜ የተቀጠሩ ስለመሆናቸው ለማስረዲት ያቀረበው የስራ ውለን ነው። በእርግጥ የስር ፍ/ቤት እንዲለው በውለ ላይ የግዜ ገደብ መጠቀሱ ብቻውን ሰራተኛው ለተወሰነ ግዜ የተቀጠረ ነው ወደሚለው መደምደሚያ ሉያደርስ የሚችል አይደለም። ከጊዜ ገደቡ ባሻገር ግራ ቀኙ ውለን ሲዋዋለ ሃሳባቸው ምንድን ነበር የሚለውን መመርመር ተገቢ ይሆናል። በዚህ መሰረት ውለን ስንመረምር የተጠሪዎች ቅጥር በጊዜ ገደብ ከመወሰኑ በተጨማሪ የተቀጠሩት ለግልገል ግቤ ኃይል ማመንጫ ፔሮጀክት ለደነባ ሳይት መሆኑ በግልጽ ተመልክቷል። ከዚህ በተጨማሪ በውለ አንቀጽ 4.1.3 ስር ተጠሪዎች ለተወሰነ ጊዜ የተቀጠሩ በመሆናቸው መብቶቻቸውና ጥቅሞቻቸው የሚወሰኑት በቅጥር ውለ በተዘረዘሩት መሰረት ብቻ መሆኑ ሰፈሮ ይገኛል። ይህም የሚያሳየው ምንም እንኳን በውለ በግልጽ ባይመለከትም ተጠሪዎች ሲቀጠሩ የነበረው የግራ ቀኙ ሃሳብ ተጠሪዎች በውለ ላይ በግልጽ ለተመለከተው የፔሮጀክት ስራ ብቻ የተቀጠሩ መሆኑን መረዲት ይቻላል። ይህም በአዋጅ አንቀጽ 10/1/ሀ/ ሥር የሚወድቅ የቅጥር ሁኔታ ነው። በመሆኑም በአመልካችና በተጠሪዎች መሃከል የተደረገው የቅጥር ውል ይዘት ሲታይ ተጠሪዎች ለተወሰነ ስራ የተቀጠሩ በመሆኑ የስር ፍ/ቤቶች አጠቃላይ የውለን ይዘት ሳይመረምሩ ተጠሪዎች ላልተወሰነ ጊዜ የተቀጠሩ ሰራተኞች ናቸው በማለት የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ሆኖ አግኝተነዋል።
ተጠሪዎች ለተወሰነ ጊዜ የተቀጠሩ ሰራተኞች ናቸው ከተባለ የጠየቋቸውን ጥቅማ ጥቅሞች እና መብቶች ሉያገኙ ይገባል ወይ? የሚለውን ቀጥለን ተመልክተናል። አመልካች ከስር ጀምሮ የሚከራከረው በህብረት ስምምነቱ መሰረት ተጠሪዎች የጠየቋቸው የመብት ጥያቄዎች ለቋሚ ሰራተኞች የሚሰጡ ናቸው በማለት ነው። ተጠሪዎችም ቢሆኑ ለላልች ሰራተኞች ስለሚከፈል ለእነሱም እንዱከፈላቸው ከመጠየቅ ባለፈ እነዚህ የጥቅማ ጥቅም እና መብቶች ለተወሰነ ጊዜ ወይም ስራ ለተቀጠሩ ሰራተኞችም ሉከፈል የሚገባበት የውልም ሆነ የሕግ መሰረት ያላቸው ስለመሆኑ ያቀረቡት ክርክር የለም። ከፍ ሲል እንደተመለከተው ተጠሪዎች ሉያገኙ የሚችለት ጥቅምም ሆነ መብቶች በውለ ላይ የተዘረዘሩትን ብቻ መሆናቸው በቅጥር ውለ ላይ ተመልክቷል። በልላ በኩል በአዋጅ 377/96 አንቀጽ 14/ረ/ ስር የተመለከተው ልዩነት ያለመፍጠር ግዳታ በድንጋጌው እንደተመለከተው በብሓረሰብ፣በፆታ፣ በሐይማኖት፣በፕለቲካ አመለካከት እና እነዚህን የመሳሰለትን ላልች ሁኔታዎችን የሚመለከት እንጂ የቅጥር ውልን መሰረት በማድረግ ልዩነት እንዲይፈጠር የማይከለክል ስለመሆኑ ይህ የሰበር ችልት በመ/ አስገዲጅ የሕግ ትርጉም ሰጥቶበታል። በመሆኑም አመልካች በተጠሪዎች የጠየቋቸውን የጥቅማ ቅጥምና ላልች የመብት ጥያቄዎች የቅጥር ሁኔታን መሰረት በማድረግ ልዩነት እንዲይፈጥር ሕጉ ክልከላ አላደረገበትም። በተጠሪዎች የክስ ማመልከቻ ላይ የተጠየቁት ነገሮች በህብረት ስምምነቱ መሰረት ለቋሚ ሰራተኞች ብቻ የሚከፈለ ስለመሆኑ በአመልካች በኩል የቀረበውን ክርክር ተጠሪዎች አላስተባበለም። በመሆኑም ተጠሪዎች በክሳቸው የጠየቋቸውን ጥቅማ ቅጥምና ላልች መብቶች ለመጠየቅ የሚያስችል ከሕግም ሆነ ከውል ያገኙት መብት መኖሩን ስላረጋገጡ ጥያቄአቸው ተቀባይነት የለውም። የስር ፍ/ቤቶችም ተጠሪዎች ላልተወሰነ ጊዜ የተቀጠሩ ሰራተኞች ናቸው በማለት በጥያቄአቸው መሰረት እንዱፈፀምላቸው የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ አግኝተነዋል።
የፋ/መ/ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 24365 ሐምል 9 ቀን 2000 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ እና የፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 69792 ታህሣሥ 27 ቀን 2001 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ ተሽሯል።
ተጠሪዎች ለተወሰነ ጊዜ የተቀጠሩ ሰራተኞች በመሆናቸው ክሳቸው ተቀባይነት የለውም ብለናል።
ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።
የስር ፍ/ቤት መዝገብ ይመለስ።
No topics extracted.