No summary available.
ግንቦት 13 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ሂሩት መለሰ ተሻገር ገ/ስላሴ ታፈሰ ይርጋ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- የአዱስ አበባ ቄራዎች ድርጅት - አልቀረቡም ተጠሪ፡- አቶ አበበ ተፈራ ይልማ - ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትና የከፍተኛው ፍርድ ቤት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት አመልካች ኀዲር 2 ቀን 2002 ዓ.ም የተፃፈ የሰበር አቤቱታ ስላቀረቡ ነው። ክርክሩ በመጀመሪያ የታየው በፋዳራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ነው። በፋዳራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ተጠሪ ከሳሽ አመልካች ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል። ተጠሪ በአመልካች ድርጅት ውስጥ በሥጋ አከፊፊይ ቡድን መሪነት ሲያገለግል መቆየቱን ገልፆ አመልካች ከግንቦት 1 ቀን 2001 ዓ.ም ጀምሮ ለሥራው ብቁ አይደለህም በማለት ወደ በፋብልት ሰራተኛ 11 አዛውረውኛል። ስለዚህ ወደ ነበርኩበት የሥራ መደብ እንዱመልሰኝ ይወሰንልኝ በማለት ክስ አቅርበዋል። አመልካች በተከሳሽነት ቀርቦ የድርጅቱ ደንበኞች ቁጥር በመቀነሱ ምክንያት በተደረገው ጥናት በእርድና ሥርጭት ክፍል ችግር ያለበት መሆኑ ተረጋግጧል ስለዚህ ሥራና ሰራተኛን ለማገናኘት ሰራተኞችን በህብረት ስምምነቱ መሰረት በመመደብ እየሰራን የምንገኝ ስለሆነ የጣስነው ሕግ የለም በማለት ተከራክሯል።
ፍርድ ቤቱ ግራ ቀኙ የተማመኑ በመሆኑ ስለጥናቱ ለማስረዲት የተዘረዘሩ ምስክሮች መስማትም ሆነ የጥናት ሰነደን አስቀርቦ ማየት አስፈላጊ ሆኖ አላገኘውም በማለት በጥናቱ የከሳሽ (ተጠሪ) ችልታ ምንም ሳይሆን ጠቅላላ የድርጅቱ ችግር የተገለፀ በመሆኑ አመልካች ተጠሪን የሥራ መደብ በማዛወር ማሰራቱ ተገቢ አይደለም። ስለዚህ አመልካች ተጠሪን ወደ ቀድሞው የእርድና የሥጋ ስርጭት አገልግልት የቡድን መሪነት የሥራ መደብ እንዱሰራ በማለት ወስኗል።
አመልካች በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለከፍተኛው ፍርድ ቤት ያቀረበ ቢሆንም የከፍተኛው ፍርድ ቤት ይግባኙን በፍታብሓር ሥነ ሥርአት ህግ ቁጥር 337 መሰረት ሰርዞታል።
አመልካች ሰራተኞችን የበለጠ ውጤታማ በሚሆኑበት የሥራ መደብ ጥቅምና ደረጃቸውን ሣይቀንስ አዛውሮ ማሰራት የአሰሪው መብትና ሥልጣን ነው። ተጠሪ አሁን የተመደበበትና የተዛወረበት የሥራ መደብ ደረጃ ስድስት የሆነና ተመሣሣይ ነው። ስለዚህ የበታች ፍርድ ቤት አሰሪው ሰራተኞቹን አዛውሮ የማሰራት ህጋዊ ሥልጣንና በህብረት ስምምነቱ አንቀጽ 12 ንኡስ አንቀጽ 2 የተደነገገውን በመተላለፍ የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝን በማለት አመልክቷል። ተጠሪ በበኩለ በነበርኩበት የሥራ መደብ የሥራ ችልታ ማነስ ያለበኝ ስለመሆኑ ያቀረበው ማስረጃ የለም። ስለዚህ የበታች ፍርድ ቤቶች የአዋጅ ቁጥር 377/96 እና የሕብረት ስምምነቱን ድንጋጌዎች በማገናዘብ የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የለበትም በማለት በጽሐፍ መልስ ሰጥቷል። አመልካች የመልስ መልስ አቅርበዋል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር የቀረበው ክርክር ከላይ የገለፀው ሲሆን እኛም መዝገቡን መርምረናል።
መዝገቡን እንደመረመርነው በአመልካች ድርጅት አግልግልት የሚፈልጉ ደንበኞች መቀነስ ዋናው ምክንያት የእርድና የሥጋ ስርጭት አገልግልት የሚሰጠው ክፍል ችግር ያለበት መሆኑ በጥናት ተረጋግጧል። ምንም እንኳን አመልካች ከሃያ በላይ የሚሆኑ የእርድና የሥጋ ስርጭት አገልግልት የቡድን መሪዎች ያለትና ለድክመቱ ተጠሪ በግል ኃላፉ ናቸው ባይባልም አመልካች የጥናትቱን ውጤት መነሻ በማድረግ ችግሩን ለማስወገድ አስፈላጊ ነው የሚለውን አስተዲደራዊ ማስተካከያ በመውሰድ ድርጅቱን ትርፊማነት ማስቀጠል ይገባዋል።
አመልካች ተጠሪን ከነበሩበት የሥራ መደብ ተመሣሣይ ደረጃ ደመወዝና ጥቅም ወደአለው የሥራ መደብ አዛውሮ ለማሰራት የወሰደው አስተዲደራዊ ማስተካከያ በአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 13 ንኡስ አንቀጽ 2 መሰረት ያከናወነው ተግባር ነው። ተጠሪ አመልካች በሕጉ በግልጽ የተፈቀደለትን አስተዲደራዊ ተግባር እንዲይፈጽም ክስ የሚያቅርብበት ምክንያት የላለ ሲሆን በተመሣሣይ የሥራ መደብ ተዛውሮ በመሥራቱ የተነካበት መብትና ጥቅም የለም።
ስለሆነም አመልካች ላልቹ የእርድና የሥጋ ሥርጭት የቡድን መሪዎች ሣይዛወሩ እኔ ተዛወርኩ በሚል ምክንያት በመነሣሣት ያቀረበው ክስ የክስ ምክንያት የላለው በመሆኑ ከጅምሩ የበታች ፍርድ ቤቶች በፍታብሓር ሥነ ሥርአት ሕግ ቁጥር 33 ንኡስ አንቀጽ እና በፍታብሓር ሥነ ሥርአት ሕግ ቁጥር 231 መሰረት መዝጋት ነበረባቸው።
የሥር ፍርድ ቤት በአመልካች የድርጅት አስተዲደር ሥልጣን በመጋፊት ተጠሪ ወደ ላላ ተመሣሣይ ደረጃ ወደ አለው የሥራ መደብ በመዛወራቸው የቀረባቸው የደመወዝ ወይም ላላ ህጋዊ ጥቅም ያለመሆኑን ባላሥረዲበት ሁኔታ ላልቹ የቡድን መሪዎች ወደ ላላ የሥራ መደብ አልተዛወሩም፣ ተጠሪ የችልታ ማነስ ያለበት ስለመሆኑ አላስረዲህም በሚል ምክንያት አመልካች ተጠሪን ወደ ቀድሞው የሥራ መደብ አዛውሮና መድቦ እንዱያሰራ የሰጠው ውሣኔ በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 13 ንኡስ አንቀጽ 2 የሚጥስና መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው በማለት ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የከፍተኛው ፍርድ ቤትና የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሰጡት ውሣኔ ተሽሯል።
አመልካች የተጠሪ የሥራ ደረጃ ደመወዝና ጥቅም በማይነካ ሁኔታ ወደ ላላ የሥራ መደብ አዛውሮ የማሰራት ሥልጣን አለው ብለናል።
በዚህ ፍርድ ቤት የወጣውን ወጭና ኪሳራ ግራ ቀኙ ለየራሳቸ ይቻለ።
ይኸ ፍርድ በፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት በሙለ ድምጽ ተሰጠ።
No topics extracted.