No summary available.
መ/ ግንቦት 17 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ሂሩት መለሰ ተሻገር ገ/ስላሴ ታፈሰ ይርጋ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- አቶ ደሬሳ ኮቱ - ቀረቡ ተጠሪ፡- የአምቦ ገበሬዎች የህብረት ሥራ ዩኒየን - ነ.ፈጅ አልቀረቡም መዝገቡ በአዲሪ የተቀጠረው ለምርመራ ሲሆን መርምረን ፍርድ ሰጥተናል።
ይህ የሰበር ጉዲይ አፈፃፀምን የሚመለከት ነው።
ለአፈፃፀሙ መነሻ በሆነው የአሰሪና ሰራተኛ ክርክር ጉዲይ ግራ ቀኙ ተከራክረው በተጠሪ በኩል የተደረገው የሥራ ስንብት ህግ ከደነገገው ውጭ ስለሆነ አመልካች ከልዩ ልዩ ክፍያዎች ጋር ወደ ሥራው ይመለስ ተብል ተወስኗል።
የአሁን አመልካች የተወሰነለትን ውሳኔ ለማስፈፀም የአፈፃፀም ክስ አቅርቧል። የጠየቀውም ዲኝነት ወደ ሥራ ለመመለስ እንደማይችል ገልፆ በምትኩ በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 43(4) መሰረት ካሣ እና የተወሰነለት ልዩ ልዩ ክፍያዎች እንዱከፈለት ጠይቋል።
አፈፃፀሙን የያዘው የሥር ፍ/ቤትም በአንቀጽ 43(4) መሰረት ለአመልካች እንዱከፈለው የተወሰነ ነገር የለም።
በውሳኔው ከተገለፀው ውጭ ማስፈፀም አይቻልም በማለት ወደ ሥራ መመለሴ ቀርቶ በምትኩ ካሣ ይከፈለኝ የሚለውን ውድቅ አድርጎ ላልች ክፍያዎች እንዱፈፀሙለት አዟል።
የአሁን አመልካች የጠየቀው የካሣ ክፍያ ውድቅ መደረጉ አግባብ አለመሆኑን በመግለፅ በየደረጃው በይግባኝ እና በክልለ ሰበር ሰሚ ችልት ዲኝነት ቢጠይቅም በተመሳሳይ ምክንያት ጥያቄው ተቀባይነት ሳያገኝ ቀርቷል።
ይህ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም በአሰሪው ችግር ምክንያት ወደ ሥራ ለመመለስ አለመቻለ ከታወቀ በፊንታው በአዋጅ አንቀጽ 43 መሰረት የካሣ ክፍያ ሉከፈለኝ ሲገባ ይህ መታለፈ የህግ ስህተት በመሆኑ ይታረምልኝ የሚል ሲሆን፤ በዚህ ቅሬታ መነሻ ሁለቱም ወገኖች በሰበር የቃል ክርክራቸውን አሰምተዋል። እኛም ጉዲዩን ተመልክተን እንደሚከተለው ተርጉመናል።
በሥር ፍ/ቤትም ሆነ በየደረጃው ባለት ይግባኝ ሰሚውና ሰበር ሰሚው ችልት የፍርድ ሐተታ ላይ እንደተገለፀው አፈፃፀም የፍርድን ይዘት መሰረት ሉያደርግ ይገባል። በአፈፃፀም ጉዲይ ከፍርድ ይዘት ውጭ መጨመርም ሆነ መቀነስ እንደማይቻል ግልፅ ነው። ይሁን እንጂ አሁን በተያዘው ጉዲይ የግራ ቀኙ ክርክር የመነጨው ከሥራ ግንኙነት ሲሆን የሥራ ግንኙነቱም በአዋጅ ቁጥር 377/96 በሆነው የአሰሪና ሰራተኛ ህግ የሚገዛ ነው። በዚህም ህግ አንቀጽ 43/3/ ላይ አከራካሪ የሆነው ስንብት ህግ ከደነገገው ውጭ ሆኖ በመገኘቱ ወደ ሥራው እንዱመለስ የተፈረደለት ሰራተኛ ወደ ሥራ ለመመለስ ፈቃደኛ ካልሆነ የሥራ ክርክሩን የሚያየው ችልት መመለሱ ቀርቶ በምትኩ ካሣ ተከፍልት እንዱሰናበት በማድረግ ሉወሰን እንደሚቻል ተደንግጓል። ከዚሁ ድንጋጌ ይዘት አንፃር ይኸው መብት ተፈፃሚ ላሆን የሚችለው ወደ ሥራ እንዱመለስ ከተፈረደለት በኋላ እንደመሆኑ መጠን ይህ የሰራተኛ አማራጭ የሆነው መብት ተፈፃሚ የሚያደርገው ችልት ፍርደን በማስፈጸም ላይ የሚገኘው ችልት ስለመሆኑ እንጂ ቀድሞ ፍርደን የፈረደው ችልት ላሆን አይችልም ወደ ሚለው ትርጓሜ ያደርሰናል።
ስለሆነም የሥር ፍ/ቤቶች በዚሁ ድንጋጌ መሰረት ሰራተኛው በእራሱ ምርጫም ሆነ በአሰሪው ችግር ምክንያት እንደፍርደ ወደ ሥራ ለመመለስ ካልፈለገ ስንብቱ ህገ-ወጥ ነው ተብል ወደ ሥራው እንዱመለስ ፍርድ ማግኘቱ ከተረጋገጠ በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 43(3) መሰረት በምትክነት በሰጠው መብት መሰረት በመመለሱ ፊንታ ካሣ ሉከፈለው ይገባል፤ ይህንንም የሚያስከፍለው አፈፃፀሙን የያዘው ችልት ሆኖ እያለ ይህንኑ ድንጋጌ በማለፍ ከተፈረደው ፍርድ ውጭ በመውጣት ማስፈፀም አይቻልም በማለት የአመልካችን የካሣ ክፍያ ጥያቄ ውድቅ በማድረግ የሰጡት ዲኝነት መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ አግኝተነዋል።
የአፈፃፀም ክሱን በማመልከት ወደ ሥራ በመመለስ ፊንታ ካሣ እንዱከፈል ውሳኔ አላረፈበትም በሚል ምክንያት የአምቦ ወረዲ ፍ/ቤት በመ/ በ12/5/2001፣ የከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ በ17/11/2001 የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት በፊይል በ28/3/2002 ዓ.ም የሰጠውን ዲኝነት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 348/1/ መሰረት ሽረናል።
በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 43/3/ መሰረት እንደተደነገገው ወደ ሥራ እንዱመለስ የተፈረደለት ሰራተኛ ወደ ሥራ አለመመለሱ ከታወቀ በምትኩ ካሣ የማግኘት መብት ያለው ስለሆነ ሉከፈለው ይገባል ብለናል። በመሆኑም ሉከፈል የሚገባውን የካሣ መጠን በአንቀጽ 43/4/ መሰረት አስልቶ ክፍያውን ያስፈፅም ብለናል። ይፃፍ።
ወጭና ኪሣራ ይቻቻለ። መዝገቡ ተዘግቷል።
No topics extracted.