No summary available.
መ/ ግንቦት 19 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ሂሩት መለሰ ተሻገር ገ/ስላሴ ታፈሰ ይርጋ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- ፉንፉኔ የቤትና የቢሮ እቃዎች ፊብሪካ ኃ.የተ.የግል ማህበር - ነ/ፈጅ ወ/ዮሐንስ ይርጉ - ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ደጃ ደምሴ ጎበና - ወኪል ጥሩነሽ ዘውዳ ቀረቡ መዘገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ የአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ ቁጥር 377/96“ን” መሰረት ያደረገ ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ ተጠሪ ባሁኑ አመልካች ላይ በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመሰረቱት ክስ መነሻ ነው። የክሱ ይዘትም ባጭሩ ከአመልካች ጋር የመሰረቱትን የአሰሪና ሰራተኛ ግንኙነት ውል በራሳቸው ፈቃድ ያቋረጡ መሆኑን ገልፀው ስራ ሰርተው ያልተከፈላቸውን የሐምል ወር 2000 ዓ.ም ደመወዝ አመልካች የፔሮቪደንት ፈንድ ክፍያ እና ክፍያው ለዘገየበት ክፍያ እንዱከፈላቸው ይወሰንላቸው ዘንድ ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው። የአሁኑ አመልካች ለክሱ በሰጠው መከላከያ መልስም ከተጠሪ ጋር የስራ ውል ግንኙነት የነበረው መሆኑንና ተጠሪ ግንኙነቱን በገዛ ፈቃዲቸው ያቋረጡ መሆኑን እንዱሁም የፔሮቪደንት ፈንድ ክፍያ ሳይከፈላቸው የቀረና የዘገየ መሆኑን ሳይክድ ክፍያው ያልተፈፀመው ተጠሪ የተረከቡትን ንብረት በአግባቡ ያልመለሱና ጉድለት የታየባቸው መሆኑን ጠቅሶ ክሱ ውድቅ ላሆን ይገባል ሲል ተከራክሯል። ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ክርክር ከመረመረ በኋላ አመልካች በተጠሪ ላይ ጉድለት ታይቷል የሚል ከሆነ ዲኝነት ከፍል በልላ ክስ ከሚጠይቅ በስተቀር የስራ ስንብት ክፍያውን አልከፍልም ለማለት አይችልም የሚል ምክንያት ይዞ የአመልካችን ክርክር ውድቅ አድርጎ አመልካች ለተጠሪ የሐምል ወር 2000 ዓ.ም ደመወዝ፣ የፔሮቪደንት ፈንድ ክፍያ እንዱከፍላቸውና ስራ ልምድ ምስክር ወረቀት እንዱሰጣቸው ሲል ወስኗል። በዚህ ውሳኔ አመልካች ባለመስማማት ይግባኙን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቢያቀርብም ይግባኙ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 337 መሰረት ተሰርዞበታል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስቀየር ነው።
የአመልካች ጠበቃ የካቲት 14 ቀን 2001 ዓ.ም በተጻፈ አንድ ገፅ የሰበር አቤቱታ በበታች ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ላይ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈፅሟል የሚለበትን ምክንያት ዘርዝረው አቅርበዋል። ይዘቱም ባጭሩ ተጠሪ በስራ ምክንያት የተረከቧቸውን ንብረቶች ያጎደለ በመሆኑ ክፍያውን አመልካች በወቅቱ ያለመፈፀሙ በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 36 መሰረት ሕጋዊ ሆኖ እያለ የአመልካች ክርክር ታልፍ ክፍያውን እንዱፈፅም መደረጉ ያላግባብ ስለሆነ ሉታረም የሚገባው ነው በማለት መከራከራቸውን የሚያሳይ ነው። አቤቱታው ተመርምሮም በሰበር ችልቱ ላታይ ይገባዋል ተብል የተጠሪ ወኪል ቀርበው መጋቢት 30 ቀን 2002 ዓ.ም በተጻፈ ማመልከቻ መልሳቸውን ሰጥተዋል። የመልሳቸው ይዘትም ባጭሩ አመልካች ተጠሪ አጎደለ ለተባለው ንብረት ላላ የፍትሐብሕር ክስ መስርቶ በክርክር ላይ ያለ መሆኑን ገልጸው በዚህ ጉዲይ የተሰጠው ውሳኔ ግን ሉጸና መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የላለበት በመሆኑ ሉፀና ይገባል ሲለ መከራከራቸውን የሚያሳይ ነው። የአመልካች ነገረ ፈጅ በበኩላቸው ሚያዚያ 15 ቀን 2002 ዓ.ም በተፃፈ አንድ ገፅ ማመልከቻ የመልስ መልሳቸውን ሰጥተዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርከር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
እንደመረመረውም ተጠሪ በስራ ምክንያት የተረከቧቸውን ንብረቶች ያጎደለ በመሆኑ ጉድለቱን ሳያወራርደ የሚፈፀም ክፍያ የለም በማለት ገልጾ ያቀረበው ክርክር ታልፍ አመልካች ክፍያዎችን እንዱከፍል መወሰኑ ባግባቡ መሆን ያለመሆኑ በጭብጥነት ላታይ የሚገባው ሆኖ አግኝቶታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው ተጠሪ ከአመልካች ጋር የመሰረቱትን የስራ ግንኙነት በገዛ ፈቃዲቸው ያቋረጡ መሆኑን፣ ተጠሪ አመልካች ሉከፈለኝ ይገባል በማለት ዲኝነት የጠየቁት የፔሮቪደንት ፈንድ ክፍያ እና ስራ ሰርተው ያልተከፈላቸው የሐምል ወር 2000 ዓ.ም ደመወዝ መሆኑን፣ አመልካች ለተጠሪ ክፍያዎችን አልከፍልም በማለት የሚከራከረው ተጠሪ በስራ ምክንያት የተረከቧቸውን ንብረቶችን ያጎደለ በመሆኑ የማወራረድ ግዳታ ያለባቸው መሆኑን በመጥቀስ ነው።
በመሰረቱ በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 36 ስር የስራ ውል ሲቋረጥ የሰራተኛው ደመወዝና ከደመወዝ ጋር የተያያዙ ክፍያዎች ሁለ በሰባት የስራ ቀናት ውስጥ መከፈል ያለበት ሲሆን የክፍያው ጊዜ ሉራዘም የሚችለው ሰራተኛው ከአሰሪው የተረከበውን ንብረት የማስረከብ ወይም የሚፈለግበትን ማናቸውንም ሂሳብ በማወራረድ የራሱ ጥፊት በሆነ ምክንያት ካዘገየ ስለመሆኑ ተመልክቷል። ሰራተኛው ስለጠየቀው ክፍያ አለመግባባት የተፈጠረ እንደሆነ አሰሪው በአንቀፅ 36 በተሰጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ለሰራተኛው ያመነውን ያህል ሉከፍል እንደሚገባ ደግሞ የአዋጁ አንቀፅ 37 ደንግጓል። እነዚህን ድንጋጌዎችን ያላገናዘበ የክፍያ ማዘግየት ውጤቱ በአንቀፅ 38 ስር የተመለከተው የሰራተኛውን እስከ ሶስት ወር ሉደርስ የሚችል ደመወዝ መክፈል ነው። ከእነዚህ ድንጋጌዎች መረዲት የሚቻለው ሰራተኛው ለአሰሪው ማስረከብ ያለበት ንብረትና ማወራረድ ያለበት ማናቸውም ሂሳብ አለመግባባት የላለበት መሆን እንዲለበት እና አለመግባባት ካለ ግን ሰራተኛው ክፍያውን ከአሰሪው ለመጠየቅ ክስ ከማቅረብ ሙለ በሙለ ሉከለከል የማይችል መሆኑን ነው። ሰራተኛው ጉድለት ስለአለበት ሂሳቡን ሳያወራርድ ተገቢ ክፍያዎችን ሉጠይቅ አይችልም ከተባለ በሕጉ የጊዜ ገደብ መብቶችን የማስከበር መብቱንም ዋጋ የሚያሳጣ እንደሚሆን ይታመናል። በመሆኑም አንድ ሰራተኛ የማያምንበት ጉድለት ካለ አሰሪው በተገቢው መንገድ ክስ መስርቶ መብቱን ከሚያስከብርና ምናልባት በራሱ ክስ ረቺ የሚሆን ከሆነ በአፈፃጸም ጊዜ ስርአቱን ጠብቆ የዕዲ ይቻቻልልኝ ጥያቄ ከሚያቀርብ በስተቀር ለሰራተኛው መክፈል ያለበትን ክፍያ ከመጠየቅ ክስ ላቀርብ አይገባም ወይም ውድቅ ላሆን ይገባል በማለት ሲከራከር ተቀባይነት ያገኛል ማለት አለመሆኑን ከአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 36 እስከ 38 ድረስ ከተመለከቱት ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ የምንገነዘበው ጉዲይ ነው። ስለሆነም አመልካች በበታች ፍርድ ቤቶች ያቀረበው ክርክር ውድቅ መደረጉ ከላይ ከተጠቀሱት ድንጋጌዎች መንፈስ እና ባሁኑ ጊዜ አመልካችና ተጠሪ በንብረት ጉድለቱ ላይ በፍትሐብሕር ጉዲይ ክርክር ላይ ያለ ከመሆኑ አንፃር ሲታይ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት አለበት ለማለት አልተቻለም። በዚህም ምክንያት ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ ታህሳስ 27 ቀን 2001 ዓ.ም ተሰጥቶ በፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ጥር 28 ቀን 2001 ዓ.ም በትዕዛዝ የፀናው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሰረት ፀንቷል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሳራ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
No topics extracted.