No summary available.
መ/ ሚያዝያ 6 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ሐጎስ ወልደ ሂሩት መለሰ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- ጉደር አግሮ ኢንደስትሪ ኃ/የተ/የግ/ማህበር - ነ/ፈጅ አየለ ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ በለጠ ጫላ - ቀረቡ
በዚህ መዝገብ የቀረበው ጉዲይ የስራ ክርክርን የሚመለከት ነው። ተጠሪ በፋ/መ/ደረጃ ፍ/ቤት ባቀረቡት ክስ ከአቅም በላይ በሆነ ሁኔታ በተፈጠረ የመኪና ግጭት አደጋ አደጋው ከደረሰ ከ4 ወራት በኋላ መጋቢት 4 ቀን 2000 ዓ.ም ያለአግባብ የስራ ውላቸው ስለተቋረጠ ወደስራቸው እንዱመለሱ ወይም የተለያዩ ክፍያዎች እንዱከፈላቸው ጠይቀዋል። አመልካችም በመልሱ መኪናውን በቸልተኛነት አጋጭተዋል፣ የትራፉክ ፕሉስ ስለአደጋው ውጤቱን የገለፀው የካቲት 26 ቀን 2000 ዓ.ም በመሆኑ እርምጃው በይርጋ አይታገድም፣ በመሆኑም ስንብቱ ህጋዊ ነው በማለት ተከራክሯል። ፍ/ቤቱም የቀረበው የትራፉክ ሪፕርት ተጠሪ ጥፊተኛ መሆናቸውን ስለማይናገር አደጋው በተጠሪ ጥፊት ነው ማለት ስለማይቻልና አደጋው በተጠሪ ቸልተኛነት የደረሰ መሆኑን አመልካች ማስረዲት ስላልቻለ ስንብቱ ህገ-ወጥ ነው በማለት የተለያዩ ክፍያዎች ተከፍሎቸው እንዱሰናበቱ ወስኗል። በዚህ ውሳኔ ላይ አመልካች ለፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ አቅርበው ፍ/ቤቱ ይግባኙን በመሰረዝ መዝገቡን ዘግቷል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሳኔ ላይ ነው። አመልካች በቅሬታው ተበላሽቶ መንገድ ዲር የቆመ ከባድ መኪና ለማመልከት ተደርድረው የነበሩትን ድንጋዮችና ላልች ምልክቶች ደርምሰው በማለፍ አደጋው መድረሱን የትራፉክ ፕሉስ ሪፕርት ስላረጋገጠ ስንብቱ በአ/ቁ 377/96 አንቀፅ 27(1/ሸ) መሰረት ህጋዊ ነው፣ የተረከቡትን የድርጅቱን ንብረትና ገንዘብ ያስረከቡና ያወራረደ ለመሆኑ ክሉራንስ ባለማቅረባቸው በገዛ ጥፊታቸው የዘገየ በመሆኑ ልንቀጣ አይገባም ብሎል። ችልቱም ስንብቱ ህገ-ወጥ ነው የመባለን አግባብነት ለመመርመር አቤቱታው ለሰበር ችልት ያስቀርባል በማለቱ ተጠሪ ክርክራቸው በፁሁፍ አቅርበዋል። ችልቱም መዝገቡን መርምሯል።
ተጠሪ ስንብቱ ህገ-ወጥ ነው የሚለት አንደኛው ለስንብቱ ምክንያት የሆነው መኪና ላይ የደረሰው የግጭት አደጋ ከአቅም በላይ በሆነ ሁኔታ በመከሰቱ ሲሆን ሁለተኛው ምክንያት አደጋው ከደረሰ ከአራት ወራት በኋላ የተወሰደ እርምጃ በመሆኑ ነው። ችልቱም አንደኛውን ምክንያት ከማየቱ በፉት በቅድሚያ ስንብቱ በሁለተኛው ምክንያት ህገ-ወጥ ልባል የሚችል ስለመሆኑ ተመልክቷል። ከክርክሩ ሂደት አደጋው ጥቅምት 23 ቀን 2000 ዓ.ም ከደረሰ በኋላ የተጠሪ የስራ ውል የተቋረጠው መጋቢት 4 ቀን 2000 ዓ.ም ስለመሆኑ ተረድተናል። ይህም ተጠሪ የስንብቱ ምክንያት የሆነውን ድርጊት ከፈፀሙ ከ4 ወራት በኋላ ከስራ የተሰናበቱ መሆኑን ያሳያል። በአ/ቁ 377/96 አንቀፅ 27(3) መሰረት አሰሪው የስራ ውለን ለማቋረጥ ያለው መብት ውለ የሚቋረጥበት ምክንያት መከሰቱን ካወቀ ከሰላሳ ቀናት በኋላ በይርጋ ይታገዲል። አመልካች በበኩለ የስራ ውለን ለማቋረጥ ያለው መብት በይርጋ አለመታገደን ተከራክሯል። በክርክሩም የትራፉክ ሪፕርቱ የደረሰው የካቲት 26 ቀን 2000 ዓ.ም በመሆኑ የይርጋው ጊዜ ሉቆጥር የሚገባው ከዚሁ ቀን ጀምሮ ነው ብሎል። አመልካች ተጠሪ መኪናውን ያጋጩ ስለመሆኑ ያወቀው የትራፉክ ሪፕርት ሲቀርብለት ሳይሆን ወዱያው አደጋው እንደደረሰ ስለመሆኑ ከክርክሩ ተገንዝበናል። ስለሆነም እርምጃውን ለመውሰድ የትራፉክ ፕሉስ ሪፕርቱን የሚጠብቅበት ምክንያት አይኖርም። ምናልባት የተጠሪን ጥፊተኛነት ለማረጋገጥ ሪፕርቱ ያስፈልግ ነበር የሚባል ቢሆን እንኳን ሪፕርቱ በወቅቱ እንዱቀርብለት መጠየቅ ይገባው ነበር። በመሆኑም ተጠሪ የፈፀሙት ድርጊት አመልካች ባወቀ በአንድ ወር ውስጥ የስራ ውለን ያላቋረጠ በመሆኑ መብቱ በይርጋ ቀሪ ይሆናል። በልላ በኩል አመልካች የስር ፍ/ቤት የይርጋውን መቃወሚያ በዝምታ በማለፈ ተጠሪ ይግባኝ ወይም መስቀለኛ ይግባኝ ባለማቅረባቸው በሰበር ደረጃ ሉከራከሩበት እንደማይችለ ተከራክሯል። ነገር ግን የፋ/መ/ደረጃ ፍ/ቤት በልላ ምክንያት ቢሆንም ስንብቱ ህገ-ወጥ ነው ብል መወሰኑ፤ ተጠሪ ይግባኝ የሚያቀርብበት ምክንያት አይኖርም። አመልካች ያቀረበውም የይግባኝ ቅሬታ ተጠሪን መጥራት ሳያስፈልግ መዝገቡ የተዘጋ በመሆኑ ተጠሪ መስቀለኛ ይግባኝ የሚያቀርቡበት ስርዓት ስለላለ በዚህ በኩል አመልካች ያቀረበው ክርክር ተቀባይነት የለውም። በአጠቃላይ አመልካች መብቱ በይርጋ ቀሪ ከሆነ በኋላ የስራ ውለን ማቋረጡ ህጋዊ ስላልሆነ የስር ፍ/ቤቶች በሰጡት ውሳኔ ላይ መሰረታዊ የህግ ስህተት ተፈፅሟል ለማለት አልተቻለም።
የፋ/መ/ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ የካቲት 16 ቀን 2001 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ እና የፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ ግንቦት 4 ቀን 2001 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ ፀንቷል።
ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።
ይህ ችልት ሰኔ 1 ቀን 2001 ዓ.ም የሰጠው የእግድ ትዕዛዝ ተነስቷል። ለሚመለከተው ክፍል ይተላለፍ።
No topics extracted.