No summary available.
መ/ ሚያዝያ 12 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ሐጎስ ወልደ ሂሩት መለሰ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- ተንዲሆ ስኳር ፊብሪካ ፔሮጀክት - ነገረ ፈጅ አንድአርጋቸው በየነ - ቀረበ ተጠሪ፡-
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የአሰሪና ሰራተኛ ወሳኝ ቦርድ እና የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት ታህሳስ 1 ቀን 2002 ዓ.ም ስላመለከተ ነው።
ክርክሩ በመጀመሪያ የታየው በአሰሪና ሰራተኛ ወሳኝ ቦርድ ነው። በአሰሪና ሰራተኛ ወሳኝ ቦርድ ተጠሪዎች በከሳሽነት በመቅረብ ተንዲሆ እርሻ ልማት አክሲዮን ማህበር በነበረበት ወቅት ለሀያሁለት ዓመት በፍርማንነት የሥራ መደብ አገልግለናል። የተንዲሆ እርሻ ልማት ፈርሶ ወደ ተንዲሆ ስኳር ፊብሪካ ፔሮጀክት በመንግስት ውሣኔ ሲዛወር የሰራተኞች መብት ጥቅም መጠበቅ እንዲለበት በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 131/99 ተደንግጓል። ከሳሽ (አመልካች) መዋቅር ሲያፀድቅ የእኛን የሥራ መደብ መያዝና ማፅደቅ ሲገባው አፍርሶታል። ስለዚህ ከሙያችንና ከልምዲችን ውጭ በሆነ ሁኔታ ደረጃችንን ዝቅ አድርጎ የመደበን በመሆኑ ተንዲሆ እርሻ ልማት ስንሰራ በነበርንበት የፍርማንነት የሥራ መደብ ይመድበን በማለት አመልክተዋል። አመልካች በተከሳሽነት ቀርቦ እየተደራጀ ያለው ከተንዲሆ እርሻ ልማት የተለየ አዱስ ድርጅት ነው። ስለዚህ ሥራውን ለመሥራት የሚያስችለው አዱስ መዋቅር ዘርግቷል።
ጥቅማቸውን በማይቀንስ ሁኔታ ባለው መዋቅር መድበናቸዋል። ድርጅቱ በላለው የፍርማንነት የሥራ መደብ ለመመደብ ያቀረቡትን ጥያቄ የህግ መሰረት የለውም በማለት ተከራክሯል። የአሰሪና ሰራተኛ ወሳኝ ቦርድ አመልካች ተጠሪዎችን በፍርማንነት የሥራ መደብ ይመድባቸው በማለት ወስኗል። አመልካች በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ አቅርቦ የከፍተኛ ፍርድ ቤት የቦርደን ውሣኔ አፅንቶታል።
አመልካች ክርክሩ ግላዊ ባህሪ ያለው ነው። ከድርጅቱ የሥራ ባህሪ በመነሳት አደረጃጀቱና መዋቅሩ ተቀይሯል።
ስለዚህ በላለ የሥራ መደብ ተጠሪዎችን እንድንመደብ የሰጠው ውሣኔ ከአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀፅ 28 ድንጋጌ የሚቃረን በመሆኑ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት አመልክቷል። ተጠሪ በበኩለ መሰረታዊ ቅሬታችን የሀያ ሁለት ዓመት አገልግልታችንን ወደ ጎን በመተው የሰራተኛ ማህበር ተወካይ ባልተገኘበት በአዱስ የሥራ መደብ ላይ በመመደባቸው ነው። ሥለዚህ ቦርደና ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የለበትም በማለት መልስ ሰጥተዋል። አመልካች የመልስ መልስ ሰጥቷል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በስር የቀረበው ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም ጉዲዩን መርምረናል። ጉዲዩን እንደመረመርነው ተጠሪዎች ያቀረቡት ጥያቄ አመልካች አዱስ በዘረጋው መዋቅር የሥራ መደባችን ፈርሷል። ስለዚህ በፉት የነበረንን የሥራ መደብ በአዱሱ መዋቅር በማካተት በፉት በሰራንበት የሥራ መደብ በፍርማንነት ይመድበን በማለት ነው። የተጠሪዎች ጥያቄና የሚሰጠው ውሳኔ በእነርሱ ብቻ የሚወሰን ውጤት ያለው ሣይሆን የላልችንም ሰራተኞች ለተመሣሣይ ጥያቄ የሚጋብዝ የወል የሥራ ክርክር ባህሪ ያለው ነው። ጉዲዩ የወል የሥራ ክርክር ባህሪ ያለው በመሆኑ የአሰሪና ሰራተኛ ወሳኝ ቦርድ የአመልካችንና የተጠሪዎችን ክርክር ሰምቶ የመወሰን ሥልጣን በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀፅ 147 መሰረት አለው። ስለዚህ አመልካች ቦርደ ጉዲዩን መርምሮ የመወሰን የሥረ-ነገር ሥልጣን የለውም በማለት ያቀረበውን አቤቱታ አልተቀበልነውም።
ቦርደ ጉዲዩን የማየትና የመወሰን ሥልጣን አለው ከሚል መደምደሚያ ላይ ከደረስን በኋላ የቦርደ ውሣኔ ህጋዊ መሰረት ያለው ነው ወይስ አይደለም? ሚለውን ጭብጥ በመያዝ መርምረናል።
ጉዲዩን እንደመረመርነው የተንዲሆ ስኳር ፊብሪካ ፔሮጀክት በፉት ከነበረው የተንዲሆ እርሻ ልማት አክሲዮን ማህበር የተለየ የሥራ ባህሪ ያለው ድርጅት ነው። አመልካች ለሥራ ባህሪው የሚስማማ የሥራ መዋቅርና የሥራ መደብ በጥናት ላይ በመመርኮዝ እንዱፀድቅ በማድረግ የሰራተኛ ምደባ አከናውኗል። ተጠሪዎች በፉት ያላቸው የሥራ ልምድና የትምህርት ዝግጅት አዱስ ለፀደቀው የሥራ መዋቅር የትኛው ቦታ ላይ ሉያስመድባቸው እንደሚችል በኮሚቴ ተጠንቶና ታይቶ በፉት ያገኙት የነበረው ደመወዝ ሣይቀነስ በአዱሱ የሥራ መዋቅር አዱስ ሥራ መደብ ላይ ተመድበዋል። ድርጅቱ ቀልጣፊና ውጤታማ በሆነ መንገድ ሥራውን ለማከናወንና አትራፉና ተወዲዲሪ ለመሆን በሚያስችለው አደረጃጀትና የመደራጀትና የሥራ መደብ የማዋቅር ሥልጣን እንዲለው ከአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀፅ 28 ድንጋጌ ለመረዲት ይቻላል። ስለሆነም አመልካች የተጠሪዎችን ደመወዝ ሣይቀንስ በአዱሱ መዋቅር ሉመጥናቸው በሚችለው የሥራ መደብ መድቦ የማሰራት ሙለ ኃላፉነት ያለው ሲሆን የአሰሪና ሰራተኛ ወሳኝ ቦርድ በአዱሱ መዋቅር ባልተካተተና በልላ የሥራ መደብ አመልካች ተጠሪዎችን መድቦ እንዱያሰራ የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል። የከፍተኛ ፍርድ ቤት የአመልካችን ሰራተኞችን ባለው መዋቅርና አደረጃጀት መድቦ የማሰራት መብት የሚጋፊውን የቦርደን ውሣኔ በይግባኝ ሣያርም ማፅናቱ መሰረታዊ የህግ ስህተት አለበት በማለት ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የአሰሪና ሰራተኛ ወሳኝ ቦርድና የከፍተኛው ፍርድ ቤት የሰጠው ውሣኔ ሙለ በሙለ ተሽሯል።
በዚህ ፍርድ ቤት ያወጡትን ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ ለየራሳቸው ይቻለ።
ይህ ፍርድ በፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት በሙለ ድምፅ ተሰጠ።
No topics extracted.