No summary available.
መ/ ሚያዝያ 21 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ሂሩት መለሰ ተሻገር ገ/ሥላሴ ታፈሰ ይርጋ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- የጎሽና እርግብ መለስተኛና አነስተኛ የሕዝብ ማመላለሻ ባለንብረቶች ማህበር - ጠበቃ ምክሩ ወልደአረጋይ ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ተሰማ ኃይለ - ቀረቡ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ የአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ ቁጥር 377/96“ን” መሰረት ያደረገ ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው ያሁኑ ተጠሪ ባሁኑ አመልካች ላይ በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመሰረቱት ክስ መነሻ ነው። የተጠሪ የክስ ይዘት ባጭሩ ከአመልካች ጋር ሕዲር 12 ቀን 2002 ዓ.ም በመሰረቱት የስራ ውል በድርጅቱ የፊይናንስ አገልግልት ኃላፉ ሆነው ሲሰሩ መቆየታቸውን ገልፀው የስራ ውለ ጥቅምት 19 ቀን 2001 ዓ.ም ከሕግ ውጪ መቋረጡን ጠቅሰው ውዝፍ ደመወዝ ተከፍሎቸው ወደ ስራ እንዱመለሱ፣ የሞባይል ስልክ አበል ከተቋረጠበት ጊዜ ጀምሮ እንዱከፈል ይወሰንላቸው ዘንድ ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው። ያሁኑ አመልካች ለክሱ በሰጠው መልስም የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ እና የፍሬ ነገር ክርክር አቅርቧል። አመልካች በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያነት ያነሳው ክርክር ተጠሪ የስራ መሪ ስለሆነ የስራ ክርክር ችልት ጉዲዩን ለማየት ስልጣን የለውም የሚል ሲሆን በፍሬ ነገር ረገድ ደግሞ በስራ አፈፃፀም ላይ ባሳዩት ጥፊትና የብቃት ማነስ ችግር የተሰናበቱ በመሆኑ እርምጃው ሕጋዊ ነው ሲል ተከራክሯል። ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ክርክር ለማየት ስልጣን እንዲለው በመግለፅ ዋናውን ክርክርም ተመልክቶ የስራ ውለ የተቋረጠው ከሕግ ውጪ ነው ወደሚለው ድምዲሜ በመድረስ አመልካች የስድስት ወራት ውዝፍ ደመወዝ ተከፍሎቸው ወደ ስራ እንዱመለሱ ሲል ወስኗል። በዚህ ውሳኔ አመልካች ባለመስማማት ይግባኙን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርቦ ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በኋላ የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ ሙለ በሙለ ፀንቷል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስቀየር ነው።
የአመልካች ጠበቃ ጥቅምት 17 ቀን 2002 ዓ.ም በፃፈት ሶስት ገፅ የሰበር አቤቱታ በበታች ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ላይ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈፅሟል የሚለበትን ምክንያት ዘርዝረው አቅርበዋል። ይዘቱም ባጭሩ ተጠሪ በስራቸው ላይ የብቃት ማነስ ያሳዩ መሆኑ ተረጋግጦ እያለ ስንብቱ ከሕግ ውጪ ነው ተብል መወሰኑ ያላግባብ ስለሆነ ሉታረም ይገባል በማለት መከራከራቸውን የሚያሳይ ነው። አቤቱታቸው ተመርምሮም ተጠሪ በብቃት ማነስ ምክንያት ለስራው ብቁ አይደለም በማለት አመልካች ያቀረበው ክርክር መታለፈ ባግባቡ መሆን ያለመሆኑን ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ ለሰበር ችልቱ እንዱቀርብ ተደርጎአል። ተጠሪም በተደረገላቸው ጥሪ መሰረት ቀርበው የካቲት 30 ቀን 2002 ዓ.ም በተፃፈ ሦስት ገፅ መልሳቸውን ሰጥተዋል። የአመልካች ጠበቃ በበኩላቸው መጋቢት 16 ቀን 2002 ዓ.ም በተፃፈ ሁለት ገጽ ማመልከቻ የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር የመልስ መልሳቸውን ሰጥተዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩ ለሰበር ችልቱ ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ አንፃር በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው አመልካች የሰራ ስንብቱን እርምጃ ሕጋዊ ነው የሚልባቸውን ምክንያቶች ገልፆ ማስረጃ ጠቅሶ የተከራከረ መሆኑና የበታች ፍርድ ቤቶች የቀረቡት ማስረጃዎች የአመልካች ምክንያት በአሳማኝ ማስረጃ ያልተደገፈ መሆኑን በመግለፅ ውሳኔ የሰጡ መሆኑን ነው። ከዚህ ሁለ መገንዘብ የተቻለው የበታች ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ማስረጃ ምዘናን መሰረት ያደረገ መሆኑን ነው። እንደሚታወቀው ይሕ ሰበር ችልት ስልጣኑ ፍሬ ነገርን የማጣራት ስልጣን ያላቸው ፍርድ ቤቶች በሕግ አተረጓጎም ረገድ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ሲፈፅሙ ማቃናት ነው። ይህም በሕገ-መንግስቱ አንቀጽ 80(3/ሀ) እና በአዋጅ ቁጥር 25/88 አንቀጽ 10 ድንጋጌዎች ስር የተመለከተ ጉዲይ ነው።
በተያዘው ጉዲይም የበታች ፍርድ ቤቶች አመልካች ለተጠሪ ተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ ሲሰጥ ነበር የተባለው የስራውን አሰራር የሚገልፅ ነው በሚል ምክንያት ተቀባይነት የላለው ነው በማለት የደመደሙት ሲሆን የሂሳብ ሪፕርቱም አመልካች የተሳሳተ ነው ብል ቢከራከርም ተጠሪ ሪፕርቱ በሰነድ ችግር ያልተሟላ ስለመሆኑ በመግለፅ ለአመልካች የገለጸ መሆኑን አረጋግጠው ሂሳቡ የተሳሳተ ነበር ለማለት ያልቻለ መሆኑን ያመኑበት ጉዲይ ነው። ይህ የበታች ፍርድ ቤቶች ድምዲሜ የማስረጃ ምዘናን መሰረት ያደረገ በመሆኑ በዚህ ችልት ሉታረም የሚችልበት የህግ አግባብ የለም። በመሆኑም አመልካች በዚህ ረገድ ያቀረበው ክርክር የመሰረታዊ ሕግ ስህተት መመዘኛን የሚያሟላ ባለመሆኑ ተቀባይነት የላለው ሆኖ ተገኝቷል። በልላ በኩል ጉዲዩ በሰበር ችልቱ እንዱታይ ሲደረግ በጭብጥነት ያልተያዘውን ተጠሪ በስራ ግንኙነቱ ከፍተኛ ችግር ሉፈጥሩ ስለሚችለ ካሳ ተከፍሎቸው እንዱሰናበቱ ይወሰን ዘንድ ዲኝነት በአማራጭ አመልካች በመልስ መልሱ ላይ ጠይቋል። ይሁን እንጂ አመልካች ተጠሪ ካሳ ተከፍሎቸው እንዱሰናበቱ ይወሰን ዘንድ ምክንያት ይሆናል ያለው ነጥብ ተጠሪ ለአለቃ የማይታዘዙ ናቸው የሚለው ሆኖ በስር ፍርድ ቤቶች የክርክር ነጥብ ያልሆነ እና በተገቢው ማስረጃም ያልተረጋገጠ ነው። አንድ ሰራተኛ ወደ ስራ ከሚመለስ በአማራጭ ካሳ ተከፍልት እንዱሰናበት የሚደረገው በስራ ግንኙነቱ ከፍተኛ ችግር የሚከሰት መሆኑን ፍርድ ቤቱ ሲያምን ስለመሆኑ አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀፅ 43(3) ድንጋጌ ያሳያል። ከድንጋጌው ይዘት በግልፅ መረዲት እንደሚቻለው ፍርድ ቤቱ የስራ ግንኙነቱ ከፍተኛ ችግር ውስጥ ይገባል ብል ለማመን የሚያስችል በቂ ምክንያት ሉኖር ይገባል። ያለበቂ ማስረጃና ምክንያት አሰሪ የስራ ግንኙነቱ ችግር ውስጥ ሉወድቅ ይችላል ብል ስለተከራከረ ብቻ ድንጋጌውን ተግባራዊ ማድረግ የስራ ዋስትናን ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ ይሆናል። በመሆኑም አመልካች በዚህ ረገድ ያቀረበው የዲኝነት ጥያቄ ተቀባይነት የላለው በመሆኑ አልፈነዋል።
በአጠቃላይ በበታች ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ላይ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈፅሟል ለማለት ስላልተቻለ ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ ግንቦት 14 ቀን 2001 ዓ.ም ተሰጥቶ በፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ጥቅምት 10 ቀን 2001 ዓ.ም የፀናው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሰረት ፀንቷል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሳራ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
ት እ ዛ ዝ በዚህ ችልት ሕዲር 30 ቀን 2002 ዓ.ም ተሰጥቶ የነበረው እግድ ተነስቷል። ይጻፍ።
No topics extracted.