No summary available.
መ/ ሚያዝያ 04 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ሐጎስ ወልደ ሂሩት መለሰ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡-
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ ፍርድ እና አፈፃፀሙን የሚመለከት ነው። ክርክሩ የተጀመረው በአፊር ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት በአውሲረሱ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲሆን ለአፈፃፀሙ መሰረት የሆነው ውሳኔ የተሰጠውም በዚሁ ፍርድ ቤት በመ/ቁጥር 1481 ሰኔ 30 ቀን 2001 ዓ.ም ነው። በዚሁ በመ/ቁጥር 1481 ሰኔ 30 ቀን 2001 ዓ.ም የተሰጠው ውሳኔ የአሁኑ ተጠሪ ባሁኑ አመልካቾች ላይ የካቲት 11 ቀን 2001 ዓ.ም በመሰረቱት ክስ መነሻ ሲሆን የክሱ ይዘትም ባጭሩ፤ ተከሳሾች በውላቸው መሰረት ስራውን እራሳቸው ወይም በሚወክለት ሰው ማሰራት ሲገባቸው ከ1999 ዓ.ም ጀምሮ እስካሁን ድረስ ውል ሰጪው እራሱ የጨው ምርቱን እያመረቱ ከጨው ማህበር ድርሻቸውን እየወሰደ መሆናቸውን፣ የጨው ማምረቱን ስራ እራሳቸው ወይም የሚወክለት ሰው እንዱጀምር በተደጋጋሚ ቢነገራቸውም ተከሳሾች ፍቃደኛ አለመሆናቸውን በመግለፅ የጠየቁት ዲኝነት ውለ እንዱፈርስ እንዱወሰንላቸው መሆኑን የሚያሳይ ነው። ጉዲዩን የተመለከተው ፍርድ ቤትም ግራ ቀኙን ካከራከረ በኋላ ውለ እንዱፈርስ ሲል በግልፅ ወስኗል። ለአፈፃፀም የቀረበው ውሳኔም ይህ ሲሆን የአሁኑ ተጠሪ የአፈፃፀም ማመልከቻቸው ላይ ውለ በፍርድ ቤት ውሳኔ እንዱፈርስ መወሰኑን ገልፀው በውለ መፍረስ ምክንያት የደረሰባቸውን ጉዲት አይነት እና መጠን ዘርዝረው ፍርድ ቤቱ አመልካቾች እንዱከፍሎቸው የአፈፃፀም ትዕዛዝ እንዱሰጥ ሐምል 06 ቀን 2001 ዓ.ም በተፃፈ ማመልከቻ ዲኝነት ጠይቀዋል። የአሁኑ አመልካቾችም ለአፈፃፀሙ ክስ በሰጡት መልስ በሕጉ አግባብ የተሰጠና ሉፈፀም የሚችል ውሳኔ ስለላለ ልንገደድ አይገባም በማለት ተከራክረዋል።
አፈፃፀሙን የያዘው ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን የአፈፃፀም ክርክር በመመርመር አመልካቾች ለተጠሪ ብር 71,000.00፣ 5789 ኩንታል ጨው እንዱሁም የ20343 ኩንታል ጨው 30% እንዱከፍለ እና እንዱሰጡ በማለት ወስኗል። በዚህ ውሳኔ አመልካቾች ቅር በመሰኘት ይግባኛቸውን ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቢያቀርቡም ተቀባይነት አላገኙም። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስቀየር ነው።
የአመልካቾች ጠበቃ ጥቅምት 30 ቀን 2002 ዓ.ም በፃፈት ሁለት ገፅ የሰበር አቤቱታ በበታች ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ላይ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት አለበት የሚለበትን ምክንያት ዘርዝረው አቅርበዋል። ይዘቱም ባጭሩ በሕጉ አግባብ የተፈረደ ውሳኔ ሳይኖር አመልካቾች ለተጠሪ ገንዘብ እንዱከፍለ፣ ጨው በኩንታል እንዱሰጡ መወሰኑ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 378 ተከታዮቹ ድንጋጌዎች ስር የተመለከተውን የፍርድ አፈፃፀም ስርዓት ያላገናዘበ ስለሆነ ሉታረም ይገባዋል በማለት መከራከራቸውን የሚያሳይ ነው። አቤቱታው ተመርምሮም በሰበር ችልቱ ላታይ ይገባዋል ተብል ተጠሪ ቀርበው በፅሐፍ መልሳቸውን ሰጥተዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
ጠበቃ መንበረስላሴ በዛብህ - ቀረቡ እንደመረመረውም የአሁኑ አመልካቾች ለተጠሪ ገንዘብ እንዱከፍለ እና ጨው በኩንታል እንዱሰጡ በአፈፃፀም መዝገብ የተወሰነው ባለእዲ በሚያደርግ ፍርድ መሰረት ነው? አይደለም? የሚለው ነጥብ በጭብጥነት ላታይ የሚገባው ሆኖ አግኝቶታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው የአሁኑ ተጠሪ በዋናው ጉዲይ ክስ ሲመሰርቱ ለውለ መፍረስ ምክንያቶች ናቸው ያሎቸውን ነጥቦች ዘርዝረው ውለ እንዱፈርስ በጠየቁት ዲኝነት መሰረት ውለ እንዱፈርስ የሚገልፅ ውሳኔ መሰጠቱን፣ ለአፈፃፀሙም መሰረት የሆነው ውሳኔ ይሕ ሲሆን የአፈፃፀም ማመልከቻ ሲያቀርቡ ግን በውለ መፍረስ ምክንያት የደረሰባቸውን ጉዲት ዘርዝረው ጉዲቱን አመልካቾች እንዱተኩ እንዱወሰንላቸው መሆኑን ነው።
በመሰረቱ አንድ ሰው በአፈፃፀም ሉገደድ የሚችለው በሕጉ አግባብ የተፈረደ ፍርድ ሲኖር ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 378 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ ያስገነዝባል። በልላ አገላለፅ አንድ ሰው የፍርድ ባለእዲ ስለመሆኑ የሚያረጋግጥ ፍርድ ሳይኖር በአፈፃፀም ሉገደድ አይገባም።
ወደተያዘው ጉዲይ ስንመለስም ለአፈፃፀሙ መሰረት የሆነው ውሳኔ በመ/ቁጥር 1481 ሰኔ 30 ቀን 2001 ዓ.ም የተሰጠው ሲሆን ይህ ውሳኔ በአመልካቾች እና በተጠሪ መካከል የነበረውን የጨው መሬት ኪራይ ውል እንዱፈርስ በማለት ከመግለፁ ውጪ አመልካቾች ለተጠሪ በዓይነትም ሆነ በመጠን እንዱከፍለ የተወሰነ የጉዲት መጠን ሁኔታ የለም። ተጠሪ በውለ መፍረስ ምክንያት የደረሰባቸው ጉዲት እንዱከፈላቸው የጠየቁት ዲኝነት በዝምታ ታልፎል በማለት በበላይ ፍርድ ቤት ያሳረሙት ሁኔታ የለም። በእርግጥ ውለ እንዱፈርስ ሲደረግ ሕጉ ያስቀመጠው አንደ መፍትሓ የጉዲት ኪሳራ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1771(2) ድንጋጌ ያሳያል። በዚህ ረገድ ዲኝነት ተጠይቆ በግልፅ የተሰጠ ፍርድ ሲኖር በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 378 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች መሰረት የሚፈፀም ይሆናል። ከዚህ ውጪ በግልጽ ፍርድ ያላረፈበት ፍርድ የሚፈፅምበት የሕግ አግባብ የለም። በመሆኑም የበታች ፍርድ ቤቶች አመልካቾች ለተጠሪ ብር 71,000.00፣ 5789 ኩንታል ጨው እንዱሁም የ20343 ኩንታል ጨው 30% እንዱከፍለ እና እንዱሰጡ በማለት የሰጡት ውሳኔ ያልተፈረደ ፍርድን ማስፈፀም ከመሆኑም በላይ የአመልካቾችን የመዲኘት ሕገ-መንግስታዊ መብት ያላገናዘበ በመሆኑ ውሳኔው መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ አግኝተናል። በዚህም ምክንያት ተከታዩን ወስነናል።
No topics extracted.
ው ሣ ኔ
በአውሲረሱ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁጥር 1631 ሐምል 07 ቀን 2001 ዓ.ም ተሰጥቶ በአፊር ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመ/ቁጥር 2067 ጥቅምት 25 ቀን 2002 ዓ.ም በትዕዛዝ የፀናው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሰረት ተሽሯል።
የአመልካቾችን ባለዕዲነት፣ የተጠሪን ባለገንዘብነት የሚያረጋግጥ ፍርድ ሳይኖር አመልካቾች በፍርድ አፈፃፀም የሚገደደበት አግባብ የለም ብለናል።
ለክርክሩ የወጣውን ወጪና ኪሣራ የየራሳቸውን ይቻለ በለናል።