No summary available.
መ/ ሚያዝያ 27 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ሂሩት መለሰ ተሻገር ገ/ስላሴ ታፈሰ ይርጋ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- አቶ ደረጀ ውለታው - ቀረቡ ተጠሪ፡- ዋሉያ ላዘርና ላዘር ፔሮዲክትስ ኃ/የተ/የግ/ማ
አመልካች በስራ ላይ በደረሰባቸው አደጋ በሁለቱም እጆቻቸው ላይ ከፍተኛ ጉዲት ስለደረሰባቸው የጉዲት ካሳ እንዱከፈላቸው ክስ መስርተው የስር ፍ/ቤት ጉዲቱ ዘላቂ ሙለ የአካል ጉዲት ነው በማለት ካሳው በዚህ መሰረት እንዱከፈል የስር ፍ/ቤትን ውሣኔ በማሻሻለ የቀረበ የሰበር አቤቱታ ነው።
ተጠሪ በፋ/መ/ደረጃ ፍ/ቤት ባቀረቡት ክስ በማሽን መጭመቂያ ስራ ተሰማርተው ሲሰሩ በስራ ላይ እያለ በግራና በቀኝ እጃቸው ላይ ዘላቂ የአካል ጉዲት ስለደረሰባቸው የጉዲት ካሳ፣ ክፍያ ለዘገየበት፣ የስንብት ክፍያና ለማስጠንቀቂያ ጊዜ ሉከፈል የሚገባው እንዱከፈላቸው ጠይቀዋል። ተጠሪም ጉዲቱ በስራ ላይ መድረሱን ሳይክድ የጉዲቱና የሚከፈለው የጉዲት ካሳ መጠን ላይ ክርክር አቅርቧል። ችልቱም ጉዲዩን መርምሮ አመልካች ላይ የደረሰው ዘላቂ ሙለ የአካል ጉዲት በመሆኑ ለአመልካች ብር 24,900 /ሃያ አራት ሺህ ዘጠኝ መቶ/ እና ክፍያ ለዘገየበትና የአገልግልት ካሳ እንዱከፈላቸው ወስኗል። ተጠሪ በዚህ ውሳኔ ላይ ለፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ አቅርቦ ፍ/ቤቱ አመልካች ላይ የደረሰው 65% የአካል ጉዲት ዘላቂ ከፉል የአካል ጉዲት ስለሆነ የጉዲቱ ካሳ ሉከፈል የሚገባው በአ/ቁ 377/96 አንቀፅ 109(3)(ለ) ነው በማለት የአመልካች የአምስት አመት ደሞዝ በ65% ተባዝቶ የሚመጣው ብር 16,185.00 /አስራ ስድስት ሺህ አንድ መቶ ሰማንያ አምስት/ እንዱከፈላቸውና ክፍያ ለዘገየበት ግን ሉከፈላቸው አይገባም በማለት የስር ፍ/ቤትን ውሳኔ በማሻሻል ወስኗል።
የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሳኔ ላይ ነው። አመልካች በቅሬታቸው የደረሰባቸው ዘላቂ ሙለ የአካል ጉዲት በመሆኑ የጉዲት ካሳው ሉከፈል የሚገባው በአ/ቁ. 377/96 109(3) (ሀ) መሰረት ነው የሚል ዝርዝር ክርክር አቅርበዋል። ይህ ችልትም አመልካች ላይ የደረሰው ጉዲት ዘላቂ ሙለ የአካል ጉዲት ነው ወይስ ዘላቂ ከፉል የአካል ጉዲት ነው የሚለውን ለመመርመር አቤቱታው ለሰበር ችልት እንዱቀርብ በማድረጉ ተጠሪ ቀርቦ ክርክሩን በፅሁፍ አቅርቧል። ችልቱም መዝገቡን ከተያዘው ጭብጥ አኳያ መርምሯል።
አመልካች በስራ ላይ ጉዲት የደረሰባቸው ስለመሆኑ በግራ ቀኙ አልተካደም። አከራካሪው የጉዲቱ መጠን ነው።
ከክርክሩ የአመልካች የቀኝ እጃቸው አራት ጣቶችና የግራ እጃቸው ሶስት ጣቶች መቆረጣቸውን ተገንዝበናል። የህክምና ቦርድም አመልካች ላይ 65% የአካል ጉዲት የደረሰባቸው መሆኑ አረጋግጧል። ዘላቂ ሙለ የአካል ጉዲት ማለት ጉዲት የደረሰበትን ሰራተኛ ማናቸውም ደሞዝ የሚያስገኝ ሥራ ለመሥራት የሚከለክለው የማይድን በሥራ ላይ የሚደርስ ጉዲት እንደሆነ አዋ/ቁ 377/96 አንቀፅ 101(2) ያመለክታል። ከፍ ሲል እንደተመለከትነው አመልካች የሁለት እጆቻቸውን አብዛኛዎቹን ጣቶች አጥተዋል። ከሞላ ጎደል ሁለን ስራ ለመስራት የእጆቻችን ጣቶች አስፈላጊዎች ናቸው። አመልካች የሁለቱንም እጆቻቸውን አብዛኞች ጣቶቻቸውን ማጣታቸው ደግሞ ማንኛውንም አይነት ደሞዝ የሚያስገኝ ስራ ለመስራት የሚከለክላቸውና የማይድን መሆኑን ተረድተናል። በእርግጥ የሃኪሞች ቦርድ ጉዲቱ 65% መሆኑን አረጋግጠዋል። ይህ ጉዲት የተለካው ግን ከአጠቃላይ የሰውነቱ ሁኔታ ጋር በማነፃፀር እንጂ የደረሰው ጉዲት ከመስራት ችልታ ጋር ተነፃፅሮ የቀረበ አይደለም። ከፍ ሲል በተገለፀው የህጉ ድንጋጌ ደግሞ የአካል ጉዲቱ ከፉልና ሙለ ተብል የሚከፈለው ከመስራት ችልታ ጋር በማነፃፀር እንጂ ከአጠቃላይ በሰውነት አካል ጉድለት ጋር ተነፃፅሮ አይደለም። ከዚህ አንፃር ሲታይ አመልካች የደረሰባቸው ጉዲት ዘላቂ ሙለ የአካል ጉዲት ነው። በሰራተኛው ላይ የደረሰው ዘላቂ ሙለ የአካል ጉዲት ከሆነ የሚከፈለው የጉዲት ካሳ መጠን የሰራተኛው የዓመት ደሞዝ በአምስት ተባዝቶ እንደሆነ አንቀፅ 109(3)(ሀ) ያመለክታል።
በመሆኑም ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት የአመልካች የጉዲት መጠን ዘላቂ ከፉል ጉዲት ነው በማለት ካሳው በአንቀፅ 109(3)(ለ) እንዱሰላ መወሰኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት ነው። በመሆኑም ተከታዩ ውሳኔ ፀንቷል።
የፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ ሰኔ 23 ቀን 2001 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ ተሻሽሎል።
አመልካች ብር 24,900 (ሃያ አራት ሺህ ዘጠኝ መቶ) ይከፈላቸው።
No topics extracted.
የፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት ክፍያ የዘገየበትን አስመልክቶ የተሰጠው ውሳኔ ፀንቷል።
ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻቻለ።