No summary available.
ሚያዝያ 12 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ሒጏስ ወልደ ኂሩት መለሰ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዲዮች ጽ/ቤት - ነ/ፈጅ በለጠ ቂጤሳ - ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ደረጃ መኮንን - የቀረበ የለም።
መዝገቡን መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ አዋጅ ቁጥር 515/1999 “ን” መሰረት ያደረገ የስራ መልቀቂያ ይሰጠኝ ጥያቄን የሚመለከት ሲሆን ጉዲዩን የተመለከተው የፋዳራል ሲቪል ሰርቪስ ኤጀንሲ አስተዲደር ፍርድ ቤት ነው፤በዚህ ፍርድ ቤት ያሁኑ ተጠሪ ያቀረቡት ይግባኝ ከስራ ከለቀቁ ከሁለት ወራት በላይ ቢሆናቸውም ለአመልካች መስሪያ ቤት የስራ መልቀቂያ ማስረጃ እንዱሰጣቸው ጥያቄ አቅርበው መስሪያ ቤቱ ፈቃደኛ አለመሆኑን፣ከመስሪያ ቤቱ ጋር በገቡት የትምህርት ስልጠና ውል መሰረት የሚጠበቅባቸውን አገልግልት የተወጡ ከመሆኑም በላይ ጉዲዩ ከስራ መልቀቂያ ጋር መያያዙ አግባብ አለመሆኑን በተመለተ ከሚመለከታቸው ከሰው ሐብት ስራ አመራር ክፍልች የተነጋገሩበት መሆኑን፣ይህንኑ መሰረት በማድረግ የፁሁፍ ማብራሪያ እንዱያቀርቡ ተስማምተው የፁሁፍ ማብራሪያ ማቅረባቸውን የገለፁ ቢሆንም አመልካች መስሪያ ቤት መልቀቂያውን ለመስጠት ፈቃደኛ አለመሆኑን በመጥቀስ አመልካች የስራ መልቀቂያ ማስረጃ እንዱሰጣቸው ይወሰንላቸው ዘንድ ዲኝት ጠይቀዋል። የአሁኑ አመልካች ለክሱ በሰጠው መልስም ተጠሪ የካቲት 29 ቀን 1996 ዓ.ም ከቀድሞው የኢትዮጵያ ዜና አገልግልት ድርጅት ካሁኑ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዲዮች ጽ/ቤት ጋር የስልጠናና የትምህርት ውል ገብተዋል፣በትምህርት ላይ የቆዩት ለሦስት አመታት ሲሆን ትምህርቱ ከተጠናቀቀ በኋላ ለስድስት አመት አገልግልት ለመስጠት ተስማምተዋል፣ትምህርታቸውን አጠናቅቀው በውለ መሰረት የሰጡት አገልግልት ሃያ ሁለት ወራት ከአስራ አምስት ቀናት ነው፣ተጠሪ በውለ መሰረት ግዳታቸውን ሳይወጡ የአገልግልት ምስክር ወረቀት የሚያገኝበት ምክንያት የለም በማለት ክሱ ውድቅ ላሆን ይገባል ሲል ተከራክሯል። ይግባኙ የቀረበለት የአስተዲደር ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ክርክር ከመረመረ በኋላ ተጠሪ በውለ የገቡትን ግዳታ ካልተወጡ አመልካች መስሪያ ቤት ስልጣን ላለው ፍርድ ቤት ክስ ከማቅረብ በስተቀር የስራ መልቀቂያ ማስረጃውን ለውለ መያዣ እንዱሆን ማድረግ አይችልም የሚል ምክንያት በመያዝ በአዋጅ ቁጥር 515/99 አንቀጽ 87 መሰረት የአገልግልት ምስክር ወረቀት እንዱሰጣቸው በማለት በአብላጫ ድምጽ ወስኗል። በዚህ ውሳኔ አመልካች መስሪያ ቤት ይግባኙን ለፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አቅርቦ ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በኋላ የአስተዲደር ፍርድ ቤቱ የሰጠው ውሳኔ በሙለ ፀንቷል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስቀየር ነው።
የአመልካች ነገረ ፈጅ ነሐሴ 21 ቀን 2001 ዓ.ም በፃፈት ሁለት ገጽ የሰበር ማመልከቻ በጉዲዩ ላይ በተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል የሚለበትን ምክንያት ዘርዝረው አቅርበዋል። አቤቱታው ተመርምሮም ተጠሪ ንብረት ሳያስረክብ ወይም የበኩለን ግዳታ ሳይወጣ የምስክር ወረቀት እንዱሰጠው መወሰኑ ባግባቡ መሆን ያለመሆኑን ለመመረመር ሲባል ጉዲዩ ለሰበር ችልት እንዱቀርብ ተደርጏ የግራ ቀኙ የቃል ክርክር ሕዲር 10 ቀን 2002 ዓ.ም በዋለው ችልት ተሰምቷል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩ ለሰበር ችልት ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ አንፃር በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው ተጠሪ በአዱስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ገብተው በአመልካች ወጪ ለሦስት አመታት የጋዜጠኝነት ትምሕርት የተከታተለ ሆኖ ከአመልካች ጋራ ባደረጉት ውል ለአመልካች ከምረቃ በኋላ ለስድስት አመታት አገልግልት ለመስጠት ግዳታ መግባታቸውን፣ከምረቃ በኋላ ተጠሪ ለአመልካች ሒያ ሁለት ወራትና አስራ አምስት ቀናት የማይበልጥ አገልግልት ከሰጡ በኋላ የስራ መልቀቂያ እንዱሰጣቸው ጥያቄ ሲያቀርቡ አመልካች የትምህርት ስልጠና ውለ ላይ የተመለከተውን የተጠሪን ግዳታ ምክንያት በማድረግ ለመስጠት ፈቃደኛ ሳይሆን የቀረ መሆኑን ነው።
በመሰረቱ የአዋጅ ቁጥር 515/1999 አንቀጽ 78/1/ ድንጋጌ ሲታይ በሕግ ወይም በውል የተቀመጡ ግዳታዎች እንደተጠበቁ ሆነው ማንኛውም የመንግስት ሰራተኛ በማንኛውም ጊዜ የአንድ ወር ቅድሚያ ማስጠንቀቂያ በመስጠት ስራውን በገዛ ፈቃደ ሉለቅ የሚችል ስለመሆኑ የተደነገገ ሲሆን የተጠቀሰው አንቀጽ በንኡስ አንቀጽ ሁለት ደግሞ በአንቀፁ ንኡስ አንድ ድንጋጌ ስር በተቀመጠው መሰረት የአንድ ወር ቅድሚያ ማስጠንቀቂያ ሳይሰጥ አገልግልቱን ያቋረጠ የመንግስት ሰራተኛ ግዳታውን ባለመወጣቱ ለሚደርሰው ጉዲት እንደተገቢነቱ በፍትሐብሕር እና በወንጀል ሕግ መሰረት ተጠያቂነት ያለበት ስለመሆኑ ተቀምጧል። የአዋጅ አንቀጽ 87 ድንጋጌ ሲታይም የአገልግልት የምስክር ወረቀት በማንኛውም የመንግስት ሰራተኛ በስራ ላይ እያለ ወይም በማናቸውም ምክንያት አገልግልት ሲያቋረጥ የስራ ልምድ ማስረጃ ከጠየቀ ሲያከናውን የነበረውን የስራ ዓይነት፣የአገልግልት ዘመኑና ሲከፈል የነበረውን ደመወዝ የሚገልጽ የአገልግልት የምስክር ወረቀት የሚሰጠው መሆኑን አስቀምጧል። ከዚህ ሁለ መገንዘብ የሚቻለው የአገልግልት ምስክር ወረቀት ለማንኛውም የመንግስት ሰራተኛ ከስራ ላይ እያለም ቢሆን የማይከለከል መሆኑን ሲሆን ሰራተኛው በመስሪያ ቤቱ የሚፈለግበት እዲ ካለ በሕጉ አግባብ ሰራተኛውን የመጠየቅ መብት ለመስሪያ ቤቱ በሕግ የተጠበቀ መሆኑን ነው። ይሁን እንጂ መስሪያ ቤቱ ከሰራተኛው የሚፈልገው እዲ አለ የሚል ከሆነ ለሰራተኛው የስራ ልምድ ምስክር ወረቀት ከመስጠት ባለፈ የስራ መልቀቂያ ወይም ክሉራንስ እንዱሰጠው የሚገደድበት ሕጋዊ ምክንያት የለም። ምክንያቱም እነዚህ ማስረጃዎች መስሪያ ቤቱ ከሰራተኛው ላይ የሚፈልገው እዲ ካለ በሕጉ አግባብ መብቱን ለማስጠበቅ የራሳቸውን የሆነ ጠቀሜታ ያላቸው ናቸውና። በመሆኑም አመልካች የተጠሪን የስራ ልምድ ምስክር ወረቀት የመስጠት በሕግ የተጣለበት ግዳታ ሲሆን የስራ መልቀቂያ እና ክሉራንስ ግን ከተጠሪ የሚፈልገው እዲ አለ የሚል እስከሆነ ድረስ በዚህ ረገድ ማስረጃ እንዱሰጥ የሚገደድ አይሆንም። የበታች ፍርድ ቤቶች አመልካች ለተጠሪ እንዱሰጠው የወሰኑት በአዋጁ አንቀጽ 87 መሰረት የስራ ልምድ ምስክር ወረቀት እንጂ የስራ መልቀቂያ እና ክሉራንስ ባለመሆኑ አመልካች በዚህ ረገድ ፍርድ ቤቶቹ ስህተት ፈጽመዋል በማለት ያቀረበው ክርክር ተቀባይነት ያለው ሆኖ አላገኘንም። በመሆኑም በጉዲዩ ላይ የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው ለማለት አልተቻለም። በዚህም ምክንያት ተከታዩን ወስነናል።
በፋዳራለ ሲቪል ሰርቪስ ኤጀንሲ አስተዲደር ፍርድ ቤት በይ/መ//2001 መጋቢት 22 ቀን 2001 ዓ.ም ተሰጥቶ በፋዳራለ ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ/ ሐምል 28 ቀን 2001 ዓ.ም የፀናው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ፀንቷል።
መዝገቡ ተዘግቷል፤ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.