No summary available.
መጋቢት 20 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሂሩት መለሰ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- የኢትዮጵያና ጅቡቲ ምድር ባቡር ድርጅት ተጠሪ፡- አቶ ምናለ በሪሁን መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የከፍተኛው ፍርድ ቤት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት ስላመለከተ ነው። ክርክሩ በመጀመሪያ የታየው በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሥራ ክርክር ችልት ነው። በሥር ፍርድ ቤት ተጠሪ አመልካች የሥራ ውል አላግባብና ማስጠንቀቂያ ሣይሰጠኝ ያቋረጠ በመሆኑ ውዝፍ ደመወዜን ከፍል ወደ ሥራ ይመልሰኝ የሚል ክስ አቅርቧል። አመልካች በተከሳሽነት ቀርቦ ተጠሪ የተቀጠረው ድርጅቱ በፍርድ ቤት የሚከራከርባቸው ጉዲዮች እስኪቃለለ ድረስ ለጊዜያዊነት ነገረ ፈጅ ሆኖ እንዱሰራ በመሆኑና ሥራው ያለቀ በመሆኑ ስንብቱ ህጋዊ ነው በማለት ተከራክሯል። የሥር ፍርድ ቤት የነገረፈጅ አገልግልት የሚጠይቀው ሥራ ያላለቀ በመሆኑ ስንብቱ ህገ-ወጥ ነው በማለት አመልካች የስድስት ወር ደመወዝ በመክፈል ወደ ሥራ ይመልሰው በማለት ወስኗል። በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት አመልካች ይግባኝ ለከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርቦ የከፍተኛ ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ አመልካች የአሥራ አምስት ቀን የቅድሚያ ማስጠንቀቂያ በመስጠት የሥራ ውለን የማቋረጥ መብት ያለው መሆኑ በሥራ ውለ ተገልጿል አመልካች የሥራ ውለን ለማቋረጥ የሚችል ቢሆንም የሥራ ውለን ያቋረጠው በሥራ ውለ መሰረት የአስራ አምስት ቀን ማስጠንቀቂያ በመስጠት ባለመሆኑና ሥርዓቱን ባለመጠበቁ አመልካች በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 377/96 የተለያዩ ድንጋጌዎች መሰረት የተለያዩ ክፍያዎችን ይክፈለ፣ ተጠሪ ወደ ሥራ መልስ ልባል አይገባውም በማለት የሥር ፍርድ ቤት ውሣኔን አሻሽል ወስኗል።
አመልካች የከፍተኛ ፍርድ ቤት ተጠሪን ለማሰናበት እንደምንችልና ማሰናበታችንም ተገቢ ነው ብል ከወሰነ በኋላ የተለያዩ ክፍያዎችን ተገቢነት የላላቸውን የህግ ድንጋጌዎች መሰረት በማድረግ እንድንከፍል መወሰኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው በማለት አመልክቷል። ተጠሪ የከፍተኛው ፍርድ ቤት እኔን በሚጎዲ ሁኔታ ውለንና ህጉን ከመተርጎሙ ውጭ አመልካችን የሚጎዲ መሰረታዊ የህግ ስህተት የለበትም በማለት መልስ ሰጥቷል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር ያቀረበው ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን ጉዲዩን መርምረናል። ጉዲዩን እንደመረመርነው አመልካች ከተጠሪ ጋር የነበረውን የሥራ ውል በማናቸውም ጊዜ የአስራ አምስት ቀናት ቅድሚያ ማስጠንቀቂያ በመስጠት ለማቋረጥ የሚችል መሆኑ የከፍተኛ ፍርድ ቤት የሥራ ውለን በማስቀረብ እንዲረጋገጠ በውሣኔው ገልጿል። ተጠሪ ሥራው ከማለቁ በፉት አመልካች የሥራ ውለን ማቋረጡ ተገቢ አይደለም በማለት ያቀረበው ክርክር ከአመልካችና ከተጠሪ የሥራ ውል በግልፅ የተመለከተውን ፍሬ ጉዲይ የሚቃረንና የህግ መሰረት የላለው ነው።
የከፍተኛው ፍርድ ቤት አመልካች ተጠሪን ከሥራ ያሰናበተው በውለ የተቀመጠውን ሥርዓት ማለትም የአስራ አምስት ቀናት የቅድሚያ ማስጠንቀቂያ ሣያሟላ መሆኑን አረጋግጧል። አመልካች ከተጠሪ ጋር ያለውን የሥራ ውል በውለ ከተመለከተው ሥርዓት ውጭ በአሰሪና ሰራተኛ ህግ ያለማስጠንቀቂያ ከሥራ ለማሰናበት የሚያስችል ሁኔታ ሣያጋጥመው ካቋረጠ በአዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀፅ 39(1/ለ) መሰረት በአንቀፅ 40 ንዐስ አንቀፅ 2፣ በአንቀፅ 44 እና በአንቀፅ 43 ንዐስ አንቀፅ 4(ለ) የተደነገጉትን ክፍያዎች ለተጠሪ የመክፈል ኃላፉነት አለበት በማለት የሰጠው ውሣኔ አግባብነት ያላቸውን የአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ ቁጥር 377/1996 ድንጋጌዎች መሰረት ያደረገና መሰረታዊ የህግ ስህተት የላለው በመሆኑ በፍትሐብሕር ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 348(1) መሰረት አፅንተነዋል።
ው ሣ ኔ
No topics extracted.