No summary available.
መጋቢት 06 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ሂሩት መለሰ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- የአ/አ ሂልተን ሆቴል - ጠ/ሃሳብከፊይ ጌራወርቅ ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ዮናስ ጥላሁን - ቀረቡ መዝገቡን መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል።
በዚህ መዝገብ የቀረበው ክርክር የሥራ ውል ማቋረጥን የሚመለከት ነው። ተጠሪ ከሥራው ጋር በተያያዘ ከባድ የማጭበርበር ድርጊት ፈጽሟል በማለት አመልካች ከሥራ ያሰናበተው ቢሆንም የሥር ፍ/ቤት ተጠሪ የፈፀመው ድርጊት ከስራ ለማሰናበት የሚያበቃ አይደለም ሲል በመወሰኑ የቀረበ አቤቱታ ነው።
ይህ ሰበር ችልትም የተጠሪ ድርጊት የሥራ ውልን ለማቋረጥ የሚያበቃ ስለመሆኑ ለመመርመር ተጠሪን አስቀርቧል። ከተያዘው ጭብጥ አንፃር የቀረበውን ክርክር ከሕጉ አገናዝበን መርምረናል።
ከሥር ፍ/ቤት መዝገብ መረዲት እንደተቻለው ተጠሪ የአመልካች ድርጅት ሰራተኛ ስለመሆኑ አላከራከረም።
ተጠሪው የሥራ ውል የተቋረጠው ለድርጅቱ ሰራተኞች በተዘጋጅ ካፍቴሪያ የውጪ ሰው አስገብቶ እንዱመገብ አድርጓል በሚል ነው። ተጠሪው ይህንን ድርጊት አልፈጸምኩም ሲል የካደ ቢሆንም የሥር ፍ/ቤት ምስክር ሰምቶ ተጠሪውን ድርጊቱን ፈጽሟል በማለት በውሳኔው አረጋግጧል። ነገር ግን የተጠሪ ድርጊት ከባድ የማጭበርበር ድርጊት ነው ልባል አይችልም በማለት ስንብቱ ሕገ-ወጥ ነው ብሎል።
ይህ ችልትም የተጠሪ ድርጊት በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 27/1/ሐ/ የሚሸፈን ስለመሆኑ መርምሯል። የተጠቀሰው አንቀጽ ድንጋጌ ይዘት “እንደጥፊቱ ክብደት በሥራው ላይ የማታለል ወይም የማጭበርበር ተግባር መፈጸም” የሥራ ውልን ያለማስጠንቀቂያ ለማቋረጥ እንደሚያስችል ያመለክታል። ተጠሪ ሥራው ሹፋር እንደነበር ተጠቅሷል። ተጠሪ ፈጽሟል የተባለው ድርጊት ደግሞ በሰራተኞች ካፍቴሪያ የውጪ ሰው አስገብቶ ጋብዟል የሚል ነው። ይህ ተግባር በራሱ በቀጥታ ከተጠሪው ሥራ ጋር የሚያያዝ አለመሆኑን መረዲት አዲጋች አይደለም።
ካፍቴሪያው ደግሞ በራሱ የቁጥጥር ሥርአት መስተንግድ እና አገልግልት እንደሚሰጥ መገንዘብ ይቻላል። በዚህ ረገድ ለዚህ የተመደቡት ሰራተኞች ተገቢውን ቁጥጥር ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው ግልጽ ነው። ይህ በእንዱህ እያለ ተጠሪው ከሥራ ጋር በተያያዘ የማታለል ወይም የማጭበርበር ተግባር ፈጽሟል ለማለት አይቻልም ሲል የሥር ፍ/ቤት የደረሰበትን ድምዲሜ ለማስተባበል የሚያስችል አሳማኝ የሕግም ሆነ የፍሬ ነገር ምክንያት በአመልካች በኩል አልቀረበም። ከዚህም ባሻገር ተጠሪው ፈጽሟል የተባለው ድርጊት በራሱ እንደሕጉ አገላለጽ እና እሳቤ “ከባድ የማጭበርበር ወይም የማታለል ተግባር” የሚያሰኝ ሁኔታ ስለመኖሩም አመልካች አላስረዲም። ስለሆነም የሥር ፍ/ቤቶች የተጠሪ ድርጊት ያልተገባ መሆኑን ተቀብለው እንደ ሕጉ አነጋገር ግን ከባድ የማጭበርበር ድርጊት ልባል አይችልም በዚህም የተነሳ ስንብቱ ሕገወጥ ነው በማለት የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈፀመበት ነው ለማለት የሚያስችል ሕጋዊ ምክንያት አላገኘንም። ስለሆነም ባለበት ሁኔታ በማጽናት ተከታዩን ወስነናል።
በዚህ መዝገብ ጥቅምት 26 ቀን 2002 ዓ.ም የተሰጠው የእግድ ትእዛዝ ተነስቷል። ይፃፍ።
No topics extracted.