No summary available.
መጋቢት 30 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ሐጎስ ወልደ ሂሩት መለሰ ብርሀኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- አልሀበሽ ሹገር ሚልስ ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር - ተወካይ አቶ ተካልኝ መለሰ ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ተገኔ ገ/ሃዋርያት - ከጠበቃ አብደራህማን መሐመድ ጋር ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የፋዳራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት በመዝገብ ሀምላ 17 ቀን 2001 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔና የከፍተኛው ፍርድ ቤት ጥቅምት 2 ቀን 2002 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት ስላመለከተ ነው።
ክርክሩ የታየው በመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ነው። በሥር ፍርድ ቤት ተጠሪ በከሳሽነት ቀርቦ በወር ብር 10,000(አስር ሺህ ብር) እየተከፈለው በአመልካች ድርጅት ሢሰራ እንደነበር ገልፆ አመልካች መጋቢት 11 ቀን 2001 ዓ.ም ከሥራ አላግባብ ያሰናበተኝ ስለሆነ ወደ ሥራ እንድመለስ ወይም የተለያዩ ክፍያዎች እንዱከፍለኝ በማለት ከስ አቅርቧል። አመልካች በተከሳሽነት ቀርቦ ተጠሪን ያሰናበተው መኪናና ሹፋር ተመድቦለት እየተገለገለ እያለ ታህሣሥ 30 ቀን 2001 ዓ.ም የድርጅቱን መኪና ቁልፍ ከሹፋሩ በመረከብ በማሽከርከር ላይ እያለ የድርጅቱን መኪና በማጋጨት ጉዲት አድርሷል። ስለዚህ ስንብቱ ህጉን መሰረት ያደረገ በመሆኑ የከሳሽ (ተጠሪ) ጥያቄ ተገቢነት የለውም የሚል ክርክር አቅርቧል። የሥር ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክር ለመደገፍ ያቀረቡትን ማስረጃ ሣይሰማና ሣይመረምር አመልካች ተጠሪን ያሰናበተው የሥራ ስንብት ደብዲቤ ፅፍ ሣይሆን በቃል በመሆኑ ስንብቱ ህገ-ወጥ ነው በማለት አመልካች ለተጠሪ የአምስት ወር ደመወዝ በመክፈል ወደሥራው እንዱመልሰው በማለት ወስኗል።
አመልካች ለዚህ ችልት የቀረበው የሰበር አቤቱታ ተጠሪ ከሥራ የተባረረው በጥፊቱ ነው። ተጠሪን የጥፊቱ ተጠቃሚ የሚያደርግ ውሣኔ መሰጠቱ የህግ ስህተት ያለበት ውሣኔ ነው። ተጠሪ ከሥራ የተባረረው የሥራ ውለ ሉጠናቀቅ አንድ ወር ሲቀረው በመሆኑ የአምስት ወር ደመወዝ ከፍላችሁ ወደሥራ መልሱ በማለት የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ችልት ማስረጃችንን በመቀበል ውሣኔ ይሰጥልን በማለት አመልክቷል።
ተጠሪ በበኩለ እኔ የተቀጠርኩት ላልተወሰነ የሥራ ጊዜ ነው። ስለዚህ አመልካች የሥራ ውለ ሉጠናቀቅ አንድ ወር ሲቀረው ነው ያሰናበትኩት በማለት ያቀረበው ክርክር የህግ መሰረት የለውም። አመልካች በህጉ የተመለከተውን ሥርዓት ሣያሟላ ከሥራ ማሰናበቱ ህገ-ወጥ ስለሚያደርገው የበታች ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የለበትም በማለት መልስ አቅርቧል። አመልካች የመልስ መልስ አቅርቧል።
ከሥር የቀረበው ክርክርና በሰበር ያቀረበው የፅሐፍ ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም ጉዲዩን መርምረናል።
ጉዲዩን እንደመረመርነው የበታች ፍርድ ቤቶች አመልካች ተጠሪን ከሥራ ያሰናበተው በፅሐፍ ሣይሆን በቃል መሆኑ ብቻ ስንብቱ ህገ-ወጥ መሆኑን ያሣያል በማለት አመልካች ተጠሪን የአምስት ወር ደመወዝ ከፍል እንዱመልስ በማለት የሰጠው ውሳኔ ተገቢ ነው ወይስ አይደለም? በሚለው ጭብጥ እልባት ማግኘት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
ለዚሀ ጭብጥ እልባት ለመስጠት በመጀመሪያ የሥር ፍርድ ቤት አመልካችና ተጠሪ የሚከራከሩበትን መሰረታዊ ጭብጥ በመለየትና በመመሥረት ለክርክሩ እልባት የሰጠ መሆኑን መመርመር ያስፈልጋል። አንድ ጭብጥ የሚመሰርተው ከሳሽ በክሱ የገለፀውን ተከሳሹ ክድ የሚከራከር ሲሆን እንደሆነ በፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 247 ተደንግጓል። ተጠሪ አመልካች አላግባብ ከሥራ ያሰናበተው መሆኑን ገልፆ ክስ ያቀረበ ሲሆን አመልካችም ተጠሪን ከሥራ አላሰናበትኩትም የሚል ክርክር አላቀረበም። አመልካች ተጠሪን ከሥራ አሰናብቸዋለሁ በማለት በግልፅ መልስ ሰጥቷል።
ስለሆነም አመልካች ከተጠሪ ጋር ያለውን የሥራ ውል ማቋረጡ ግራቀኙ የሚተማመኑበት ነጥብ በመሆኑ ስንብቱ በፅሐፍ ነው ወይስ በቃል የሚል ማጣሪያ ማድረግ የሚያስፈልገው አይደለም። በአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀፅ 27 ንዐስ አንቀፅ 2 መሰረት አሰሪው ለሰራተኛው የሥራ ውለ ያቋረጠበትን ምክንያት በፅሐፍ አለመግለፁ ብቻውን ስንብቱን ህገ ወጥ የሚያደርግ አይደለም። አሰሪው ይህንን ሣይፈፅም ቢቀርና በፅሐፍ ሣይሆን በቃል ወይም በድርጊት የሥራ ውለን ቢያቋርጥ የሥራ ውለን ለማቋረጥ የሚያበቃ ምክንያት ያለው መሆኑን ከመከራከርና ማስረጃ ከማቅረብ የሚገድብ አይደለም። ከዚህ አንፃር ስንመለከተው የሥር ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ማስረጃ ሣይሰማና ግራቀኙ የሚከራከሩበትን ጭብጥ ሣይመሰርት ስንብቱ በፅሐፍ ያልተደረገ በመሆኑ ብቻ አመልካች ከተጠሪ ጋር ያለውን የሥራ ውል አላግባብ አሰናብቷል በማለት የሰጠው የሕግ ትርጉምና ውሣኔ ተገቢ ሆኖ አላገኘነውም።
በአንድ ጉዲይ ጭብጥ የሚመሰረተው ከሳሽ ያቀረበውን ክስና ማስረጃ ተከሳሽ የሚሰጠውን የመከላከያ መልስና ማስረጃና ፍርድ ቤቱ በፍትሐብሕር ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 241 መሰረት በሚያደርገው የቃል ምርመራ የተሰጠ መልስ መሰረት በማድረግ መሆን እንዲለበት የፍትሐብሕር ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 248 ይደነግጋል። በዚህ ጉዲይ አመልካች ከተጠሪ ጋር ያለውን የሥራ ውል ማቋረጡ አከራካሪ ጭብጥ አይደለም። አከራካሪው ጭብጥ አመልካች በድርጅቱ መኪና ላይ ጉዲት በማድረሡና ያለማስጠንቀቂያ የሥራ ውለን ለማሰናበት የሚችል ጥፊት በመፈፀሙ ስንብቱ ህጋዊ ነው የሚል ክርክር ያቀረበና ይህንን ለማስረዲት የማስረጃ ዝርዝር መግለጫ ያቀረበ መሆኑን ከሥር ፍርድ ቤት ውሣኔ ለመገንዘብ ችለናል። ስለሆነም የሥር ፍርድ ቤት አመልካችና ተጠሪ የሚካካደበትን ይህንን ጭብጥ በመመሥረትና በማስረጃ በማጣራት ውሳኔ መስጠት ሲገባው የሥራ ስንብቱ በቃል የተደረገ መሆኑ ብቻውን ስንብቱ ህገወጥ መሆኑን ያሣያል በማለት የሰጠውን ውሣኔ ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ሣያርም እንዲለ ማፅናቱ መሰረታዊ የህግ ስህተት ነው በማለት ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሣኔ ተሽሯል።
የፋዳራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት አመልካች ተጠሪን ከሥራ ያሰናበተው ሰራተኛው(ተጠሪ) ከሥራ ሉያሰናብት የሚችል ጥፊት በመፈፀሙ ነው ወይስ አይደለም የሚለውን ጭብጥና ላልች ነጥቦች ለማስረዲት በግራ ቀኙ በኩል ያቀረበውን ክርክርና ማስረጃ ሰምቶ ውሣኔ እንዱሰጥ ጉዲዩን በፍትሐብሕር ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 343(1) መሰረት መልሰን ልከንለታል።
በዚህ ፍርድ ቤት የወጡትን ወጭና ኪሣራ ግራቀኙ ለየራሳቸው ይቻለ።
ይህ ፍርድ በፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት በሙለ ድምፅ ተሰጠ።
No topics extracted.