No summary available.
መጋቢት 30 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ሐጎስ ወልደ ሂሩት መለሰ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- በቦላ ክፍለ ከተማ ቀበላ 02/01 የመዝናኛ ክበብ - ጠበቃ አሰፊ ዝቅአርጋቸው ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ማስረሻ ሁሴን - ቀረቡ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ የአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ ቁጥር 377/96“ን” መሰረት ያደረገ ሲሆን ክርክሩ የተጀመረውም በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የአሁኑ ተጠሪ ባሁኑ አመልካች ላይ በመሰረቱት ክስ ነው። ክሳቸውም ሰኔ 01 ቀን 2001 ዓ.ም የተፃፈ ሁኖ ይዘቱም ባጭሩ በአመልካች ድርጅት ውስጥ ከነሐሴ 01 ቀን 1997 ዓ.ም ጀምሮ ተቀጥረው በወር ደመወዝ ብር 314(ሦስት መቶ አስራ አራት) እየተከፈላቸው በመስራት ላይ እንዲለ ያላግባብ ግንቦት 24 ቀን 2001 ዓ.ም ከስራ የተሰናበቱ መሆኑን በመግለፅ የተለያዩ ክፍያዎች እንዱከፈላቸው ይወሰንላቸው ዘንድ ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው። የአሁኑ አመልካችም ለክሱ በሰጠው መልስ፤ ስንብቱ የተከናወነው ተጠሪ የድርጅቱን ትዕዛዝ ባለማክበራቸው ስለመሆኑ በመግለፅ ክሱ ውድቅ ላሆን ይገባል ሲል ተከራክሯል። ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ መርምሮ ስንብቱ ሕገ-ወጥ ነው በማለት አመልካች ድርጅት ለተጠሪ የስራ ስንብት፣ የካሣ፣ የማስጠንቀቂያ ጊዜ ክፍያ እና የፔሮቪደንት ፈንድ ክፍያ እንዱከፍላቸው ሲል ወስኗል።
በዚህ ውሳኔ አመልካች ባለመስማማት ይግባኙን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቢያቀርብም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 337 መሰረት ተሰርዞበታል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ በመቃወም ለማስቀየር ነው።
የአመልካች ጠበቃ ጥቅምት 06 ቀን 2002 ዓ.ም በፃፈት ሦስት ገጽ የሰበር አቤቱታ በበታች ፍርድ ቤቶች ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል የሚለበትን ምክንያት ዘርዝረው አቅርበዋል። ይዘቱም ባጭሩ ተጠሪ የተሰናበቱት የአመልካችን ትዕዛዝ ሉያከብሩ ባለመቻላቸው መሆኑ ተረጋግጦ እያለ የስር ፍርድ ቤት ለሕብረት ስምምነቱ አፈፃፀም የተዛባ ትርጉም በመስጠት ስንብቱ ሕገ-ወጥ ነው በማለት መወሰኑ ያላግባብ ስለሆነ ሉታረም ይገባል በማለት መከራከራቸውን የሚያሳይ ነው። አቤቱታው ተመርምሮም ስንብቱ ሕገ-ወጥ ነው በማለት መወሰኑ ባግባቡ መሆን ያለመሆኑን ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ ለሰበር ችልቱ እንዱቀርብ ተደርጎ ተጠሪ ጥር 25 ቀን 2002 ዓ.ም በተጻፈ ሁለት ገጽ ማመልከቻ መልሳቸውን ሰጥተዋል። የአመልካች ጠበቃም የካቲት 09 ቀን 2002 ዓ.ም በተጻፈ ማመልከቻ የመልስ መልሳቸውን ሰጥተዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩ ለሰበር ችልት ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ አንፃር በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው ተጠሪ የአመልካች ሰራተኛ ሆነው በሚሰሩበት የስራ ሰዓት ወቅት አመልካች የድራፍት በርሜል እንዱረከቡ ትዕዛዝ ሲያስተላልፍላቸው ሉቀበለ ያልቻለ መሆኑ የስር ፍርድ ቤት አረጋግጦ ይህ የተጠሪ ድርጊት ከስራ ለመሰናበት ሕጋዊ ምክንያት አይደለም ለማለት የቻለው በሕብረት ስምምነቱ እንደጥፊት ቢጠቀስም ሰራተኛው ትዕዛዙ ሕገ-ወጥ እስከሆነ ድረስ ለመቃወም የሚችል ስለመሆኑ በአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀፅ 13(2) ድንጋጌ መረዲት ይቻላል በሚል ነው። በእርግጥ አንድ ሰራተኛ በስራ ውለ ላይ የተጣለውን ግዳታ የመወጣት ኃላፉነት ያለው ስለመሆኑ ይኸው የተጠቀሰው ድንጋጌ ያሳያል። በልላ በኩል በአዋጁ በአንቀጽ 27(1/ሸ) ድንጋጌ ሕጉ ካስቀመጣቸው በተጨማሪ በሕብረት ስምምነቱ ላይ ከስራ ሉያስባርሩ የሚችለ ጥፊቶችን መወሰን እንደሚቻል ተመልክቷል።
ወደ ተያዘው ጉዲይ ስንመለስም አመልካች ተጠሪን ከስራ ሉያሰናብታቸው የቻለው በሕብረት ስምምነቱ መሆኑን በመጥቀስ የሚከራከር ሲሆን የህብረት ስምምነቱ አለመታዘዝ ከማስጠንቀቂያ በኋላ ከስራ ሉያስባርር እንደሚችል ተቀምጧል። የስር ፍርድ ቤት ይህ የሕብረት ስምምነቱ ክፍል በዚህ መልኩ መቀመጡ የተረጋገጠ ቢሆንም ተቀባይነት የለውም ያለው ለሰራተኛው ከሕጉ ከተቀመጠው ጥቅም ያነሰ ያስገኛል በሚል ነው። ይሁን እንጂ ሕጉ ከሕጉ ከተቀመጡት ጥፊቶች ውጪ በሕብረት ስምምነቱ ያለማስጠንቀቂያ ከስራ ሉያስባርሩ ይችላለ ተብል መደንገግ የሚቻል መሆኑን ከማስቀመጡም በላይ በአዋጁ አንቀፅ 134(2) መሰረት የሕብረት ስምምነቱ ለሰራተኛው ሕጉ ካስቀመጠው ጥቅም ያነሰ የሚያስገኝ ሆኖ ከተገኘ ተፈፃሚነት የላለው መሆኑን አስቀምጧል። ከእነዚህ ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ መገንዘብ የሚቻለው ጥፊትና ጥቅምን በተመለከተ ሕጉ የተለያየ አቋም የያዘ መሆኑን እንጂ አሰሪና ሰራተኛ በሕብረት ስምምነቱ ያለማስጠንቀቂያ ከስራ ሉያሰናብት የሚችል ጥፊት በማለት የተስማሙበት ድርጊት ተቀባይነት የለውም የሚለውን ነጥብ አይደለም። አንድ ሰራተኛ የአሰሪውን ትዕዛዝ ማክበርም ተገቢነት ያለው ስለመሆኑ የአዋጁ አንቀጽ 13(7) ድንጋጌ ያስገነዝባል። በመሆኑም የስር ፍርድ ቤት የደረሰበት መደምደሚያ ህጋዊ መሰረት የላለው ሲሆን ይግባኝ ሰሚ ቤትም ይህንኑ ሳያርም ማለፈ ተገቢነት ያለው ሆኖ አላገኘነውም። በዚህም ምክንያት በጉዲዩ ላይ የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ሥህተት ያለበት ሆኖ አግኝተናል፤ ተከታዩንም ወስነናል።
ው ሣ ኔ
በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ ሐምል 09 ቀን 2001 ዓ.ም ተሰጥቶ በፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ነሐሴ 21 ቀን 2001 ዓ.ም በትዕዛዝ የፀናው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሰረት ተሽሯል።
አመልካች ከተጠሪ ጋር የነበረውን የስራ ውል ያቋረጠው በሕጉ አግባብ ነው ብለናል። በመሆኑም ተጠሪ ከፔሮቪደንት ፈንድ ውጪ የሚከፈላቸው ክፍያ የለም ብለናል።
ለክርክሩ የወጣውን ወጪና ኪሳራ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
No topics extracted.