No summary available.
መጋቢት 20 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ኂሩት መለሰ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- የሸቀጦች ጅምላ ንግድና አስመጪ ድርጅት - ነ/ፈጅ ታደለ ገ/ወልድ ተጠሪ፡- አቶ አንማው ላቀው - ቀረቡ
በዚህ መዝገብ የቀረበው ጉዲይ የስራ ክርክርን የሚመለከት ነው። ተጠሪ በደብረ-ማርቆስ ከተማ ወረዲ ፍ/ቤት ባቀረቡት ክስ አመልካች ድርጅት ያለአግባብ ከስራና ከደሞዝ ስላገዲቸው ወደ ስራቸው እንዱመለሱ ካልቻለ የስንብት ክፍያ እንዱከፈላቸው ጠይቀዋል። አመልካች ድርጅት ለክሱ በሰጠው መልስ ተጠሪ የፈፀሙት ድርጊት በዱሲፑሉን ታይቶ ተጠሪ ለአንድ ወር በታገደበት ላለው ጊዜ ደሞዝ ሳይከፈላቸው ወደ ስራ እንዱመለሱ ስለተወሰነ ደሞዝ ሉከፈላቸው አይገባም ብሎል። ፍ/ቤቱም ክርክሩን መርምሮ አመልካች ተጠሪን ያገደው ያለአግባብ መሆኑን አምኖበት ወደ ስራ ስለመለሳቸው የመስከረምና የጥቅምት ወር ደሞዛቸው ይከፈላቸው በማለት ወስኗል። በዚህ ውሳኔ ላይ አመልካች ለምስ/ጏጃም አስተዲድር ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ ቢያቀርብም ፍ/ቤቱ ተጠሪን ሳይጠራ መዝገቡን ዘግቶታል። አመልካች በዚህ ውሳኔ ላይ ለአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት አቤቱታ አቅርቦ በድምጽ ብልጫ አቤቱታው ውድቅ ተደርጏበታል።
የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሳኔ ላይ ነው። አመልካች በቅሬታው ተጠሪ ጥፊተኛ ሆነው በመገኘታቸው የመጨረሻ የፁሁፍ ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው መሆኑ ተገልፆ እያለ ከስራ የታገደት ያለአግባብ መሆኑ ታምኖበት ወደ ስራ ስለተመለሱ ደሞዛቸው ይከፈላቸው መባለ ስህተት ነው፣አሰሪ ሰራተኛው ጥፊተኛ ሆኖ ካገኘው ለ30 ቀናት ከደሞዝና ከስራ አግድ ለማቆየት እንደሚችል አዋጁ ስልጣን ስለሚሰጠው ለታገደበት ጊዜ ደሞዝ እንዱከፈላቸው የተሰጠው ውሳኔ የሕግ ስህተት አለበት ብሎል። ይህ ችልትም ተጠሪ በቀረበበት የዱሲፑሉን ክስ ምክንያት ለታገደበት ጊዜ ደሞዝ ይከፈላቸው የመባለን አግባብነት ለመመረመር አቤቱታው ለሰበር ችልት ያስቀርባል ብሎል። ተጠሪም ለቀረበባቸው አቤቱታ መልሳቸውን በፁሁፍ አቅርበዋል። በመልሳቸውም አመልካች ጥፊት ሳይፈጽሙ ለአንድ ወር ከስራና ከደሞዝ ታግደው የመጨረሻ ደረጃ የፁሁፍ ማስጠንቀቂያ የሰጣቸው ያለአግባብ መሆኑን በመግለጽ የስር ፍ/ቤት ውሳኔ እንዱፀናላቸው ጠይቀዋል። ችልቱም መዝገቡን ከተያዘው ጭብጥ አኳያ እንደሚከተው መርምሯል።
ተጠሪ ከስር ፍ/ቤት ክስ የመሰረቱት አመልካች ያለአግባብ ከስራና ከደሞዝ ስላገዲቸው ለታገደበት ጊዜ ደሞዝ እንዱከፈላቸውና ወደ ስራ እንዱመልሳቸው ጠይቀዋል። አመልካች በበኩለ ተጠሪ ለፈፀሙት ጥፊት ጉዲዩ በዱሲፑሉን እስከሚታይ ድረስ ከደሞዝና ከስራ ማገድ ስለሚችል ጥያቄው ውድቅ እንዱሆንለት አመልክቷል። አመልካች ለክርክሩ መሰረት ያደረገው አ/ቁ. 377/1996 እና የድርጅቱን ህብረት ስምምነት ነው። በዚህ ጉዲይ በጭብጥነት ላታይ የሚገባው ተጠሪ ከስራና ከደሞዝ ለታገደበት ጊዜ ደሞዝ ሉከፈላቸው የሚገባ መሆን አለመሆኑ ነው። ይህንንም ጭብጥ ለመመለስ ችልቱ የአሰሪና ሰራተኛ አዋጁንና በወቅቱ በስራ ላይ የነበረውን የድርጅቱን ህብረት ስምምነት ተመልክቷል። በአ/ቁ 377/96 አንቀጽ 27/4/ ስር ያለማስጠንቀቂያ የሰራተኛውን የስራ ውል እንዱቋረጥ ከመደረጉ በፉት ሰራተኛውን ከስራ አግድ ማቆየት ስለሚቻልበት ሁኔታ በህብረት ስምምነት ሉወሰን እንደሚችልና የእገዲው ጊዜ ግን ከ30 ቀናት እንደማይበልጥ ተደንግጓል። አመልካች የሚከራከረው የድርጅቱ ህብረት ስምምነት ጥፊት የፈፀመ ሰራተኛ ጉዲዩ በዱሲፑሉን እስከሚታይ ለ30 ቀን ከስራና ከደሞዝ አግድ ማቆየት እንደሚቻል ተደንግጓል በማለት ነው። ተጠሪ ጥፊቱን ፈጽመዋል ተብለው ከስራ የታገደት ከመስከረም 2001 ዓ.ም ጀምሮ በመሆኑ ችልቱ በወቅቱ በስራ ላይ የነበረውን የድርጅቱን የህብረት ስምምነት ተመልክቷል። በዚህ ህብረት ስምምነቱ አንቀጽ 51 ስር ማንኛውም ሰራተኛ ከባድ ጥፊት በመፈፀሙ ምክንያት ጥፊቱ ተጣርቶ ውሳኔ አስከሚሰጥበት ድረስ ከ30 ቀናት ላልበለጠ ጊዜ ከመደበኛ ሥራው ያለደሞዝ እንዱታገድ ማድረግ እንደሚቻልና ለውሳኔው መዘግየት ሰራተኛው ራሱ ምክንያት መሆኑ ካልተረጋገጠ በስተቀር ከ30 ቀናት በላይ ላለው ጊዜ ደመወዝ እንደሚከፈለው ተመልክቷል። በመሆኑም ሰራተኛው ጥፊት ሲገኝበት ጉዲዩ እስከሚጣራ ለአንድ ወር ከስራና ደሞዝ ሉያግደው እንደሚችል የአመልካች ድርጅት ህብረት ስምምነት ይፈቅዲል። ይህ ደግሞ አዋጁን መሰረት አድርጏ የወጣ የስምምነት ቃል በመሆኑ ተጠሪ ላይ ተፈፃሚ ላሆን የሚችል ነው። በመሆኑ አመልካች ተጠሪ ፈጸሙ ያለውን ጥፊት እስከሚያጣራ ከስራና ላገደበት ጊዜ ደሞዝ እንዱከፍል አይገደድም። የስር ፍ/ቤት አዋጅንና የህብረት ስምምነቱን ድንጋጌዎች ሳይመረመር ተጠሪ ከስራ ለታገደበት ጊዜ ደሞዝ እንዱከፈል የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው።
በልላ በኩል ተጠሪ ከስራ የታገደት ለሁለት ወራት መሆኑና የሁለት ወር ደሞዝ ያልተከፈላቸው ስለመሆኑ ከመዝገቡ ተረድተናል። ነገር ግን ከፍ ሲል እንደተመለከትነው ሰራተኛው ከስራና ደሞዝ ሉታገድ የሚችለው ለ30 ቀናት ብቻ ነው። የህብረት ስምምነቱ ከ30 ቀን ደሞዝ የማይከፈለው ውሳኔው የዘገየው በሰራተኛው ምክንያት ከሆነ ብቻ እንደሆነ ቢደነግግም አመልካች ውሳኔው በተጠሪ ምክንያት ስለመዘግየቱ ያቀረበው ክርክርም ሆነ ማስረጃ የለም።
በመሆኑም ተጠሪ ለሁለት ወራት ከስራና ከደሞዝ መታገዲቸው አዋጁንም ሆነ የሕብረት ስምምነቱን የሚቃርን በመሆኑ አመልካች ለተጠሪ የመስከረም ወር እንዱከፈላቸው መወሰኑ በአግባቡ ሆኖ አግኝተነዋል። በመሆኑም ተከታዩን ውሳኔ ተሰጥቷል።
የደብረ-ማርቆስ ወረዲ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 5852 ታህሣሥ 21 ቀን 2001 ዓ.ም የሰጠው ብይን፣ምስ/ጏጃም አስተዲደር ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 96588 ጥር 4 ቀን 2001 ዓ.ም የሰጠው ትእዛዝና የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ቁ. 00973 ግንቦት 18 ቀን 2001 ዓ.ም የሰጠው ትእዛዝ ተሻሽሎል።
ተጠሪ ከስራ ለታገደበት አንድ ወር ጊዜ ደሞዝ ሉከፈላቸው አይገባም ብለናል።
ተጠሪ ያልተከፈላቸው የመስከረም ወር 2001 ዓ.ም ደሞዛቸው እንዱከፈል የተሰጠው ውሳኔ ፀንቷል።
ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የራሳቸውን ይቻለ።
No topics extracted.