No summary available.
መ/ የካቲት 25 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ መንበረፀሐይ ታደሰ ሂሩት መለሰ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- የኮንስትራክሽንና ቢዝነስ ባንክ አ.ማ - ነ/ፈጅ አስቴር በቀለ ቀረቡ ተጠሪ፡-
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ የአዋጅ ቁጥር 377/96“ን” መሰረት ያደረገ ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ ተጠሪዎች በአሁኑ አመልካች ላይ በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሐምል 29 ቀን 2000 ዓ.ም በመሰረቱት ክስ መነሻ ነው። የክሱ ይዘትም ባጭሩ ከአመልካች ጋር የአሰሪና ሰራተኛ ግንኙነት እንደነበራቸው፣ ይህ ግንኙነታቸው የተቋረጠው በተጠሪዎች ፈቃድ መሆኑን፣ የስራ ውለ ሲቋረጥ ሉከፈላቸው የሚገባው ደመወዝ ሳይከፈላቸው የቀረ መሆኑን፣ ልዩነቱ መከሰቱን ያወቁት መንግስት የደመወዝ ጭማሪ ወይም ማስተካከያ ማድረጉን የካቲት 28 ቀን 2000 ዓ.ም ከጻፈው ደብዲቤ መሆኑን፣ የደመወዝ ማስተካከያው ከሕዲር 01 ቀን 2000 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ እንዱሆን መወሰኑን፣ በዚህም መሰረት አንደኛ ተጠሪ ሉከፈላቸው ከሚገባው ደመወዝ ብር 6338.84(ስድስት ሺህ ሶስት መቶ ሰላሳ ስምንት ብር ከሰማንያ አራት ሳንቲም)፣ ሁለተኛ ተጠሪ ደግሞ .93(አስራ አራት ሺህ አራት መቶ ሰላሳ ከዘጠና ሶስት ሳንቲም) መሆኑን ገልፀው ይኸው በልዩነት የመጣውን ገንዘብ አመልካች እንዱከፍላቸው ይወሰንላቸው ዘንድ ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው። የአሁኑ አመልካች ለከሱ በሰጠው መልስም የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ እና የፍሬ ነገር መከራከሪያ ነጥቦችን በማንሳት ተከራክሯል። ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ክርክር እና ማስረጃ ከመረመረ በኋላ አመልካች በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያነት ያቀረባቸውን የመከራከሪያ ነጥቦችን ውድቅ ከማድረጉም በላይ ለተጠሪዎች ክስ ኃላፉነት አለበት በማለት የክሱን ገንዘብ ለተጠሪዎች እንዱከፍል ወስኗል። በዚህ ውሳኔ አመልካች ባለመስማማት ይግባኙን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቢያቀርብም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 337 መሰረት ተሰርዞበታል።
የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ ለማስቀየር ነው።
የአመልካች ነገረ ፈጅ ሐምል 24 ቀን 2001 ዓ.ም በፃፈት ሁለት ገፅ የሰበር ማመልከቻ በበታች ፍርድ ቤቶች ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈፅሟል የሚለበትን ምክንያት ዘርዝረው አቅርበዋል። ይዘቱም ባጭሩ የስር ፍርድ ቤት በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያነት የቀረቡትን የአመልካችን መከራከሪያ ነጥቦችን ውድቅ ያደረገው ያላግባብ መሆኑን፣ ተጠሪዎች ከአመልካች ጋር የነበራቸው የስራ ግንኙነት በገዛ ፈቃዲቸው ከተቋረጠ በኋላ መንግስት ያደረገው የደመወዝ ማስተካከያ እንዱከፈላቸው የተወሰነው ከመመሪያው ዓላማና መንፈስ ውጪ መሆኑን ዘርዝረው ውሳኔው ሉሻር ይገባል በማለት ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው። አቤቱታቸው ተመርምሮም ተጠሪዎች ከአመልካች ድርጅት ስራ ከለቀቁ በኋላ ተፈቀደ የተባለው የደመወዝ ስኬል ጭማሪ ተጠሪዎችን ይመለከታል ወይስ አይመለከታቸውም? የሚለውን እና ላልችን ነጥቦች ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ ለሰበር ችልት እንዱቀርብ ተደርጎ የተጠሪዎች ጠበቃ ሕዲር 23 ቀን 2002 ዓ.ም በፃፈት ሁለት ገፅ ማመልከቻ የበታች ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ተገቢነት አለው የሚለባቸውን ምክንያቶች ጠበቃ ክፍላ ታደሰ ቀረቡ ዘርዝረው አቅርበዋል። የአመልካች ነገረ ፈጅ በበኩላቸው ሕዲር 25 ቀን 2002 ዓ.ም በጻፈት ሁለት ገጽ ማመልከቻ የሰበር አቤቱታቸውን አጠናክረው ተከራክረዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩ ለሰበር ችልት ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ አንጻር በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው በአመልካችና በተጠሪዎች መካከል የነበረው የአሰሪና ሰራተኛ ግንኙነት በተጠሪዎች ፈቃድ ከጥር 03 ቀን 2002 ዓ.ም ጀምሮ መቋረጡን፣ በዚህ ወቅት ተጠሪዎች ከአመልካች ድርጅት ሲሰናበቱ በወቅቱ ሉከፈላቸው ይገባል የተባለው የተለያየ ክፍያ መከፈለን፣ ተጠሪዎች ሐምል 29 ቀን 2000 ዓ.ም በተጻፈ ማመልከቻ በአመልካች ላይ ክስ ሉመሰርቱ የቻለት የካቲት 28 ቀን 2000 ዓ.ም የደመወዝ ጭማሪ መመሪያው ተፅፍ ከህዲር 01 ቀን 2000 ዓ.ም ጀምሮ ጭማሪው ተግባራዊ እንዱሆን ከተወሰነ በኋላ መሆኑን ነው። እንግዱህ ተጠሪዎች የመብት ጥያቄው ምንጭ ነው የሚለት የስራ ውለ ከመቋረጡ በፉት ለሰሩበት ስራ በደመወዝ ጭማሪ መመሪያው መሰረት ሉከፈለን የሚገባው የደመወዝ ልዩነት አለ በማለት ነው።
No topics extracted.
በመሰረቱ አንድ ሰራተኛ ከአሰሪው ጋር በሚፈጥረው የስራ ግንኙነት መሰረት ሕጉ የሚፈቀደው ማንኛውም መብት የሚጠበቅለት መሆኑ አከራካሪ አይሆንም። የአንድ መብት ወይም ግዳታ መሰረት ደግሞ ሕግ ወይም ውል መሆኑ ይታወቃል። በተያዘው ጉዲይም ምላሽ የሚያስፈልገው አቢይ ነጥብ ተጠሪዎች የጠየቁትን ክፍያ የሚያገኙበት የሕግ መሰረት አለ ወይስ የለም? የሚለው ነው። አመልካች አጥብቆ የሚከራከረው የደመወዝ ስኬል ማስተካከያ መመሪያው ከመውጣቱ በፉት ተጠሪዎች በገዛ ፈቃዲቸው ስራቸውን ስለለቀቁ መመሪያው በስራ ላይ ያለትን ሰራተኞች ለማበረታታት የወጣ እንደመሆኑ መጠን ሉከፈላቸው የሚገባ ቀሪ ደመወዝ የለም በማለት ነው። ለጉዲዩ አግባብነት አለው የተባለው መመሪያም የወጣበት መሰረታዊ ዓላማ ሲታይ የፊይናንስ ድርጅቶች ሰራተኞች የሆኑት በጭማሪው ተነቃቅተው ከፍተኛ ውጤት ለማስመዝገብ ስለመሆኑ በመግቢያው ላይ የተገለፀ መሆኑን የስር ፍርድ ቤትም ያረጋገጠው ጉዲይ ነው።
የመመሪያው መሰረታዊ ዓላማ ይህ ከሆነ መመሪያው ከመውጣቱ በፉት ስራውን በገዛ ፈቃደ የለቀቀ ሰራተኛ ወደኋላ ተመልሶ ማስተካከያውን መሰረት አድርጎ ቀሪ ደመወዝ ሉከፈለኝ ይገባል በማለት የሚያቀርበው የዲኝነት ጥያቄ ተቀባይነት የሚያገኝበት የሕግም ሆነ የስነ አመክንዮ(ልጂክ) አግባብ የለም። በመሆኑም የስር ፍርድ ቤቶች የተጠሪዎችን የዲኝነት ጥያቄ ከመመሪያው ዓይነተኛ ዓላማ ጋር በማዛመድ መመልከት ሲገባቸው ይህንኑ ሳያደርጉ የአመልካችን ክርክር ውድቅ በማድረግ ለተጠሪዎች በቀሪነት የሚፈለጉት ደመወዝ ይከፈል በማለት የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ አግኝተናል። በዚህም ምክንያት ተከታዩን ወስነናል።
በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ መጋቢት 30 ቀን 2001 ዓ/ም ተሰጥቶ በፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ሐምል 06 ቀን 2001 ዓ.ም በትዕዛዝ የፀናው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሰረት ተሽሯል።
ተጠሪዎች ከአመልካች ጋር የነበራቸውን የስራ ግንኙነት በገዛ ፈቃዲቸው ከለቀቁ በኋላ በወጣው የደመወዝ ጭማሪ ማስተካከያ መመሪያ መሰረት የሚከፈላቸው ቀሪ ደመወዝ የለም ብለናል።
ለክርክሩ የወጣውን ወጪና ኪሳራ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።