No summary available.
የሰ/መ/ የካቲት 24 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ መንበረፀሐይ ታደሰ ሂሩት መለሰ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- የፃልቄ የትምህርትና የተቀናጀ የልማት ማህበር - የቀረበ የለም ተጠሪ፡-
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ በአዋጅ ቁጥር 377/96 መሰረት የቀረበውን የአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ ተጠሪዎች በአሁኑ አመልካች ላይ ሚያዚያ 29 ቀን 2001 ዓ.ም በተፃፈ የክስ ማመልከቻ በመሰረቱት ክስ ነው። የክሱ ይዘትም ባጭሩ አንደኛ ተጠሪ ከአመልካች ድርጅት ታህሳስ 13 ቀን 2000 ዓ.ም ጀምሮ በፔሮግራም ማናጀርነት፣ ሁለተኛ ተጠሪ ደግሞ ከጥቅምት 03 ቀን 2000 ዓ.ም ጀምሮ በኮሚኒቲ ወርከር የስራ መደብ ተቀጥረው እንደሰሩና የስራ ውለ ያላግባብ ሚያዚያ ዐ8 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም መቋረጡን ገልፀው ካሳ፣ የስራ ስንብት፣ ክፍያ ለዘገየበት ክፍያ፣ የማስጠንቀቂያ ጊዜ ክፍያ፣ የሚያዚያ ወር ደመወዝ እና የዓመት እረፍት ክፍያ ከወጪና ኪሳራ ጋር ተከፍሎቸው እንዱሰናበቱ ይወሰን ዘንድ ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚይሳይ ነው። የአሁኑ አመልካች ድርጅትም ለክሱ በሰጠው መልስ፣ ተጠሪዎች ለተወሰነ ጊዜ የተቀጠሩ ሰራተኞች ሆነው የስራ ቅጥር ውላቸውም ለማህበሩ በለጋሽ ድርጅቶች የሚሰጠው እርዲታ በመቆሙ ፔሮጀክቱ የተዘጋ ስለሆነ መቋረጡን ገልፆ የስራ ውል የተቋረጠው በሕጉ አግባብ በመሆኑ የተጠየቁት ክፍያዎች ሉከፈለ አይገባም ሲል ተከራክሯል። የስር ፍርድ ቤትም ክርክሩንና ማስረጃዎችን መርምሮ የስራ ውለ ለአንድ ፔሮጀክት ተጠሪዎች የተቀጠሩ ስለመሆኑ የማያሳይ፣ ተጠሪዎች ለተወሰነ ስራ የተቀጠሩ ሰራተኞች ናቸው ስለማይባለ፣ በአንድ ፔሮጀክት መዘጋት ምክንያት ተጠሪዎችን ማሰናበቱ ህጋዊ አይደለም የሚል ምክንያት በመያዝ የአመልካችን ክርክር ሙለ በሙለ ውድቅ አድርጎ ተጠሪዎች ካሳ፣ የስራ ስንብት ክፍያ፣ የማስጠንቀቂያ ጊዜ ክፍያ፣ የሚያዚያ ወር ደመወዝ እና የዓመት ፈቃድ ክፍያ አመልካች ሉከፍላቸው ይገባል ሲል ወስኗል። በዚህ ውሳኔ አመልካች ባለመስማማት ይግባኙን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቢያቀርብም ስንብቱ ሕገ-ወጥ ተብል ውጤቶቹን በተመለከተም የስር ፍርድ ቤት የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 337 መሰረት ተሰርዞበታል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ ለማስቀየር ነው።
የአመልካች ነገረ ፈጅ ነሐሴ 01 ቀን 2001 ዓ.ም በፃፈት ሦስት ገፅ የሰበር አቤቱታ በይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ውሳኔ ላይ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈፅሟል የሚለበትን ምክንያት ዘርዝረው አቅርበዋል። ይዘቱም ባጭሩ ተጠሪዎች ለተወሰነ ስራ የተቀጠሩና የተቀጠሩበት ፔሮጀክት የተዘጋ መሆኑ ተረጋግጦ እያለ ስንብቱ ሕገ-ወጥ ነው ተብል ተጠሪዎች የተለያዩ ክፍያዎች ተከፍሎቸው እንዱሰናበቱ መወሰኑ ያላግባብ ስለሆነ ሉታረም ይገባዋል የሚል ነው።
አቤቱታው ተመርምሮም የተጠሪዎች የስራ ውል ለተለየ ፔሮጀክት የተቀጠሩ መሆኑን የሚያስረዲ ባለመሆኑ ተጠሪዎች ይሰሩበት የነበረው ፔሮጀክት ተቋርጧል በሚል የስራ ስንብቱ ሕገ-ወጥ ነው መባለ እና የተለያዩ ክፍያዎች እንዱከፈለ መወሰኑ ባግባቡ መሆን ያለመሆኑን ለመመርመር ሲባል ለሰበር ችልቱ እንዱቀርብ ተደርጎ ተጠሪዎች ቀርበው ታህሳስ ቀረቡ 13 ቀን 2002 ዓ.ም በተፃፈ ሁለት ገፅ ማመልከቻ ተጠሪዎች የተቀጠሩት ለጠቅላላ ፔሮጀክት በመሆኑ የአመልካች የሰበር አቤቱታ ቅሬታ ነጥቦች ተገቢነት የላላቸው መሆኑን፣ በአንፃሩ የይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤትን ውሳኔ ተገቢነት ያለው መሆኑን በመዘርዘር መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት አልተፈፀመም ሲለ ተከራክረዋል። የአመልካች ነገረ ፈጅም ታህሳስ 19 ቀን 2002 ዓ.ም በተፃፈ ሁለት ገፅ የመልስ መልስ ሰጥተዋል። ይህ ችልትም ጉዲዩን መርምሮ ግራ ቀኙን ጥር 12 ቀን 2002 ዓ.ም በዋለው ችልት ያነጋገረ ሲሆን ግራ ቀኙ የስራ ውል ለጠቅላላ ፔሮጀክት የተደረገ መሆኑንና አመልካች ድርጅትም በአሁኑ ወቅት ስራውን እየሰራ እንደሚገኝ ተማምነዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
እንደመረመረውም የአመልካች እርምጃ ሕገ-ወጥ ተብል ተጠሪዎች የተለያዩ ክፍያዎች ተከፍሎቸው እንዱሰናበቱ የተወሰነው ባግባቡ ነው ወይም አይደለም? የሚለው ነጥብ በጭብጥነት ላታይ የሚገባው ሆኖ ተገኝቷል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው አመልካች ተጠሪዎችን አሰናበትኩ የሚለው ተጠሪዎች የተቀጠሩበት ፔሮጀክት በመዘጋቱ ነው የሚል ምክንያት ሲሆን ተጠሪዎች ደግሞ ቅጥሩ ለተዘጋው ፔሮጀክት ሳይሆን ለጠቅላላ ፔሮጀክት ሆኖ ድርጅቱ በአሁኑ ወቅት በስራ ላይ ይገኛል በማለት የሚከራከሩ ሆኖ ቅጥሩ ለጠቅላላ ፔሮጀክት ስለመሆኑ በዚህ ችልት በተደረገው ማጣራት መረጋገጡን ነው። ይህ ፍሬ ነገር ከተረጋገጠ ደግሞ በተጠሪዎች እና በአመልካች መካከል ያለው ግንኙነት መገዛት ያለበት በመካከላቸው በተቋቋመው ውል በመሆኑ ተጠሪዎች በአዋጁ ቁጥር 377/96 አንቀፅ 10(1ሀ) መሰረት ለአንድ ለተለየ ፔሮጀክት የተቀጠሩ ሰራተኞች አለመሆናቸውን መገንዘብ አስቸጋሪ አይሆንም።
No topics extracted.
በመሆኑም በጉዲዩ ላይ የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ነው ለማለት አልተቻለም። በዚህም ምክንያት ተከታዩን ወስነናል።
በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ ሰኔ 03 ቀን 2001 ዓ.ም ተሰጥቶ በፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ሐምል 30 ቀን 2001 ዓ.ም በከፉል የፀናው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሰረት ፀንቷል።
በዚህ ችልት በተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሳራ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
በዚህ ችልት ነሐሴ 29 ቀን 2001 ዓ.ም ተሰጥቶ የነበረው እግድ ተነስቷል። ይጻፍ።