No summary available.
የካቲት 10 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ሐጏስ ወልደ ሂሩት መለሰ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ አመልካች፡- የሕፃን ዮናታን ነጋ ተሻገር ሞግዚት - ጠ/ጥጋቡ ጌጤ ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ለገሰ አበራ - ጠ/ወርቁ መንገሻ ቀረቡ መዝገቡን መርመረን ፍርድ ሰጥተናል።
በዚህ መዝገብ የቀረበው ጉዲይ በሞት ምክንያት የሥራ ውል ሲቋረጥ ለሰራተኛው ጥገኞች ስለሚከፈል ካሣ የአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 110 አተረጓጏምን የሚመለከት ነው።
የአመልካች አባት አቶ ነጋ ተሻገር በተጠሪ ተቀጥረው ለሥራ ሲንቀሳቀሱ ሕይወታቸው በማለፈ ያልተከፈለ ደመወዝ ብር 6,500 /ስድስት ሺህ አስምት መቶ/፣ ያልተከፈለ አበል ብር 9,750 /ዘጠኝ ሺህ ሰባት መቶ ሀምሳ/፣የቀብር ማስፈጸሚያ ወጪ ብር 2000 /ሁለት ሺህ/ እና ሟች ላላ ጥገኛ ስላልነበራቸው የሞት ካሣ ክፍያ ብር 60,000 /ስልሳ ሺህ/ እንዱከፈል አመልካች በሞግዚቱ አማካይነት ክስ መሰረተ። የሥር ፍ/ቤት ተጠሪ ያቀረቡትን የመጠን ክርክር በማስረጃ አጣርቶ ከካሣ ገንዘብ በተቀረ ላልቹን እንደ ክሱ አቀራረብ ወስኗል የሞት ካሣ አከፊፈል አስመልክቶ አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 110/3/ /ለ/ እድሜያቸው 18 ዓመት ያልሞላቸው ልጆች የእያንዲንዲቸው ድርሻ 10% ብቻ ነው በሚል ከተጠየቀው ብር 60,000 /ስልሳ ሺህ/ ውስጥ 10,000 (አስር ሺህ) ብቻ እንዱከፈል ወስኗል።
በዚህ ውሳኔ አመልካች ቅር ተሰኝቶ ለፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ ያቀረበ ሲሆን ከፍተኛው ፍ/ቤትም ተጠቃሹ ድንጋጌ የአንደን ጥገኛ ድርሻ ለላላኛው እንዱከፈል ሕጉ በግልጽ አልደነገገም የሚል ምክንያት ሰጥቶ የሥር ፍ/ቤት ውሳኔን አጽንቷል።
የሰበር አቤቱታ የቀረበው ይህ የሥር ፍ/ቤቶች ውሳኔ የአዋጁን አንቀጽ 110/3/ በአግባቡ አልተረጏመም፣የሟች ብቸኛ ወራሽ እና ጥገኛ አመልካች ነው፤እንዱሁም ሟች ሚስት አልነበረውም፤የሚስትም ድርሻ ጭምር ታስቦ ለአመልካች ሉከፈል ይገባል አመልካችም የተወለደው ከጋብቻ ውጪ ነው የአመልካች ሞግዚት አክስቱ ናቸው በሚለ ፍሬ ነገሮች መነሻ የሥር ፍ/ቤት ውሳኔ እንዱታረም አመልክተዋል።
ይህ ሰበር ሰሚ ችልት የሥር ፍ/ቤት የአዋጁን አንቀጽ 110 አተረጓጏም አግባብነት ለመመርመር ተጠሪን አስቀርቧል። ከተያዘው ጭብጥ አንፃር ጉዲዩ ከሕጉ ጋር በማገናዘብ መርምረናል።
በተያዘው ጉዲይ የአመልካች ወላጅ አባት በተጠሪ ተቀጥረው ሥራ ላይ እያለ ሕይወታቸው ማለፈ አላከራከረም።
የአመልካች አባት በሥራ ላይ በሞት የተለዩ ስለመሆኑ እስከተረጋገጠ ድረስ የሞት ካሣ ለጥገኞች ስለሚከፍልበት ሁኔታ በዝርዝር የተደነገገው በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀጽ 110 እንመለከታለን።
በተጠቀሰው አንቀጽ 110/1/ የተመለከተው ሉከፈል የሚገባው የክፍያ ዓይነት ነው። ይህም አንደ ለጥገኞች የሚከፈል ካሣ ነው። ለጥገኞች የሚከፈል ካሣ መጠን እና ጥገኞች የሚባለት እነማን እንደሆኑ ድንጋጌው በቀጣይ ንኡስ አንቀጾች አመልክቷል። የሟች ጥገኞች ብል ሕጉ የዘረዘራቸው የሟች ልጆች ሆነው 18 ዓመት በታች የሆኑ፣የሟች ሕጋዊ ባል ወይም ሚስት እና በሟች ሰራተኛ ድጋፍ ይረደ የነበሩ የሟች ወላጆች መሆናቸውን አንቀጽ 110/2/ ዝርዝር ያመለክታል። በተያዘው ጉዲይ ከአመልካች ላላ የቀረበ የሟች ጥገኛ ነኝ ባይ የላለ መሆኑ ከመዝገቡ ተረድተናል።
ቀጥል ላታይ የሚገባው ጉዲይ የካሳ ስላት እና የአከፊፈለ ሁኔታ ነው። ሉከፈል የሚገባው ካሳ መጠን አስመልክቶ የአዋጅ አንቀጽ 110/3/ የመጀመሪያው አረፍተ ነገር ይገልፃል። ይኸውም “የሰራተኛው የዐመት ደመወዝ በአምስት ተባዝቶ የሚገኘው” የገንዘብ መጠን ነው። ስለሆነም የክፍያው መጠን ጣሪያ በሕጉ በግልጽ ተወስኗል። ከዚህ ተከትል የሚታየው ይህንን ገንዘብ በጥገኞች መካከል የሚከፊፈልበት ሥርአት የሚያመለክት ድንጋጌ ነው። ለዚህም የሟች ጥገኞች ናቸው ተብለው ከላይ የተዘረዘሩት የእያንዲንዲቸው ድርሻ መጠን በመቶኛ በአንቀጽ 110/3/ ሀ-ሐ ተዘርዝሯል። ከፍ ሲል የተመለከትነው የጥገኞች ማንነት፣ሉከፈል የሚገባው ካሣ መጠን ጣሪያው እና የስላቱ አወሳሰን እንዱሁም የጥገኞች ድርሻ መጠን አስመልክቶ በሕጉ የተዘረዘሩትን መሰረተ ሐሳቦች ነው።
ከተያዘው ጉዲይ አንፃር አከራካሪው ሟች አንድ ጥገኛ ብቻ ያለው መሆኑ በታወቀ ጊዜ ሉከፈል የሚገባው የካሳ መጠን ጣሪያው የተወሰነው (100%) ወይንስ ከላይ በዝርዝር በተመለከተው መሰረት የጥገኛው ማንነት ተከትል የተቀመጠው መቶኛ የሚለው ጉዲይ ነው። ይህንን አከራካሪ ጭብጥ መልስ ለማግኘት የአዋጅ ቁጥር 377/96 ድንጋጌ አንቀጽ 110/4/ በዝርዝር መመርመር ተገቢ ነው። የዚህ ድንጋጌ ይዘት እንዱህ ይነበባል።
“በዚህ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ 3 የክፍፍል መጠን መሰረት ተሰልቶ የክፍፍለ መጠን በድምር (100%) (መቶ በመቶ) የሚበልጥ እንደሆነ የክፍፍለ ድምር መጠን 100%(መቶ በመቶ) እስኪሆን ከእያንዲንደ ጥገኛ ላይ ጥገኛ በየመጠኑ ይቀነሳል። እንዱሁም የክፍፍለ መጠን መከፈል ከሚገባው አጠቃላይ መጠን የሚያንስ የሆነ እንደሆነ የክፍፍለ መጠን መቶ በመቶ እስከሚሆን ለእያንዲንደ ጥገኛ ድርሻ እንደመጠኑ የጨመራል” ይላል።
አንቀጽ 110/4/ ይመለከታል።
ከዚህ ድንጋጌ የመጀመሪያው ዓረፍተ ነገር መገንዘብ የሚቻለው የእየንዲንደ ጥገኛ ድርሻ ተዲምሮ ሉከፈል ከሚገባው ጣሪያ (ወሰን) በላይ የሚሆን ከሆነ የእያንዲንደ ጥገኛ ድርሻ በመቶኛ በሕጉ ከተሰጠው ሉቀነስ እንደሚገባ ነው።
የዚህ ድንጋጌ መንፈስ ሟች ሰራተኛ በርካታ ጥገኞች ቢኖሩት በአዋጁ አንቀጽ 110/3/ ሀ-ሐ በተቀመጠው መጠን ለእያንዲንደ እየተሰላ የአሰሪውን ሃላፉነት መጠን ከጣሪያው(ወሰን) እንዲያልፍ ወይም የአሰሪው ሃላፉነት በአንቀጽ 110/3/ የመጀመሪያው ዐረፍተ ነገር ከተቀመጠው የሥላት መጠን እንዲያልፍ ለመከላከል ነው። ይህ የሕጉ ሐሳብ ተፈፃሚነት የሚኖረው ሟች ሰራተኛ በርካታ ጥገኞች ኖሮት የእያንዲንዲቸው ድርሻ በመቶኛ ድምር ከጠቅላላው መቶኛ ድምር በላይ ሆኖ ሲገኝ ነው ማለት ነው። አንቀጽ 110/4/ ሁለተኛው ዐረፍተነገር ይዘት ደግሞ ሲታይ ሟች ሰራተኛ ያለው ጥገኛ ቁጥር አነስተኛ ሆኖ የእያንዲንዲቸው ድርሻ ስላት ተደምሮ አሰሪው ሉከፈል ከሚገባው በታች ሆኖ ሲገኝ ቀሪውን መቶኛ ገንዘብ ላልቹ ጥገኞች እንዱያገኙት ለማድረግ እንደሚቻል የታሰበ መሆኑን ነው። ይህም ማለት ሟች ሁለት ልጆች ብቻ ቢኖሩት እና ሚስት ባይኖረው በአንቀጽ 110/3/ /ለ/ መሰረት የልጆቹ ድርሻ 20% ሲሆን ቀሪው 80% ተጠቃሚ (ባለመብት ጥገኛ) የለውም ተብል የሚቀር ሳይሆን ለእነዚሁ ልጆች እንደየድርሻው በመቶኛ ሉጨመርላቸው እንደሚገባ የሚያመላክት ነው። የዚህ ድንጋጌ መንፈስ የጥገኞች ቁጥር አነስተኛ ከሆነ የአሰሪ ሃላፉነት ጣሪያ ወሰን ድረስ ያለት ጥገኞች ተጠቃሚ እንዱሁኑ ለማድረግ ያሰበ መሆኑን ያመለክታል።
በተያዘው ጉዲይ ሟች አቶ ነጋ ተሻገር ከአመልካች ላላ ጥገኛ ስለመኖሩ የቀረበ የለም። በሥር ፍ/ቤት የተወሰደው አቋም አመልካች ድርሻ 10% ብቻ ነው የሚል ነው። ነገር ግን የአንቀጽ 110/4/ ድንጋጌ ሁለተኛው ዐረፍተ ነገር እንደሚያስገነዝበው አመልካች ብቸኛ የሟች ጥገኛ መሆኑ እስከተረጋገጠ ድረስ የተጠሪ የሃላፉነት መጠን ጣሪያ ድረስ ካሳው ሉከፈለው ይገባል። ይህም ማለት የአመልካች ድርሻ 10%(አስር በመቶ) ሳይሆን መቶ በመቶ(100%) ነው።
ስለዚህ የሥር ፍ/ቤቶች ይህንን በአግባቡ ሳይገናዝቡ የአመልካች ድርሻ 10% ብቻ ነው በማለት የአዋጁን አንቀጽ 110/3/ለ በመጥቀስ የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለው ሆኖ አግኝተናል።
የአመልካች ድርሻ መቶ በመቶ ነው ከተባለ ስላቱ ምን ያህል ነው ለሚለው የሥር ፍ/ቤት የአመልካች አባት ደመወዝ በወር 1000 /አንድ ሺህ ብር/ መሆኑን መሰረት አድርጏ የሰጠው ፍርድ ተጠሪ ስላልተቃወሙ በአንቀጽ 110/3/ መሰረት በሞት ምክንያት ሉከፈል የሚገባው የካሣ መጠን አመልካች በሥር ፍ/ቤት ያቀረቡት ብር 60,000 (ስልሳ ሺህ ብር) መሆኑን ተገንዝበናል። በዚሁ መሰረት ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
የፋ/መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 22962 የሰጠው ፍርድ እና የፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 66031 የሰጠው ውሳኔ የአመልካች የካሣ ድርሻ አስመልክቶ የሰጡት የውሳኔ ክፍል በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕቁ. 348/1/ መሰረት ተሻሽል ተከታዩ ተወስኗል።
አመልካች የሟች አቶ ነጋ ተሻገር ብቸኛ ጥገኛ መሆኑ ስለተመለከተ በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 110/4/ መሰረት ካሣ ሙለ ለሙለ ሉከፈለው ይገባል ብለናል። ስለሆነም በሟች ደመወዝ ተሰልቶ የቀረበው ብር 60,000 (ሥልሳ ሺህ ብር) ይከፈለው ብለናል። የሥር ፍ/ቤት በዚሁ መሰረት እንዱያስፈጽም ታዟል።
የዚህን ፍ/ቤት ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።
No topics extracted.