No summary available.
የካቲት 12 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ሐጏስ ወልደ ኂሩት መለሰ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- ግዮን ትራቭልና ቱርስ ኃ/የተ/የግ/ማ - ነ/ፈጅ ዲንኤል ወርቅዬ - ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ዲንኤል አስፊው - አልቀረቡም መዝገቡን መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል።
በዚህ መዝገብ የቀረበው የሥራ ውል ማቋረጥን የሚመለከት ነው። ተጠሪ ያለአግባብ ከሥራ መሰናበቱን ጠቅሶ ውዝፍ ደመወዝ ተከፍልት ወደ ሥራ እንዱመለስ እንዱወሰንለት ዲኝነት ጠይቋል። በአመልካች በኩል ሥር ፍ/ቤት የቀረበው ክርክር ተጠሪው የሥራ ሃላፉው ላይ አላስፈላጊ አምባጓሮ፣ ፀብ፣ ዛቻ፣ ስድብ በመፍጠሩ ተሰናብቷል የሚል ነው ጉዲዩን በመ/ደረጃ የተመለከተው የፋ/መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ተጠሪ ሥራ አስኪያጅ ላይ እንደዛተ እንጂ አምባጓሮ ወይም ፀብ ስለፍጠሩ አልተረጋገጠም በሚል ስንብቱ ሕገ-ወጥ ነው ሲል ፈርዶል። አመልካች የአምስት ወር ደመወዝ ለተጠሪ ከፍል ወደ ሥራ እንዱመለስ ሲልም ወስኗል።
ይግባኝ የቀረበለት የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኙን ባለመቀበል መዝገቡን ዘግቷል።
የሰበር አቤቱታ የቀረበው ይህንን ውሳኔ ለማስለወጥ ነው የአመልካች ነ/ፈጅ ጥቅምት 21/2002 ዓ.ም ጽፍ ያቀረበው አቤቱታ ይዘት ተጠሪው የነዲጅ ያቀረበው ደረሰኝ የተጋነነ እና ታማኒነት የጏደለው በመሆኑ በሥራ አስኪያጁ ሲጠየቅ በአግባቡ ማስረዲት ሲገባው ጠብ አጫሪነት በመፍጠር ወይ አንተ ወይ እኔ እንኖራለን በማለት በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 27/1/ ረ መሰረት ጥፊት ስለመፈፀሙ መረጋገጡን ስንብቱ ሕጋዊ ስለመሆኑ በአማራጭ ተጠሪው በአዋጁ አንቀጽ 43/1/ መሰረት ካሣ ተከፍልት ሉሰናበት እንደሚገባ ራሱ የጠየቀው ዲኝነት የሥር ፍ/ቤቶች ማለፊቸው የሕግ ስሕተት መሆኑን ጠቅሶ የሥር ፍ/ቤቶች ውሳኔ እንዱሻር አመልክቷል።
ይህ ሰበር ሰሚ ትልትም በተጠሪ ተፈጽሟል የተባለው ድርጊት ከአዋጁ አንቀጽ 27/1/ረ አንፃር ለመመርመር የሚገባው ሆኖ ስላገኘው ተጠሪ መልስ እንዱሰጥበት አድርጓል ተጠሪ የካቲት 12 ቀን 2002 ዓ.ም የተፃፈ መልስ አቅርቧል። የሥር ፍ/ቤት ውሳኔ የሕግ ስሕተት የለውም ሲል እንዱጸና ጠይቋል።
እኛም የቀረበውን አቤቱታ ከተያዘው ጭብጥ አንፃር ከሕጉ ጋር አገናዝበን መርምረናል።
ከሥር ፍ/ቤት መዝገብ መረዲት የተቻለው ተጠሪው የአመልካች ድርጅት ሥራ አስኪያጅ ላይ የዛቻ ኃይለ ቃል እንደተናገረው ተመስክሯል። በፍሬ ነገር ረገድ የተረጋገጠው የተጠሪ ድርጊት የአዋጁ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 27/1/ረ የተደነገገውን ጥፊት ያሟላል የሚል ክርክር በአመልካች በኩል ቀርቧል። ይህንኑ ለመመረመር የተጠቃሹን ድንጋጌ ይዘት በዝርዝር መመልከት ይገባል። አንቀጽ 27/1/ረ እንደሚከተለው ይነበባል።
“እንደጥፊቱ ክብደት በሥራው ቦታ አምባጓሮ ወይም ጠብ እጫሪነት ተጠያቂ መሆን” ያለማስጠንቀቂያ የሥራ ውል ለማቋረጥ ከሚያስችለ ምክንያቶች ሥር ተመልክቷል። በተያዘው ጉዲይ ተጠሪ የሥራ አስኪያጅን “ወይ አንተ ወይ እኔ እንኖራታለን” በማለት የዛተበት ስለመሆኑ በሥር ፍ/ቤት የተረጋገጠ ፍሬ ነገር መሆኑ ከመዝገቡ መረዲት ችለናል።
ይህ የተጠሪው ድርጊት ከተጠቀሰው ድንጋጌ አንፃር ሲታይ የጠብ አጫሪነት ኃይለቃል መሆኑን መገንዘብ ይቻላል። የሥር ፍ/ቤት የተጠሪው የድርጊት ዛቻ ነው ካለ በኋላ ይህ ድርጊት ፀብ ድርጊት ልባል እንደማይችል ጠቅሶ ይህ ክብደት ሉሰጠው አይገባም ብሎል። በኛ በኩል ስንመረመረው አንድ ሰራተኛ የአሰሪው ወይም የሥራ ኃላፉው ትእዛዝ ከሕግ ውጪ እስካልሆነ ድረስ ማክበር እና መፈጸም እንዲለበት ልብ ልባል ይገባል። አንድ ሰራተኛ አሰሪው ወይም የሥራ ኃላፉው የሚሰጠውን ሕጋዊ ትእዛዛት መፈጸም እንዲለበት አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 13/2/ በግልጽ ተመልክቷል።
ተጠሪ ስለሥራው አካሄድ በሥራ አስኪያጅ ሲጠየቅ አግባብ ባለው ሥርአት ማስረዲት ሲገባው ለምን ተጠየቅኩ በሚል ስሜት ኃይለ ቃል እና ዛቻ ማድረጉ የጠብ አጫሪነት ድርጊት መባል የሚገባው ስለመሆኑ ተረድተናል።
ድርጊቱም የተፈፀመው በአመልካች ድርጅት የሥራ አስኪያጅ ላይ መሆኑ የተጠሪን ድርጊት ጥፊት ከባድነት አመልካች ነው። ስለሆነም የተጠሪው ድርጊት የአዋጁን አንቀጽ 27/1/ረ የተመለከተውን ጥፊት አያሟላም ሲል የሥር ፍ/ቤት የደረሰበት ድምዲሜ ሕግ ያስቀመጠውን የሰራተኛውን ግዳታ የሚመለከተውን ድንጋጌ እና የጥፊቱን አደገኛነት ከተጠቃሹ ድንጋጌ አንፃር በአግባቡ ሳያገናዝብ መሆኑን ስለተረዲን የሥር ፍ/ቤት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈፀመበት ሆኖ አግኝተነዋል።
ስለሆነም ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
የፋዳራል የመ/ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 40658 የሰጠው ፍርድ እና የፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 83563 የሰጠው ትእዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
የተጠሪ የሥራ ውል የተቋረጠው በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 27/1/ረ መሰረት በመሆኑ ስንብቱ ሕገ-ወጥ ልባል አይገባም ብለናል።
ግራ ቀኝ ወጪና ኪሣራ የየራሳቸውን ይቻለ።
No topics extracted.