No summary available.
የካቲት 25 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ መንበረፀሐይ ታደሰ ኂሩት መለሰ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- ውድመጣስ ኑሮ አስመጪና ላኪ ድርጅት - የቀረበ የለም ተጠሪ፡- እነ አቶ ሁኘኛው ሰጠ (11 ሰዎች) - ቀረቡ
በዚህ መዝገብ የቀረበው ጉዲይ የስራ ክርክርን የሚመለከት ነው። ተጠሪዎች በፋ/መ/ደረጃ ፍ/ቤት በመሰረቱት ክስ አመልካች ያለአግባብ ከስራ ያሰናበታቸው በመሆኑ የተለያዩ ክፍያዎች እንዱከፍላቸው ጠይቀዋል። አመልካች ለክሱ መልስ ሲሰጥ የተጠሪዎች የስራ ውል የተቋረጠው ድርጅቱ ለዘለቄታው ስራ በማቆሙ ስለሆነ የተጠየቀው ክፍያ ሉከፈል እንደማይገባና ተጠሪዎችም የቀን ሰራተኞች በመሆናቸው የአመት እረፍት በገንዘብ ተቀይሮ እንዱሰጣቸው ያቀረቡት ጥያቄ ውድቅ እንዱሆን አመልክቷል። ፍ/ቤቱም ጉዲዩን መርምሮ ተጠሪዎች ከስራ የተሰናበቱት ድርጅቱ ለዘለቄታው በመዘጋቱ ስለሆነ ስንብቱ ህጋዊ ነው በማለት አመልካች የስራ ስንብት ክፍያና የማስጠንቀቂያ ጊዜ ክፍያ እንዱከፈላቸው ወስኗል። በዚህ ውሳኔ ላይ አመልካች ለፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ አቅርበው ፍ/ቤቱ ይግባኙን ባለመቀበል መዝገቡን ዘግቷል። አመልካች የሰበር አቤቱታ ያቀረበው ይህንን ውሳኔ ለማስለወጥ ነው። በቅሬታውም አመልካች ድርጅት የተዘጋው በባንክ እዲ ምክንያት ባንኩ ተረክቦት በመሆኑ ማስጠንቀቂያ መስጠት አስፈላጊ አይደለም እንዱሁም ተጠሪዎች በአዋጁ አንቀጽ 10/ሰ/ መሰረት የተቀጠሩ የቀን ሰራተኛ በመሆናቸው ስራ ስንብት ክፍያ ሉከፈላቸው አይገባም በማለት ቅሬታውን አቅርቧል። ይህ ችልት የተጠሪዎች የስራ ስንብት ህጋዊ ከሆነ የስራ ስንብትና የማስጠንቀቂያ ጊዜ ክፍያ እንዱከፈላቸው መወሰኑ አግባብ መሆን አለመሆኑን ለመመርመር አቤቱታው ለሰበር ችልት ያስቀርባል ብሎል።
ተጠሪዎችም ክርክራቸውን በፁሁፍ አቅርበዋል። መዝገቡም ተመርምሯል።
አመልካች ድርጅት ለዘለቄታው በመዘጋቱ ተጠሪዎች ከስራ መሰናበታቸውን የስር ፍ/ቤቶች አረጋግጠዋል።
አመልካች በክርክር ድርጅቱ የተዘጋው በባንክ እዲ ምክንያት ባንኩ ድርጅቱን በመረከቡ ስለሆነ የማስጠንቀቂቃ ጊዜ ሉከፈል አይገባም በማለት ተከራክሯል። ነገር ግን በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 28/2/ሀ/ ሰራተኞች የተሰማሩባቸውን ስራዎች በከፉልም ሆነ በሙለ በቀጥታና ለዘለቄታው የሚያስቆም የሰራተኛ ቅነሳ የሚያስከትል ሁኔታ ሲከሰት የስራ ውለ በማስጠንቀቂያ ሉቋረጥ እንደሚችል ይገልፃል። ድንጋጌው የድርጅቱ ስራ በከፉል ብቻ ሳይሆን በሙለ ለዘለቄታው ሲቆም ማስጠንቀቂያ ላሰጥ እንደሚገባው የሚያሳይ ነው። ድርጅቱ በሙለ ስራ ካቆመ የቅነሳ ጥያቄ ሉነሳ አይችልም።
ይልቁንም ሰራተኞች በሙለ የሚሰናበቱበትን ሁኔታ ነው የሚያስከትለው። በተያዘውም ጉዲይ ድርጅቱ ስራውን በሙለ ለዘለቄታው የሚያስቆም ሁኔታ በመከሰቱ አመልካች የስራ ውለን ሲያቋርጥ ማስጠንቀቂያ ላሰጥ ይገባዋል። በመሆኑም አመልካች ማስጠንቀቂያ ላሰጥ የሚገባው ቅነሳ ሲደረግ ብቻ እንጂ ድርጅቱ እንዲለ ሲዘጋ አይደለም በማለት ያቀረበው ክርክር ተቀባይነት የለውም።
በልላ በኩል ተጠሪዎች የአመልካች ድርጅት ሰራተኞች መሆናቸው በስር ፍ/ቤቶች የተረጋገጠ ፍሬ ነገር ነው።
አመልካች ተጠሪዎች የቀን ሰራተኞች ናቸው በማለት ይከራከር እንጂ የስር ፍ/ቤቶች ክርክሩን አልተቀበለትም። የሙከራ ጊዜውን የጨረሰ ሰራተኛ ድርጅቱ በመክሰሩ ወይም በልላ ምክንያት ለዘለቄታው በመዘጋቱ የስራ ውለ ሲቋረጥ የስራ ስንብት ሉከፈል እንደሚገባ የአዋጁ አንቀጽ 39/1/ሀ/ ይገልፃል። በመሆኑም ድርጅቱ ለዘለቄታው በመዘጋቱ ለተጠሪዎች የስንብት ክፍያ እንዱከፈላቸው የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የለውም።
የፋ/መ/ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 34121 መስከረም 28 ቀን 2001 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔና የፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 70887 ኀዲር 25 ቀን 2001 ዓ.ም የሰጠው ትእዛዝ ፀንቷል።
ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።
No topics extracted.