No summary available.
የካቲት 11 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም.
ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ሐጎስ ወልደ ሑሩት መለሰ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ አመልካች፡- ተንዲሆ ስኳር ፊብሪካ ፔሮጀክት - አንዲርጋቸው በየነ ቀረቡ።
ተጠሪዎች፡-
ኃይላ ይማም - ቀረበ።
ዓሉ ሐሰን - ቀረበ።
መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ለአቤቱታው መነሻ የሆነው ጉዲይ በአሰሪና ሰራተኞች መካከል የተነሳውን የሥራ ክርክር የሚመለከት ነው።
ክርክሩ በተጀመረበት በደብቲ ደአር ወረዲ ፍ/ቤት ከሣሾች የነበሩት ተጠሪዎች ናቸው። በአመልካች ላይ ክስ የመሰረቱት ሥራችንን በገዛ ፈቃዲችን ለመተው የፈለግን ስለሆነ የአገልግልት ካሣ ከፍልና ምስክር ወረቀት በመስጠት እንዱያሰናብተን ይወሰንልን በማለት ነው። አመልካች ለክሱ በሰጠው መልስ ተጠሪዎች በጡረታ የሚገለለ ከመሆናቸው በተጨማሪ የአገልግልት ካሣ ሉከፈላቸው አይገባም በማለት የተከራከረ ሲሆን፣ ፍ/ቤቱ ግን ክርክሩን ውድቅ በማድረግ የተጠየቀውን የአገልግልት ካሣ እንዱከፈል ወስኖአል። ጉዲዩ በይግባኝ የቀረበለት በአፊር ብ/ክ/መ/የአውሲ ረሱ ከፍተኛ ፍ/ቤትም እንደዚሁ ክርክሩን የሰማ ሲሆን፣ በመጨረሻም ይግባኝ የተባለበትን ውሣኔ አጽንቶአል። የሰበር አቤቱታ የቀረው በዚህ ላይ ነው።
እኛም አመልካች ግንቦት 27 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም. በፃፈው ማመልከቻ ያቀረበውን አቤቱታ መሰረት በማድረግ ተጠሪዎችን አስቀርበን ክርክሩን ሰምተናል። ክርክሩ የተሰማው ተጠሪዎች የአገልግልት ካሣ /የስንብት ክፍያ/ ይከፈላቸው የመባለን አግባብነት ከመመርመር አንፃር ነው። በመሆኑም በዚህ ረገድ ግራ ቀኝ ወገኖች ያሰሙት ክርክር አቤቱታ ከቀረበበት ውሣኔ እና ከሕጉ ጋር አገናዝበን ተመልክተናል።
በሥር ፍ/ቤቶች በተደረገው ክርክር ያልተካደው ወይም የተረጋገጠው ተጠሪዎች የክፍያ ጥያቄን እና ስንብትን መሰረት በማድረግ ክስ የመሰረቱት በጡረታ የሚገለለበት ጊዜ እንደደረሰ ነው። አመልካች የክፍያ ጥያቄውን ከሥር ጀምሮ ሲቃወም የመጣውም ተጠሪዎች መደበኛ የጡረታ ዕድሜ የደረሱና የጡረታ አበልም የሚከፈላቸው ናቸው በማለት ነው። ተጠሪዎችም በዚህ መልክ ከአመልካች የቀረበውን ክርክር የሚያስተባብል ክርክርም ሆነ ማስረጃ አላቀረቡም። የሥር ፍ/ቤቶችም ቢሆኑ ተጠሪዎች በአመልካች ዘንድ ማገልገላቸውን ብቻ በማየት ወሰኑ እንጂ በሕጉ የተቀመጠውን ድንጋጌ ከቀረበላቸው የፍሬ ነገር ክርክር ጋር አላገናዘቡም።
የአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ ቁ. 377/96“ን” ለማሻሻል በወጣው አዋጅ ቁ. 494/98 አንቀጽ 2/2/ሰ/ እና /ሸ/ ከተቀመጡት ድንጋጌዎች መገንዘብ እንደሚቻለው በአዋጅ ቁ. 377/96 አንቀጽ 39 እንደተደነገገው የሥራ ስንበት ከፍያ የሚከፈለው ሰራተኛው የፔሮቪደንት ፈንድ ሽፊን ወይም የጡረታ መብት የላለው ከሆነ እንደዚሁም ሥራውን ሲለቅ መደበኛ የጡረታ ዕድሜ ያልደረሰ ሲሆን ነው። በያዝነው ጉዲይ ተጠሪዎች ሥራችንን በገዛ ፈቃዲችን ለቀናልና የስንብት ክፍያ እንዱከፈለን ይወሰንልን በማለት ክስ የመሰረቱት የጡረታ መውጫ እድሜያቸው ሳይደርስና ተገቢውን ዝግጅት እንዱያደርጉ አመልካች ካስታወቃቸው በኋላ እንደሆነ በአመልካች ክርክር ተመልክቶአል። ተጠሪዎች ይህ እውነት ላለመሆኑ ያሳዩት ነገር የለም። ከዚህ እንግዱህ መገንዘብ የሚቻለው ተጠሪዎች የጡረታ መብት ያላቸው ብቻ ሳይሆኑ፣ መደበኛ የጡረታ ዕድሜም የደረሱ መሆናቸው ጭምር ነው። በመሆኑም የስንብት ክፍያ የሚያገኙበት የሕግ አግባብ የለም። የሥር ፍ/ቤቶች የሰጠው ውሣኔም ከዚህ አንፃር ሲታይ በሕጉ አተረጓጎም ረገድ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነው ለማለት ችለናል።
ው ሣ ኔ
በአፊር ብ/ክ/መ/ የደብቲ ደአር ወረዲ ፍ/ቤት በፍ/ብ/መ/ቁ. ዐ956/2ዐዐዐ ሐምል 1ዐ ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. የሰጠው ውሣኔ እና የአውሲ ረሱ ከፍተኛ ፍ/ቤት በይ/መ/ቁ. 1279 ግንቦት 1ዐ ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም. የሰጠው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽረዋል።
ተጠሪዎች ያቀረቡት የሥራ ስንብት ክፍያ ሉያገኙ አይችለም በማለት ወስነናል።
No topics extracted.